Daily Afar News

Daily Afar News ይህ ፔጅ የአፋር ህዝብን ታሪክ፣ ባህል፣
ማህበራዊና ፖለቲካ የሚዳስስ የእርሶ ገፅ ነው

እህታችንን እናሳክማት 🙏ለብዙዎች በመድረስ ለብዙዎች መታከም ፣ መዳን ፣ መሳቅና  መጥገብ ምክንያት እና ሰበብ በመሆን የምናውቃት እህታችን Fetehya Hassen አመመኝ አግዙኝ እያለችን ነ...
18/09/2024

እህታችንን እናሳክማት 🙏

ለብዙዎች በመድረስ ለብዙዎች መታከም ፣ መዳን ፣ መሳቅና መጥገብ ምክንያት እና ሰበብ በመሆን የምናውቃት እህታችን Fetehya Hassen አመመኝ አግዙኝ እያለችን ነዉ !

ህመሟ ግዜ የማይሰጥና አስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልገው በመሆኑ ለዚህም መታከሚያ ከ 1.5 ሚሊየን በላይ ስለተጠየቀች በምንችለው አቅም እንርዳት አናግዛት እላለሁ 🙏 50 ሎሚ ለአንድ ሰዉ ሸክሙ ለ50 ሰዉ ጌጡ አይደል ሚባለዉ.....!🥹

Ethiopia ንግድ ባንክ 1000640155055
huseen Qabudu macammad

Saudi bank = SA8310000083500002351206 FETEHYA HASSEN

ልት ደፈር የነበረች ህፃን በጩኸት ራሷን አድናለች!ቦሌ ቡልቡላ አንዲት የ 5 አመት ህፃን ሰፈር ውስጥ ለመጫወት ከቤት እንደወጣች ለረጅም ሰአት ድምፅዋ ሲጠፋ አክስቷ እሷን ለመፈለግ ከቤት ት...
20/08/2024

ልት ደፈር የነበረች ህፃን በጩኸት ራሷን አድናለች!

ቦሌ ቡልቡላ አንዲት የ 5 አመት ህፃን ሰፈር ውስጥ ለመጫወት ከቤት እንደወጣች ለረጅም ሰአት ድምፅዋ ሲጠፋ አክስቷ እሷን ለመፈለግ ከቤት ትወጣለች፡፡ፈልጋ ስታጣት አንድ በእዴሜ ገፋ ያለ የጥበቃ ሰራተኛ እሱጋ ሄዳ ስታንኳኳ አልከፍትም ይላታል፡፡

ከውስጥ የልጅቷን ድምፅ ስትሰማ ሰፈሩን በጩኧት ቅልጥ ታረገዋለች፡፡ የሰፈሩ ሰው ተሰብስቦ በሩን ሰብረው ውስጥ ሲገቡ ህፃኗ ልጅ አልጋ ላይ ተኝታለች፡፡ ሰውዬው ደሞ ሱሪውን አውልቆ ቆሞ ተገኘ፡፡ በአከባቢው የነበሩ ፖሊሶች ሰውዬውን በባጃጅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት ሄደዋል፡፡ ልጅቷን ደግሞ ሆስፒታል ቼክ ለማስደረግ ይዘዋት ሄዱ።ይህ አዲስ አበባ ዛሬ የተፈፀመ ነው‼

በህጻን ሄቨን ላይ የተፈጸመውን ዘግ*ናኝና ኢ-ሰብአዊ ወንጀል በፅኑ እናወግዛለን! በሀገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በህፃናትና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ዘግ*ናኝና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ቀጥለዋል፡፡ ...
19/08/2024

በህጻን ሄቨን ላይ የተፈጸመውን ዘግ*ናኝና ኢ-ሰብአዊ ወንጀል በፅኑ እናወግዛለን!

በሀገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በህፃናትና በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ዘግ*ናኝና ኢሰብአዊ ድርጊቶች ቀጥለዋል፡፡

ከእነዚህ መካከል ሰሞኑን በህዝባችን ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰው የህፃን ሄቨን ዘግ*ናኝና ኢሰብአዊ ወንጀልም ይጠቀሳል፡፡

ዓባይ ቴሌቪዥን በአሰ*ቃቂ ሁኔታ በተገደለችው ህፃን ሄቨን የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ይህንን መሰል የህፃናትና ሴቶች ጥ ቃ ት በፅኑ ያወግዛል።

