Gamo nation

Gamo nation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gamo nation, Digital creator, Addis Ababa.
(2)

ጥሪ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህዝብን ብር ያልመዘበረ ንፁህ እጅ ሊሸለም ይገባዋል ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር በተደረገው የታላቁ የ...
25/08/2026

ጥሪ ለዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን

ይህ የድሃ ኢትዮጵያውያን ህዝብን ብር ያልመዘበረ ንፁህ እጅ ሊሸለም ይገባዋል

ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ጋር በተደረገው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አስቸጋሪ ድርድር ወቅት የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በፅናት የተሞገቱትንና የዲፕሎማሲያዊ ግምባር መሪ የነበሩትን የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ዛሬ በስደት ሀገር በተራ የመኪና ማቆሚያ ስራ ላይ ተሰማርተው ማየት በእጅጉ የሚያሳዝንና የሚያስቆጭ አጋጣሚ ነው።

በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ በከፍተኛ የስልጣን ማዕረግ ላይ የነበሩ ሰዎች የህዝብን ሀብት ዘርፈው በውጭ ሀገር ባንኮች በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር አካብተው በቅንጡ ህይወት ሲኖሩ ማየት በተለመደበት በዚህ ዘመን፣ አቶ ገዱ በስልጣን ዘመናቸው እጃቸውን ከሙስና እና ከሀገር ሀብት ምዝበራ ያቀቡ ታማኝ መሪ መሆናቸውን ዛሬ በራሳቸው ላብና ጥረት ለመኖር የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ህያው ምስክር ነው።

ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላት እና ሀገር ወደድ ወገኖች፣ ይህንን የታማኝነት እና የህሊና ንጽህና አርአያ የሆነ ታላቅ ሰው በሰው ሀገር በጉልበት ስራ እንዲንገላታ መተው የለብንም።

ሀገራቸውን በቆራጥነት ያገለገሉ እና የህዝብን አደራ ያልበሉ ንጹሃን መሪዎችን ማከበርና መደገፍ የታማኝነትን ዋጋ የሚያጎላ ከመሆኑም በላይ ለቀጣዩ ትውልድና ለሌሎች ባለሥልጣናት ትልቅ አስተምህሮ የሚሰጥ ነው።

እኒህ ክቡር ሰው ያላቸውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲና የአመራር ልምድ ተጠቅመው የሚገባቸውን የክብር ቦታ እንዲያገኙ፣ ባሉበት ሀገር የግል ቢዝነሳቸውን ማስጀመር የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ እና ተገቢውን የሞራልና ቁሳዊ ድጋፍ በመስጠት ከጎናቸው እንድንቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ዛሬ 14 ዓመታት ተቆጠሩ።ስለ አቶ መለስ ሲያስቡ ቀድሞ ወደ አዕምሮዎ የመጣው ምንድነው ❓
20/08/2026

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ዛሬ 14 ዓመታት ተቆጠሩ።

ስለ አቶ መለስ ሲያስቡ ቀድሞ ወደ አዕምሮዎ የመጣው ምንድነው ❓

ሰበርአቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ! ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን ...
17/08/2026

ሰበር

አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ!

ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን በቅድመ ሁኔታ የታሠረ የምኅረት መጠየቂያ ሠነድ መፈረማቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርሰቲያን ታደለን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይንን ጨምሮ በርካታ እስረኞች የምኅረት መጠየቂያውን በመሙላት ስምምነታቸውን እንደገለጡ ምንጮች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። አምስት ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን ጨምሮ 30 ያህል እስረኞች ግን ሠነዱን 'አንፈርምም' ማለታቸው ታውቋል።

ሠነዱን አንፈርምም ካሉት መካከል፤ የአማራ ክልል ምክር አባሉ ዮሐንስ ቧያለው፤ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደወሠን አሠፋ፣ መስከረም አበራ እና ጎበዜ ሲሳይ ይገኙበታል ተብሏል። የምኅረት ሠነዱን እንዲፈርሙ የቀረበላቸው እስረኞች 300 ገደማ እንደሚጠጉ ታውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ውለዋል ድርጊቱን የፈፀሙት ሶስት ናቸወ።አሁን በተገኘው ትክክለኛ መረጃ መሰረት ልጆቹ አለምን ባንክ ፖሊስ ጣቢያ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።ድርጊቱን የፈፀሙት ወንጀለኞ...
17/08/2026

በቁጥጥር ስር ውለዋል
ድርጊቱን የፈፀሙት ሶስት ናቸወ።አሁን በተገኘው ትክክለኛ መረጃ መሰረት ልጆቹ አለምን ባንክ ፖሊስ ጣቢያ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ድርጊቱን የፈፀሙት ወንጀለኞች ስም ዝርዝር

