Daily News Ethiopian

  • Home
  • Daily News Ethiopian

Daily News Ethiopian news page

📌 አንግሶም ሙሉጌታ📌 ሀብቶም ገ/ፃዲቅ📌 ሰመረ አበራ📌 ኤፍሬም ታጀበ📌 አውት መብራቱ እና ሌሎች 42 ተጠርጣሪዎች...በቡድን በመደራጀት በመኪና በመንቀሳቀስ ሰዎች ብቻቸውን አልያም ሁለት ሆነ...
25/04/2025

📌 አንግሶም ሙሉጌታ
📌 ሀብቶም ገ/ፃዲቅ
📌 ሰመረ አበራ
📌 ኤፍሬም ታጀበ
📌 አውት መብራቱ
እና ሌሎች 42 ተጠርጣሪዎች...

በቡድን በመደራጀት በመኪና በመንቀሳቀስ ሰዎች ብቻቸውን አልያም ሁለት ሆነው ሲንቀሳቀሱ ከኋላ አንገታቸውን በማነቅ የግለሰቦች ንብረት ዘርፈው ሲሰወሩ የነበሩ ቡድኖች ነበሩ።

አሁን ላይ 42 ተጠርጣሪዎች ካሉበት በአዲስ አበባ ፖሊስ ተለቃቅመው ተይዟል።

በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል...
04/11/2024

በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል።

"ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው።

"ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው።

ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው።

እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው!

Subscribe አድርጉ ቤተሰብየአቡነ አብረሀምና የአብይ ፍጥጫ ገብታችሁ እዩት !ይሄን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉ ሁላችሁም❗️
16/03/2024

Subscribe አድርጉ ቤተሰብ
የአቡነ አብረሀምና የአብይ ፍጥጫ ገብታችሁ እዩት !
ይሄን ቻናል ሰብስክራይብ አድርጉ ሁላችሁም❗️

የአቡነ አብረሀም እና የአብይ ፍጥጫ

ትላንት ለመምህራን ከወጡ 435 ቤቶች ውስጥ እንዲህም አይነት ነገር ታይቷል፣ አንድ ሰው ሁለት ግዜ! በርካታ ቅሬታ አቅራቢዎች ባደረሱኝ አስተያየት የመምህራን የቤት እጣ መውጣቱ ጥሩ ሁኖ ሳለ...
16/03/2024

ትላንት ለመምህራን ከወጡ 435 ቤቶች ውስጥ እንዲህም አይነት ነገር ታይቷል፣ አንድ ሰው ሁለት ግዜ!

በርካታ ቅሬታ አቅራቢዎች ባደረሱኝ አስተያየት የመምህራን የቤት እጣ መውጣቱ ጥሩ ሁኖ ሳለ አንድ ሰው ሁለት ግዜ መቅረቡ ግርምታን ፈጥሯል፣ ይህም የገባው ዳታ የተደጋገሙ ስሞች ያሉበት ነው ብለው እንዲጠረጥሩ እንዳደረጋቸው ገልፀዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ "ይህ እንደ ኮንዶሚኒየም እጣ አወጣጥ እንኳን በሺዎች ያሉበት ዝርዝር አይደለም፣ 435 ብቻ ነው፣ እንዴት በዚች ትንሽ ቁጥር እንዲህ አይነት ድግግሞሽ ሊኖር ይችላል" ብለው ጠይቀዋል።

የሚመለከተው አካል መልስ ከሰጠበት እመለስበታለሁ።

 #መልካምአንድነት ቦታው የሃዋሳዋ ወሰንተኛ ቢሻን ጉራቻ ከተማ ነው። በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ የጥቁር ውሃ ማሪያም ህንፃ ቤተክርስቲያን አርማታ ሙሌት የሚከናወንበት ነው። እናም ምዕመኑ ከሃዋሳ፣ ...
16/03/2024

#መልካምአንድነት ቦታው የሃዋሳዋ ወሰንተኛ ቢሻን ጉራቻ ከተማ ነው።

በዛሬው ዕለተ ቅዳሜ የጥቁር ውሃ ማሪያም ህንፃ ቤተክርስቲያን አርማታ ሙሌት የሚከናወንበት ነው። እናም ምዕመኑ ከሃዋሳ፣ ከጥቁር ውሃ እና አካባቢው ተሰባስቦ ስራውን ከልቡ እያከናወነ ነው።

እናም በስራው ላይ ይህንን ተመለከትኩ። ሰው የስራ ልብስ የለበሰ በመሆኑ ሃይማኖቱ ይሄ ነው ብሎ መለየት አይቻልምና ሁሉም አንድ ሆኖ በአንድነት እየሰራ ነው። ትንሽ እረፍት ፈለኩና ከዛፍ ስር እንዳለሁ፣ ይሄው እነዚህ ስራ ላይ የነበሩ የእስልምና እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን የሶላት ሰዓት ደርሶባቸው ከህንፃ ቤተክርስቲያኑ አናት ላይ ወርደው ሲሰግዱ አገኘኋቸውና ፈቃዳቸውን ጠይቄ ፎቶ አነሳኋቸው።

የመልካም አንድነት፣ የመቻቻል ማሳያ ነው።

አየ ሰው ከስፍራው ያደረሰኝ መረጃ ነው።

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ አለአግባብ የወሰዱት ገንዘብ ካለ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ አሳስቧልትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ...
16/03/2024

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ አለአግባብ የወሰዱት ገንዘብ ካለ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ አሳስቧል

