Adil Media አዲል ሚዲያ

Adil Media   አዲል ሚዲያ "በኢስላም ፍፁም ሰላም...'

ኢንና ሊላሂ ወኢንና ዒለይሂ ራጂዑን… የወግዲው ደብሪቱ ሐሪማ ባለቤት ታላቁ ሸይኽ ሚስባህ በማረፋቸው የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ቀብራቸውን ኑር፤ ማረፊያቸው...
16/03/2024

ኢንና ሊላሂ ወኢንና ዒለይሂ ራጂዑን… የወግዲው ደብሪቱ ሐሪማ ባለቤት ታላቁ ሸይኽ ሚስባህ በማረፋቸው የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለፅን አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ቀብራቸውን ኑር፤ ማረፊያቸውን ፊርደውስ እንዲያደርግልን እንማፀነዋለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለታላቁ ሸይኽ ሚስባህ የዒልም ተማሪዎች፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንደዚሁም ለመላው ሙስሊሞች መፅናናትን እንመኛለን፡፡

 #ሞተ የFoX Sport ጋዜጠኛ አሜሪካዊው በቅርብ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ አርማ ያለበት ቲሽርት ለብሼ ስታዲየም ውስጥ ካልገባው ብሎ ሲቀውጠው የነበረው ነገር ግን በኳታር ፖሊሶች አይ ይሄንማ...
10/12/2022

#ሞተ

የFoX Sport ጋዜጠኛ አሜሪካዊው በቅርብ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ አርማ ያለበት ቲሽርት ለብሼ ስታዲየም ውስጥ ካልገባው ብሎ ሲቀውጠው የነበረው

ነገር ግን በኳታር ፖሊሶች አይ ይሄንማ ለብሰህ አትገባም ብለው ከልክለው ከስታዲዮሙ ያባረሩት

ትላንትና እዛው ኳታር በስታዲዮም ውስጥ በስራ ላይ ወድቆ ከዚህ ዓለም ተሰናበተ።

ምንጭ ጉርሻ

Croatia congratulations ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካዊው ስም ጥር ቦክሰኛ ማይክ ታይሰንና ፍልስጤማዊ-አሜሬካዊው የሙዚቃ ፕሮዱሰር እና የሙዚቃ ማቀናበሪያ ኩባንያ ባለቤት DJ K...
09/12/2022

Croatia congratulations

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሜሪካዊው ስም ጥር ቦክሰኛ ማይክ ታይሰንና ፍልስጤማዊ-አሜሬካዊው የሙዚቃ ፕሮዱሰር እና የሙዚቃ ማቀናበሪያ ኩባንያ ባለቤት DJ Khaled (ኻልድ ሙሐመድ ኻልድ) መካ ውስጥ ኡምራ ሲያደርጉ ታይተዋል። የቀድሞው ሙዚቀኛ (ራፐር) Mutah "Napoleon" Beale እንደዘገበው።

በአዲስ አበባ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በገደለችው ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት ተወሰነ****************** በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ አካባቢ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ...
05/12/2022

በአዲስ አበባ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በገደለችው ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት ተወሰነ
******************

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አራብሳ አካባቢ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ በገደለችው ግለሰብ ላይ ፍርድ ቤቱ በሞት ቅጣት እንድትቀጣ ውሳኔ አሳለፈ።

ፍርዱ የተሰጠው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ከባድ ግድያ እና የውንብድና ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ባዋለው ችሎት መሆኑን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

የጃፓናውያን ጨዋነት!!ጃፓናውያን በብዙ ነገር ለአለም ሕዝብ ምሳሌ እንደሆኑ ይነገራል። በስልጣኔ፣ ቴክኖሎጂ ወዘተ። ከዚህ በዘለለም የጃፓን ሕዝብ ፍጹም ጨዋና ምስጉን ስነምግባር ያለው መሆኑን...
23/11/2022

የጃፓናውያን ጨዋነት!!