Via ዓባይ TV

Justice for Heaven

  ኢትዮጵያውያን ተመልከቱ እቺ ምስኪን እናት የህክምና ባለሙያ ናት፣ ልጇን በ ግ ፍ ያጣች ሴት ነች ፣ ልጇን የነጠቋት ሰዎች በሙያዋ እንዳትሰራ እስከ ማድረግ ድረስ አድርገዋታል።       ...
19/08/2024

ኢትዮጵያውያን ተመልከቱ
እቺ ምስኪን እናት የህክምና ባለሙያ ናት፣ ልጇን በ ግ ፍ ያጣች ሴት ነች ፣ ልጇን የነጠቋት ሰዎች
በሙያዋ እንዳትሰራ እስከ ማድረግ ድረስ አድርገዋታል።
እቺ እናት ፍትህ ትሻለች....

#ፍትህ #ሼር

በዚሁ አጋጣሚ ፍትህ መጠየቁ እንዳለ ሆኖ ይችን የተበደለች እናት ለቀሪ ልጇ ትቆም ዘንድ መርዳት እንዳይረሳ
♦️ አይዞሽ አለንልሽ እንበላት በአካውንቷ የቻልነውን እናስገባላት።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000177318934
አበቅ የለሽ አደባ

ስልኳ :- 0942707163
አበቅ የለሽ አደባ

— ሞ*ት ለአስገድዶ ደፋሪ —ከታች ምስሏ የተለጠፈችው ሴት ማሪያን ባክማየር (Marianne Bachmeier) ትባላለች። የሰባት ዓመት ሴት ልጅ ነበራት። ይህቺን ልጅ ክላውስ ግራቦውስኪ ( K...
18/08/2024

— ሞ*ት ለአስገድዶ ደፋሪ —

ከታች ምስሏ የተለጠፈችው ሴት ማሪያን ባክማየር (Marianne Bachmeier) ትባላለች። የሰባት ዓመት ሴት ልጅ ነበራት። ይህቺን ልጅ ክላውስ ግራቦውስኪ ( Klaus Grabowski ) የተባለ ጎረቤቷ ይደፍራትና ይገድ*ላታል። ግራቦውስኪ የለመደ ደፋሪ (s e x offender) ነው። ይህን ከማድረጉ አስቀድሞም ኹለት ሴቶችን በመድፈር ተጠርጥሮ በተዳከመ የፍትሕ ሥርዓት ምክንያት ተገቢውን ቅጣት ሳይቀበል ሊለቀቅ ችሏል። —ባይለቀቅ ምናልባት የባክማየርንም ልጅ ባልደፈረ ነበር።

ግራቦውስኪ ተይዞ ፍርድ ቤት ቀረበ። የፍርድ ሒደቱ በሚካሄድበት በሦስተኛው ቀን ግን ባክማየር በድብቅ ሽጉጥ ይዛ በመግባት ሰባት ጊዜ ግራቦውስኪ ወደተቀመጠበት አቅጣጫ አከታትላ ትተኩሳለች። (ነገሩን ፖየቲክ ሊያደርጉት ሲፈልጉ እያንዳንዱ ጥ ይ ት ለእያንዳንዱ የልጇ ዕድሜ ይላሉ።) ከተኮሰችው ውስጥ ስድስቱ ታላሚው ላይ አርፈው እዚያው ፀጥ አለ —የታ*ባቱ። ባክማየርም ያለምንም ማንገራገር እጇን ሰጠች።

ፍርድ ሁሉ ፍትሕ አይደለም። የተበዳዮችን አንጀት የማያደርስ፣ ካቀረቀሩበት ቀና የማያደርግ፣ ዕምባ የማያብስ የፍትሕ ሥርዓት የወንጀለኛ ልብ ያላቸውን ግለሰቦች የልብ ልብ ይሰጣቸዋል። ቁርጠኝነት የሌለው፣ ልፍስፍስ የወንጀለኛ መቅጫ «ብታሠርም ጥቂት ዓመት ነው፤ ምን አላት?» የሚሉ አስገድዶ ደፋሪ*ዎችን የሚያፈራ መደላድል ይሆናል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እሥር ቤትን ቤታቸው ያደረጉ፣ መታሰር ብርቃቸው ያልሆኑ ዱርዬ*ዎችና ባለጌ*ዎች የሚፈጠሩት በዚህ ሒደት ነው።