1,ፊርደውስ
2,ሀናን
3,ኤደን

ድብደባ የተፈፀመባት ልጅ ስም-ኦብሳ (ኦብሴ

ተገቢውን ፍትህ ለተበዳይዋ እንደሚሰጣት ተስፋ እናደርጋለን።

Via ዘመን ተሻጋሪው

ከኋላ ትዝታ አለ፣ እውነት አለ፣ ታሪክ አለ፤ከፊት ተስፋ አለ፣ እቅድ አለ፣ ለውጥ አለ።ትላንቱም በእኛ፣ ነገም በእኛ እጅ ነው፤የትላንቱን ትምህርት ይዘን፣የነገን ተስፋ እንገንባለን።ያለፈው ለ...
16/08/2026

ከኋላ ትዝታ አለ፣ እውነት አለ፣ ታሪክ አለ፤
ከፊት ተስፋ አለ፣ እቅድ አለ፣ ለውጥ አለ።

ትላንቱም በእኛ፣ ነገም በእኛ እጅ ነው፤
የትላንቱን ትምህርት ይዘን፣
የነገን ተስፋ እንገንባለን።

ያለፈው ለመርሳት አይደለም፣
ለመማር ነው፤
የሚመጣውምlን ለመጠበቅ ብቻ አይደለም፣
በእጃችን ለመፍጠር ነው።

ትላንትን እናከብራለን፣
ዛሬን እንኖራለን፣
ነገን እንገነባለን

ካሙዙ ካሳ

"ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት"በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የ 2018 የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በድምቀ...
16/08/2026

"ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት"

በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ
ጽ/ቤት "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የ 2018 የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በድምቀት አካሂዷል።

በብልፅግና ፓርቲ አባላት ተሳትፎ ብዙ ተግባራት ማከናወን መቻሉን በመግለፅ ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህታማማችነት ማዕከል ያደረገ የውስጥ ዴሞክራሲን በማጎልበት ለቀጣይ ሁለንታዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ የፈጠር ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከተሰሩ ተግባራት ውስጥ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የተደረገው ጥረት የአባላት ተሳትፎ ጠንካራ የነበረ መሆኑና አቅም ለመገንባት የተደረገው ጥረት በጥንካሬ የተነሳ ሲሆን በጥቅሉ ከፖለቲካና ድርጅት ስራዎች እንዲሁም ከሚዲያ ተግባራት አንፃር የተሻለ ስራ መሰራት መቻሉን ተገልጿል ።

አባላቱ በሰጡት አስተያየት፤ የፓርቲውን የጋራ አቋም ለማጠናከርና በቀጣይ ለሚከናወኑ ተግባራት አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ የተሰጣቸውን ህዝባዊ አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።ይህ የማጠቃለያ ኮንፍረንስ ቀጣይ አቅጣጫዎች ለመጠቆም እና የተገኙ ድሎችን ወደ ላቀ አፈፃፀም ግንባታ ለማሸጋገር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል። በኮንፍረንሱ ላይ የወረዳው አመራሮች እና የፓርቲ አባላት ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ መስከረም ላይ በባህርዳር ስቴዲየም ከሴኔጋል ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለችሳይዶ ማኔ ግን ራሱን ከብሄራዊ ቡድኑ ስላገለለ ወደ ኢትዮጵያ አይመጣምሸገር ስፖርት
15/08/2026

ኢትዮጵያ መስከረም ላይ በባህርዳር ስቴዲየም ከሴኔጋል ጋር ጨዋታዋን ታደርጋለች

ሳይዶ ማኔ ግን ራሱን ከብሄራዊ ቡድኑ ስላገለለ ወደ ኢትዮጵያ አይመጣም

ሸገር ስፖርት

15/08/2026

“ሀሮሜ”፣ በኦሮሚያ ክልል ለአርሶ አደሮች ምቹና ዘመናዊ መኖሪያን የመፍጠር ሒደት

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ብዙ የመልማት አቅም እያላቸውና ተረስተው የቆዩ የገጠር አካባቢዎችን በማልማት ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ ነው፡፡

ለዚህም በከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት በገጠር አካባቢዎች በመተግበር የአርሶ አደሮች የኑሮ ዘይቤ እንዲሻሻል እያደረገ ነው፡፡

የኦሮሚያ ክልል በዚሁ እሳቤ መሠረት “ሀሮሜ” በሚል ስያሜ በተሰየመ መርሐ ግብር ገጠርን ወደ ዘመናዊነት ለማሸጋገር በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡

ሀሮሜ በኦሮሚያ ክልል ያሉ ገጠራማ ቀበሌዎችን የለውጥ ማዕከላት ለማድረግ የታቀደ መርሐ ግብር ነው፡፡

ሀሮሜ ፕሮግራም የግንባታ ሥራ ብቻ አይደለም፤ የልማት አስተሳሰብን መቀየርና ገጠርን ወደ አዲስ የልማት ደረጃ ማሸጋገር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