ጃፓናውያን በብዙ ነገር ለአለም ሕዝብ ምሳሌ እንደሆኑ ይነገራል። በስልጣኔ፣ ቴክኖሎጂ ወዘተ።

ከዚህ በዘለለም የጃፓን ሕዝብ ፍጹም ጨዋና ምስጉን ስነምግባር ያለው መሆኑን ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ደርሰው የተመለሱ ሰዎች ሲናገሩ ይሰማል።

ጃፓናውያን ባለፈው 2018 የሩሲያ አለም ዋንጫ ወቅት ጨዋታዎችን ተከታትለው ሲጨርሱ ስቴድየም ውስጥ የተጠቀሙትን ቆሻሻ አጽድተው መውጣታቸው አነጋጋሪ ነበር።

ዛሬም ጃፓናውያን ይህን ጨዋነታቸውን በከሊፋ ኢንተርናሽናል ስቴድየም ደግመው አሳይተዋል።

አስገራሚው ነገር ጃፓን በዛሬው ጨዋታ ጀርመንን ባልተጠበቀ ሁኔታ 2ለ1 አሸንፋ ደጋፊዎቿ በትልቅ የደስታ ስሜት ውስጥ እንኳን ሆነው ከጨዋታው በኋላ ይህን የጨዋነት ተግባራቸውን ዘንግተው ወደ ፈንጠዝያ ከመሄድ ይልቅ የተለመደውን የማጽዳት ስራ መቀጠላቸው ነው።

ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን ማሸናፏን ምክኒያት በማድረግ ነገ እሮብ ስራ እና ትምህርት ዝግ መሆኑን አውጃለች ነገ እሮብ ለሁሉም ሳኡዲ ውስጥ ለሚኖሩ ሰራተኞች ሳኡዲ በእግር ኳስ ያስመዘገብችውን...
22/11/2022

ሳዑዲ አረቢያ አርጀንቲናን ማሸናፏን ምክኒያት በማድረግ ነገ እሮብ ስራ እና ትምህርት ዝግ መሆኑን አውጃለች
ነገ እሮብ ለሁሉም ሳኡዲ ውስጥ ለሚኖሩ ሰራተኞች ሳኡዲ በእግር ኳስ ያስመዘገብችውን ድል በማስመልከት የሳኡዲው ንጉስ ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱል አዚዝ የእረፍት እና የደስታ ቀን ነው ብሔራዊ በዓል እንዲሆን ሲሉ አውጀዋል :: ትምህርት ቤት እንዲሁም ማንኛውም የግል እና የመንግስት ሰራተኞች ዝግ እንደ ሚሆን ገልፀዋል::

የኳታር ዓለም ዋንጫ ድምቀት የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ የኳታር ዜጋ፣ Caudal Regression Syndrome (CDS) በተባለ ች...
20/11/2022

የኳታር ዓለም ዋንጫ ድምቀት የሆነው ጋኒም አል-ሙፍታህ

ጋኒም አል-ሙፍታህ ይባላል፤ የ20 ዓመት ዕድሜ ያለው ይህ የኳታር ዜጋ፣ Caudal Regression Syndrome (CDS) በተባለ ችግር ምክንያት ከወገብ በታች አካል የለውም።

እናቱ ከመወለዱ በፊት ልጇ ችግሩ እንዳለበት ተነግሯት በበርካቶች "ልጅሽን አስወርጂ" በሚል ብትመከርም፣ እናት ግን ጋኒምን ወልዳ ችግሩን አብራ መጋፈጥን መርጣለች።

ከአባቱ ጋር በመሆንም "ልጃችን ከወገቡ በታች አካል ባይኖረውም አንዳችን ቀኝ እግር፣ ሌላችን ግራ እግር እንሆንለታለን” ሲሉ ቃል በመግባት የዓለምን ፈተና አብረውት ለመታገል ቆረጡ።