በተለይም ራሳቸውን በምንም መንገድ መከላከል የማችሉ፣ ሕመማቸውን በቅጡ መናገር የማይችሉ ሕፃናትንም ኾነ ሴቶችን አሳድደው፣ አልመውና አቅደው ለዕድሜ ልክ ጾታዊ፣ አካላዊና ሥነ ልቡናዊ ቁስል የሚዳርጉ ሰዎች አንድ ተጨማሪ ቀን በምድር ላይ የሰላምን አየር ሊምጉ አይገባቸውም። ተበዳዮች በኀፍረትና በመሸማቀቅ አቀርቅረው፣ ወንጀለኞች በድፍረትና በልበ ሙሉነት ቀና ቀና የሚሉባት ሀገር ለማንም አትበጅም። ነገ በእያንዳንዳችን ቤት ባሉ ሕፃናትና ሴቶች በደሉ ይደርሳል። ስለዚህም እንደ ወንጀሉ አሰቃቂነት ሁሉ፣ የፍርድ ብይን ዜናውም ምሕ*ረትን የማያውቅ፣ ለቀጣይ ወንጀል እየተዘጋጁና አድብተው ቀን እየጠበቁ ያሉ ነውረኛ ግለሰቦችን ጆሮ ጭው የሚያደርግ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ የ ሞ*ት ፍርድ መሆን አለበት።

ወንጀለኛው ይግባኝ ጠይቆ ፍርድ ቤትም ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶል እንግዲህ በዚህ ቀን በመላ ኢትዮጵያን የሚኖር ከ ፍትህ ጎን የሚቆም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ባህርዳር ከተማን ያጥ...
18/08/2024

ወንጀለኛው ይግባኝ ጠይቆ ፍርድ ቤትም ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶል

እንግዲህ በዚህ ቀን በመላ ኢትዮጵያን የሚኖር ከ ፍትህ ጎን የሚቆም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ባህርዳር ከተማን ያጥለቀልቃል

የሄቭን እናት እንደበደለኛ ሳይሆን እንደተከሳሽ አንገቱዋን በደፋችበት ከተማ ኢትዮጵያውያን አለንልሽ ከጎንሽ በሚል ከጎኖ የሚቆሙበት ቀን እየመጣ ነው

እንግዲህ አለንልሽ ያለ በሙሉ ከጥቅምት 20 በፊት ባህርዳር ከቶ ሊጠብቅ ይገባል

የባህርዳር ህዝብ ጥቅምት 20 በመላ ከተማው ስራ ዘግቶ ፍትህ በባህርዳር ፍርድ ቤት ተገኝቶ መጠየቅ አለበት

ዘመድ አለኝ ወገን አለኝ እያለ ሲኩራራ የነበረው ደፋሪ እራቁቱን በማስቀረት በወንጀሉ በማዘን የሞ*ት ፍርድ ፍረዱብኝ በራሱ እንዲል እና በጸጸት እንዲ*ሰቃይ መሆን አለበት

ወንጀለኛው ጌትነት ከማረሚያ ቤት አምልጦ ነበር ………...............መግለጫ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር  በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድ...
18/08/2024

ወንጀለኛው ጌትነት ከማረሚያ ቤት አምልጦ ነበር

………...............

መግለጫ

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድጋሜ ይገልጿል::

ከተማ አስተዳደሩ *ሀምሌ 25 / 2015 ዓ.ም* በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ በ7 አመቷ ታዳጊ ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት በእጅጉ ማዘኑን ገልፆ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

በህጻናት ላይ የሚፈጸምን ማንኛውም ጥቃት መከላከል በዋነኛነት የመንግስት ሃላፊነት ሲሆን በሌላ በኩል የሁሉም አካል ተመሳሳይ ድርሻ ያለው መሆኑን የገለፀው ከተማ አስተዳደሩ እንደዚህ አይነት አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት በከተማችን በመፈፀሙ በእጅጉ ዛሬም በድጋሜ አዝነናል ።

የባሕር ዳር ከተማ ህዝብ ሰው ወዳድ፣ ሁሉን አክባሪ፣ ባህሉን፣ ወጉንና ታሪኩን ጠባቂ አስተዋይ ጨዋ ህዝብ ነው ። በዚህ እሴትና ባህል በተገነባ ማህበረሰብ ውስጥ የተፈፀመው ድርጊት በፍፁም ነውረኛና የከተማውን ህዝብ የማይገልፅ ሁሉም ሰው ሊያወግዘው የሚገባ ዘግናኝ ተግባር ነው ።