ትናንት መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከኢትዮጰያ ንግድ ባንከ ኤ.ቲ.ኤም ማሽን የሌላቸውን ገንዘብ ወጪ ያደረጉ የተቋሙ ተማሪዎች በፍጥነት በቅሊንጦ ቅርንጫፍ በመቅረብ እንዲመልሱ አሳስቧል።

ወጪ ያደረገውን ገንዘብ የማደመልስ ተማሪ ላይ ዩኒቨርሲቲው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድና ተማሪዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በተመሳሳይ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከትክክለኛ ሒሳባቸው ውጪ ገንዘብ ወጪ ያደረጉ ተማሪዎች የራሳቸው ያለሆነውን ገንዘብ በአስቸኳይ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትኛውም ቅርንጫፍ በመሔድ ተመላሽ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስቧል።

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ …የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ መዘጋት የከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደሩ ተገለጸከአዲስ አበባ በደብረ ብርሃን መንገድ በኩል ወደ ደሴ የሚደረገው የየብስ ትራንስ...
16/03/2024

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ …

የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ መዘጋት የከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ

ከአዲስ አበባ በደብረ ብርሃን መንገድ በኩል ወደ ደሴ የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት መቋረጡ ለከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ዳርጎናል፤ ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ፥ ሕክምና ለማግኘት ተቸግረናል፤ የሸቀጥ ዋጋ ከዕጥፍ በላይ ጨምሯል፤ አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ወደ ገበያ ለማቅረብ አልቻለም፤ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰንበቴ ከተማ አካባቢ፣ ሕክምና መውሰድ የነበረባቸው አምስት እናቶች መንገዱ ስለተዘጋ በወሊድ ምክንያት እንደሞቱ፣ የከተማው ጤና ጣቢያ አመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ከአጣዬ ከተማ አካባቢ፣ ለተሻለ ሕክምና በሌላ መንገድ በመወሰድ ላይ የነበረ አንድ ሕፃን፣ ወደ ሕክምና ተቋም ሳይደርስ ሕይወቱ እንዳለፈ፣ አንድ የጤና ባለሞያ ጠቁመዋል፡፡

ሌላው የአጣዬ ከተማ ነዋሪም፣ ቀደም ሲል ከተማዋ ከ10 ለማያንስ ጊዜ ቃጠሎ እንደተፈጸመባት አውስተው፣ ከዚያ ጥፋት ሳታገግም ለሌላ ጉዳት ተዳርጋለች፤ ብለዋል፡፡

የሁለቱ ሃይማኖቶች አጽዋማት እየተፈጸሙ ባለበት ወቅት መንገዱ መዘጋቱ ደግሞ፣ የሸቀጥ አቅርቦት እጥረቱ እንዲባባስ ማድረጉን፣ አስተያየት ሰጭዎቹ አስረድተዋል፡፡
Via:VOA

አዲስ አበባ‼️             ነገ መጋቢት 8  በአዲስ አበባ ከተማ  በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ  የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክር...
16/03/2024

አዲስ አበባ‼️

ነገ መጋቢት 8 በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ከሰዓት በሗላ ከቀኑ 7፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጲያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የፀሎት መርሐ-ግብር ስለሚያከናውኑ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት:—

✔ ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ኡራኤል አደባባይ ላይ

✔ ከቦሌ ጌቱ ኮሜርሻል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ኦሎምፒያ አደባባይ በታች እና በላይ እንዲሁም ግራና ቀኝ

✔የቀድሞው አራተኛ ክፍለጦር (ጥላሁን አደባባይ ላይ )

✔ ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለሚጓዙ ለገሀር መብራት ላይ

✔ ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

✔ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

👉መንገዶቹ ከጠዋቱ 4፡ 00 ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡

👉አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ፕሮግራሙ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡

ገብታችሁ እዩት 👀👀🤔 እየገባችሁ ሰብስክራይብም አድርጉ 1 ሺህ መሙላት አለበት !
15/03/2024

ገብታችሁ እዩት 👀👀🤔 እየገባችሁ ሰብስክራይብም አድርጉ 1 ሺህ መሙላት አለበት !

ፍቅርሲዝም ምንድነው የሚለው ትግራይ ?

ዘመድኩን በቀለ  በቀጥታ
13/03/2024

ዘመድኩን በቀለ በቀጥታ

ዘመድኩን በቀለ በ TikTok live አሁን

17/02/2024

በዝግ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ስለ ወደብ ጉዳይ ያረገው የተቀነጨበች ንግግር ።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/Daily_News_Ethiopian

ህዳር 30/2016 በአዲስ አበባ ሰልፍ መጠራቱ ይታወሳል።እንዳለኝ መረጃ ከሆነ ማለት የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው።ያልገባችሁ ጉዳዩን በክፋት ልትወስዱት ብትችሉም፣ሠርቶ አደር የሆናችሁ በ...
05/12/2023

ህዳር 30/2016 በአዲስ አበባ ሰልፍ መጠራቱ ይታወሳል።እንዳለኝ መረጃ ከሆነ ማለት የምፈልገው አንድ ነገር ብቻ ነው።ያልገባችሁ ጉዳዩን በክፋት ልትወስዱት ብትችሉም፣ሠርቶ አደር የሆናችሁ በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ አትውጡ።ወንድማዊ ምክር ነው።ለምን? ካላችሁኝ ዛሬ ምሽት ጀምሮ በየሰፈራችሁ፣በየቤታችሁ የሚደረገውን ስታዩት ትረዳላችሁ።🙏🙏ቅር ለተሰኘ ይቅርታ።

ሼር ይደረግ❗️

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 🇪🇹ኢትዮጵያ አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 አስተያየትና መልክት ካሎት ምርትና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከ....

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily News Ethiopian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share