የሚጋባ ፈገግታ የተቸረው ጋኒም በማኅበራዊ ሚዲያው ለሚሊዮኖች ንቃትን የሚፈጥር ወጣት ሆኗል።

ቀድሞ በጓደኞቹ ማንጓጠጥ ሊያቋርጠው የነበረውን ትምህርት ቀጥሎም በፖለቲካል ሳይንስ ዲግሪውን ለማግኘት እየተማረ ይገኛል።

ዛሬ ደግሞ የ2022ቱ የኳታር የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ድምቀት ሆኖ አሳልፏል።

22ኛውን የዓለም ዋንጫ እያስተናገደች የምትገኘው ቀጠር ጅምሩን በአሏህ(ሰ.ወ) ቃል ቁርኣን በማድረግ አል-በይት ስታዲየም አሸብርቋል::

«እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ ከእናንተ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡»

(ቁርኣን 49:13)

‎{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقۡنَـٰكُم مِّن ذَكَرࣲ وَأُنثَىٰ وَجَعَلۡنَـٰكُمۡ شُعُوبࣰا
‎وَقَبَاۤىِٕلَ لِتَعَارَفُوۤا۟ۚ إِنَّ أَكۡرَمَكُمۡ عِندَ ٱللَّهِ أَتۡقَىٰكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِیمٌ خَبِیرࣱ }
[Surah Al-Hujurât: 13]

20/11/2022

የወንድማማችነት ተጽእኖ 😍

በቴክኒክ ችግር ምክንያት ከእሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የሚንበር ቲቪ ስርጭት ችግሩ ተፈትቶ ወደ ስርጭት ተመልሷል ፡፡አልሐምዱሊላህ
10/11/2022

በቴክኒክ ችግር ምክንያት ከእሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ጀምሮ ተቋርጦ የነበረው የሚንበር ቲቪ ስርጭት ችግሩ ተፈትቶ ወደ ስርጭት ተመልሷል ፡፡

አልሐምዱሊላህ

ድሮግባ ሰልሟል ተብሎ የተወራው ውሸት ነው አልሰለመም ::ድሮግባ በትዊተር ገፁ ባሰፈረው ፅሁፉ ከሙስሊም ወንድሞቼ ጋር ሰፈሬን ጎበኘሁኝ እንጅ ሀይማኖቴን አልቀየርኩም ብሏል ። ድሮግባን አላህ...
07/11/2022

ድሮግባ ሰልሟል ተብሎ የተወራው ውሸት ነው አልሰለመም ::

ድሮግባ በትዊተር ገፁ ባሰፈረው ፅሁፉ ከሙስሊም ወንድሞቼ ጋር ሰፈሬን ጎበኘሁኝ እንጅ ሀይማኖቴን አልቀየርኩም ብሏል ።

ድሮግባን አላህ ትክክለኛውን መንገድ ይመራው ዘንድ ምኞታችን ነው ።

አልሀምዱሊላህ! ተሳክቷል!መኪና ለኡስታዝ ማን ነው የገዛው? ሲባል ፣ እከሌ የሚባል አንድ ግለሰብ ሳይሆን.. ኡማው (ሙስሊሙ ማህበረሰብ) በህብረት ነው የገዛው እንዲባል ላደረጋችሁ ሁሉ አላህ...
03/11/2022

አልሀምዱሊላህ! ተሳክቷል!
መኪና ለኡስታዝ ማን ነው የገዛው? ሲባል ፣ እከሌ የሚባል አንድ ግለሰብ ሳይሆን.. ኡማው (ሙስሊሙ ማህበረሰብ) በህብረት ነው የገዛው እንዲባል ላደረጋችሁ ሁሉ አላህ ይመንዳችሁ! ህዝቡ ምላሽ ሰጥቷል!! አንበሳችንን አኩርቷል! አልሀምዱሊላህ!!! በመጪዎቹ ቀናት ገበያ ወጥተው፣ ለጉዞ አመቺ የሆነን ይገዛሉ! በመቀጠል ለህዝብ ይፋ ይደረጋል። ለተቋም ግንባታ ርብርብ ከነገ ጀምሮ ይቀጥላል!

Ali Amin

Address

Addis Ababa

Telephone

+251922092225

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adil Media አዲል ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share