ሁሉም እንደሚያስታዉስዉ ወንጀሉ እንደተፈፀመ የከተማ አስተዳደሩ የሚመለታቸው ተቋማት በዋነኝነትም ከፖሊስ ፣ ከጤና ተቋም ፣ ከፍትህ እንዲሁም ከተበዳይ ወገኖች ጋር በመቀናጀት ጉዳዩ በህግ እንዲያዝ በማድረግ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ተይዞ በ20/06/2016 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት የ25 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ባህርዳር ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።

በዚህ አጋጣሚ ከተማ አስተዳደሩ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ነፃነት የሚያከብር ቢሆንም ከተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትና የማህበረሰቡን ሞራልና ክብር ዝቅ ያደረገ ወጀል በፈፀመው ወንጀለኛ ላይ የተሰጠው ፍርድ አስተማሪነት የሚያንሰው መሆኑን አስተዳደሩ በፅኑ ያምናል ።

ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን በጥብቅ ለመከታተል ባለው ፅኑ አቋም ክልሉን ባጋጠመው ቀውስ ወንጀለኛው ከማረሚያ ቤት አምልጦ የወጣ መሆኑን እንዳወቀ በልዩ ሁኔታ የፀጥታ ሀይሉ ክትትል እንዲያደርግ አመራር ተሰጦ ወንጀለኛው ተይዞ ድጋሜ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ወንጀለኛው ይግባኝ የጠየቀ እንደሆነ እና ጉዳዩ ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ቀጠሮ የሰጠ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ያውቃል። የፍርድ ቤቱን ነጻነት በጠበቀ መልኩ ከህግ አኳያ የይግባኙን ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት የምንከታተለው እና ፍትህ እንዲረጋገጥ በፅናት የምንታገል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ከተማ አስተዳደሩ በልጃችን ህፃን ሄቨን ለደረሰው ግፍ ፍትህ ሲጠይቅ ፣ ለጉዳዩ ለሰጠው ትኩረት እና እያደረገ ላለው ትግል ለመላው የህብረተሰብ ክፍል ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ለፍትህ መረጋገጥ ለምናደርገው ትግል ህ/ሰቡ ከጎናችን እንዳይለይ ጥሪያችን እያቀረብን በቀጣይም የህፃናት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል።

ነሐሴ 12/2016ዓ.ም
ባሕር ዳር .

በዚሁ አጋጣሚ ፍትህ መጠየቁ እንዳለ ሆኖ ይችን የተበደለች እናት ለቀሪ ልጇ ትቆም ዘንድ መርዳት እንዳይረሳ ♦️ አይዞሽ አለንልሽ እንበላት በአካውንቷ የቻልነውን እናስገባላት።የኢትዮጵያ ንግድ...
18/08/2024

በዚሁ አጋጣሚ ፍትህ መጠየቁ እንዳለ ሆኖ ይችን የተበደለች እናት ለቀሪ ልጇ ትቆም ዘንድ መርዳት እንዳይረሳ
♦️ አይዞሽ አለንልሽ እንበላት በአካውንቷ የቻልነውን እናስገባላት።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000177318934
አበቅ የለሽ አደባ

ስልኳ :- 0942707163
አበቅ የለሽ አደባ

♦️ ፓስቱን ፊስቡክ ላይ እንዲሸራሸር #ሼር በማድረግ ተባበሯት አይዞሽ አለን ከጎንሽ ነን እንበላት::

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊቃወም የሚገባ ጉዳይ ነው..!!!ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገራችን ማዕዘን መስራት መለወጥ ይችላል።የሶማሌ ክልል ይቅርታ መጠየቅ አለበት።
27/07/2024

ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊቃወም የሚገባ ጉዳይ ነው..!!!

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገራችን ማዕዘን መስራት መለወጥ ይችላል።የሶማሌ ክልል ይቅርታ መጠየቅ አለበት።

"ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ጌትነት ሰምዖን ይባላል።የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ባልደረባ ነው።የካሜራ ባለሙያው ጌትነት ጎፋ የተከሰተውን አሰቃቂ የተፈጥሮ አደጋ ሲቀርፅ የእሱ ሁኔታ በሌላ ካሜራ...
25/07/2024

"ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ጌትነት ሰምዖን ይባላል።የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ባልደረባ ነው።የካሜራ ባለሙያው ጌትነት ጎፋ የተከሰተውን አሰቃቂ የተፈጥሮ አደጋ ሲቀርፅ የእሱ ሁኔታ በሌላ ካሜራ ተይዞ ነበር።ሰብዓዊነት የሁሉም ሙያዎች ገዥ ነው።"
~ Abel Birhanu