ዘመናዊነት ማለት የልማት መሠረተ ልማቶችን፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶችን፣ የፋይናንስና የፍትሕ ተቋማትን፣ ገበያን እንዲሁም አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን የምርታማነት ማዕከል ለማድረግና ወደ ሕዝቡ ማድረስን ያካትታል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሀሮሜን ሲመሠርት፣ የመንግሥት አገልግሎት፣ መንገድ፣ ውሃ፣ ኃይል፣ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ጣቢያዎች፣ መድኃኒት ቤቶች፣ ባንኮችና ሌሎች አገልግሎቶችን ወደ አርሶ አደሮች መኖሪያ አካባቢ ለማድረስ ዓላማ አድርጎ ነው፡፡

ሀሮሜ በገጠር፣ በከተማና በመንግሥት መካከል ያለውን ትስስርና ግንኙነት በአዲስ መንገድ ለመገንባት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡

የገጠር ሽግግር ማለት ግብርናን ብቻ ማሻሻል ሳይሆን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወትንም አብሮ ማሸጋገር ይጠይቃል፡፡

ገጠርን የጥሬ ዕቃ ምንጭ ብቻ አድርጎ ከመመልከት በመውጣት፣ የምርታማነት፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ የሙያና የፈጠራ እንዲሁም የብልጽግና ማዕከላት ወደማድረግ መቀየር ያስፈልጋል፡፡

መንግሥት በርካታ የገጠር መኖሪያ አካባቢዎችን ከከፋ ችግር በማውጣት፣ በሀሮሜ አማካይነት የሕዝቡ ኑሮ እንዲለወጥ በቁርጠኝነት እየሠራ ነው፡፡

በገጠር እየተገነቡ ያሉት የሀሮሜ ቤቶች ምቹ ከመሆናቸው በላይ የአርሶ አደሩ ሀብት እየሆኑ መምጣታቸውን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

መርሐ ግብሩ በአንድ በኩል የሕዝቡን ኑሮ በማሻሻል፣ በሌላ በኩል ደግሞ ኢንቨስትመንትና ከተማነትን በተግባር ላይ እያዋለ እንደሚገኝ ነው ያወሱት፡፡

ሀሮሜ የገጠር ሕዝብን ወደ ዘመናዊነት በማቅረብ ሁሉም ገጠራማ አካባቢዎች በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያደርግ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ የተገነቡት የሀሮሜ ማዕከላት ለምረቃ እየተዘጋጁ ይገኛሉ፡፡

በአቤል ነዋይ

"የመጨረሻው ግባችን ሰው ነው። የሚበለፅገው መሬቱ ወይ መሰረተ ልማቱ ሳይሆን የዚህ ሁሉ ስራ ተጠቃሚው ሰው ነውና ዋናው ማዕከላችን ሰው ነው። ከተማችን ላይ ማንኛውም የምንሰራው ስራ የሰው አ...
11/08/2026

"የመጨረሻው ግባችን ሰው ነው። የሚበለፅገው መሬቱ ወይ መሰረተ ልማቱ ሳይሆን የዚህ ሁሉ ስራ ተጠቃሚው ሰው ነውና ዋናው ማዕከላችን ሰው ነው። ከተማችን ላይ ማንኛውም የምንሰራው ስራ የሰው አኗኗር እንዲቀየር የሰው ህይወት ላይ ለውጥ እንዲያመጣ ነው።"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መሎ ግን እንዴት ተደብቆ ኖረ?ከጨው በስተቀረ የማያመርተው ወደ ሌለ ምድረ ገነት ሄጄ መጣሁ። የጎፋን ተራሮች ከመድፈር ወደ ደኑን ማጣጣም ያደገ ጉዞዬ ኬታማ ነበር። ሲርሶ ጥብቅ ደን ነው። 3...
11/08/2026

መሎ ግን እንዴት ተደብቆ ኖረ?
ከጨው በስተቀረ የማያመርተው ወደ ሌለ ምድረ ገነት ሄጄ መጣሁ። የጎፋን ተራሮች ከመድፈር ወደ ደኑን ማጣጣም ያደገ ጉዞዬ ኬታማ ነበር። ሲርሶ ጥብቅ ደን ነው። 3503.38 ሄክታር ስፋት ሲኖረው በአገር በቀል እፅዋት ተሸፍኗል። በዚያ ውስጥ ማደርን አስቡት? የማይዘሎ ቀበሌ ሰው ደስ እንዲለኝ አድርጎኛል። በኮረሪማዋ ምድር እስከ ቱርሞ ፏፏቴና ዋሻ ተጓዝኩ። መሎ ተደብቆ የኖረ ምድር ነው። የጎፋን ፀጋዎች መቁጠር ቀጥለናል።
Saro Hiking
Gofa Zone Government Communication Affairs Department
የቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Tourism-Ethiopia

በተጓዥ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo nation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share