ውሃን በቀን ውስጥ በተወሰኑ ጊዜያት መጠጣት ለጤና እና ለደህንነት ያለውን ጥቅም ይጨምረዋል። ውሃ ለመጠጣት ተመራጭ ጊዜ እና ጠቀሜታው፡-1. ጠዋት ከእንቅልፍ ከተነቃ በኋላ፡-   - ጥቅም፡ ...
25/07/2024

ውሃን በቀን ውስጥ በተወሰኑ ጊዜያት መጠጣት ለጤና እና ለደህንነት ያለውን ጥቅም ይጨምረዋል። ውሃ ለመጠጣት ተመራጭ ጊዜ እና ጠቀሜታው፡-

1. ጠዋት ከእንቅልፍ ከተነቃ በኋላ፡-
- ጥቅም፡ በመጀመሪያ ጠዋት ውሃ መጠጣት ሜታቦሊዝምን ለመጀመር፣ ከሰዓታት እንቅልፍ በኋላ ሰውነታችንን ለማጠጣት እና በአንድ ጀምበር የተከማቹ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ይረዳል።

2. ከምግብ በፊት:
- ጥቅም፡- ከምግብ በፊት ውሃ መጠጣት ጨጓራውን ለምግብነት በማዘጋጀት ለምግብ መፈጨት ይረዳል። እንዲሁም የሙሉነት ስሜት እንዲሰማዎት ሊረዳዎት ይችላል፣ ይህም የካሎሪ ቅበላን ሊቀንስ እና ክብደትን ለመቆጣጠር ይረዳል።

3. በምግብ ጊዜ፡-
- ጥቅም፡- በምግብ ወቅት ውሃ መጠጣት ለምግብ መፈጨት እና ከመጠን በላይ መብላትን ይከላከላል። ይሁን እንጂ በአጠቃላይ በምግብ ወቅት ከመጠን በላይ ከመጠጣት መቆጠብ ይመከራል ምክንያቱም ለትክክለኛው የምግብ መፈጨት አስፈላጊ የሆኑትን የሆድ አሲዶች እና ኢንዛይሞችን ያጠፋል ።

4. *ከምግብ በኋላ:
- ጥቅም፡- ከምግብ በኋላ ውሃ መጠጣት ለምግብ መፈጨት ይረዳል እና ንጥረ ምግቦችን ለመምጠጥ ይረዳል። በተጨማሪም የላንቃን ማጽዳት ሊረዳ ይችላል.

5. ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በፊት እና በኋላ:
- ጥቅም፡- ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በፊት ውሃ ማጠጣት ሰውነትዎ በደንብ መዘጋጀቱን ያረጋግጣል እናም ድርቀትን ይከላከላል። ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ በኋላ ውሃ መጠጣት በላብ የጠፉ ፈሳሾችን ይሞላል እና ለማገገም ይረዳል።

6. ከመተኛት በፊት፡ከ
- ጥቅም፡- ከመተኛቱ በፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ መኖሩ በአንድ ሌሊት የእርጥበት መጠንን ለመጠበቅ ይረዳል። ይሁን እንጂ ወደ መጸዳጃ ቤት አዘውትሮ ላለመሄድ ትንሽ መጠን ብቻ መጠጣት ጥሩ ነው, ይህም እንቅልፍን ሊያስተጓጉል ይችላል.

7. የድካም ስሜት ሲሰማ፡-
- ጥቅም፡- ድካም አንዳንድ ጊዜ የሰውነት ድርቀት ምልክት ሊሆን ይችላል። የመጠጥ ውሃ የኃይል ደረጃን ለመጨመር እና ትኩረትን ለማሻሻል ይረዳል.

8. በህመም ጊዜ፡
- ጥቅም፡- በሚታመምበት ጊዜ በተለይም ትኩሳት፣ትውከት ወይም ተቅማጥ ሲኖርዎ እርጥለበትን ማቆየት በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም እነዚህ ሁኔታዎች ወደ ድርቀት ስለሚመሩ።

የሰውነትዎን ጥማት ምልክቶች ማዳመጥ እና እንደ አስፈላጊነቱ ቀኑን ሙሉ ውሃ መጠጣት ጥሩ ውሃ እንዲኖርዎት ቁልፍ ነው።

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ ህወሓትን አስጠነቀቁ!!!👉
24/07/2024

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ ህወሓትን አስጠነቀቁ!!!

👉

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily Afar News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category