Prophet Misganu Milkias

  • Home
  • Prophet Misganu Milkias

Prophet Misganu Milkias Servant of God's kingdom in Christ Promote International Church
https://youtube.com/?si=sXP

 #በአዲስአበባ እና #አካባቢዋ የምትኖሩ ሁሉ  #ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈራንስ  #ተዘጋጅቷል ሁላቹህም ተጋብዛችኃል #  #👉 በእለቱ ወንጌል በሀይል ይሰበካል 👉ጌታን በዝማሬ እናመልካለን 👉  ለ...
23/07/2025

#በአዲስአበባ እና #አካባቢዋ የምትኖሩ ሁሉ #ታላቅ መንፈሳዊ ኮንፈራንስ #ተዘጋጅቷል ሁላቹህም ተጋብዛችኃል # #👉 በእለቱ ወንጌል በሀይል ይሰበካል 👉ጌታን በዝማሬ እናመልካለን 👉 ለበሽተኛ ይፀለያል #።🦅🇪🇷🦅🇪🇹🦅፡፡፡

09/07/2025
ዛሬም ተመርቋል! እንኳን ደስ አለህ ኤፍሬም በለጠ! 🎉   ከሦስት ዓመት በፊት እናቱን በክብር በእንጨት ተሸክሞ በማስደመም፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመላው ኢትዮ...
01/07/2025

ዛሬም ተመርቋል! እንኳን ደስ አለህ ኤፍሬም በለጠ! 🎉

ከሦስት ዓመት በፊት እናቱን በክብር በእንጨት ተሸክሞ በማስደመም፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመላው ኢትዮጵያን ልብ የነካው ቀን ትዝ ይላችኋል? ያኔ እናቱን በክብር በማሰብ ያሳየው ፍቅር እና መልካምነት ለሁላችንም ትልቅ ትምህርት ነበር።

ዛሬም፣ ጀግናው ኤፍሬም በለጠ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ School of Commerce በ2025 ተመርቋል!

ዛሬም እንደ ትናንቱ ሁሉ፣ የእናቱን ውለታና ፍቅር ባለመዘንጋት የሀገር ልብስ አልብሶ ከእርሷ ጋር መታየቱ ምን ያህል ትልቅ ሰው እንደሆነ ያሳያል። ትምህርት የማያልቅ የህይወት ጉዞ መሆኑን በተግባር ያሳየኸን ጀግናችን እንኳን ደስ አለህ!

ይህ ለእኛ ለሁላችንም ትልቅ ተነሳሽነት ነው፤ ፍቅር፣ ትጋትና ትምህርት የህይወት መሰረት መሆናቸውን ኤፍሬም በተግባር አሳይቶናል።

በወቅቱ ክብርት ከንቲባዋ ለእናቱ ኮንዶሚኒየም መሸለማቸውም አይዘነጋም።
መልካም የህይወት ጉዞ እንመኛለን!

Congratulations ኤፍሬም በለጠ 👏😮

'' እግዚአብሔር ይመሰገን !!“ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።”  — ሐዋርያት 5፥14
30/06/2025

'' እግዚአብሔር ይመሰገን !!
“ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።”
— ሐዋርያት 5፥14

27/06/2025

ከይድነቃቸው ጋር

👉   ዘመኑን ዋጁ !!በዘመነ ጭላጭ፥ በእንጥፍጣፊ፥ እንዳለን ሁሉ ያሳያል። የምርም የጌታችን ኮቴ በደጅ ነው፤ ቃሉን ለሚመረምሩ ግልጽ መልእክት አለው። ሲመጣ ስንተጋ ያግኘን። ክብር ለእርሱ ...
23/06/2025

👉 ዘመኑን ዋጁ !!
በዘመነ ጭላጭ፥ በእንጥፍጣፊ፥ እንዳለን ሁሉ ያሳያል። የምርም የጌታችን ኮቴ በደጅ ነው፤ ቃሉን ለሚመረምሩ ግልጽ መልእክት አለው። ሲመጣ ስንተጋ ያግኘን። ክብር ለእርሱ ሰላም ለእኛ ይሁን።

🙏❤🙏 እንሰባሰብ፥ እንመካከር!!🙏❤🙏

“በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።” ዕብ 10፥25

🤔 እንደ ልማድም ቢሆን አንድ ቀን ከልምምድ ውጭ የሆነ ነገር ለመሰብሰባችን፥ ምክንያት የሆነው አምላክ ይሰራል።
🤗 መሰባሰባችንን አንተው።
🤗 እርስበርሳችን እንመካከር።
🤗 አንበታተን ይህንን ከቀድሞ ይልቅ እናድርግ።

🤔በብዙዎቻችን ዘንድ🤔 ይህ ጥያቄ ይኖር ይሆናል፤ ለመሰብሰብ እና ለምምክክር 🤔የውስጥን ለመግለጥ 🤔 የሌላውንም ለመስማት እና ምስጢር የሚጠብቅ አቅም ያለው አለ? 🤔እንዲህ ዓይነት ሥፍራስ የት አለ?

🙏የመሰባሰብ ዓላማችንንም ግባችንንም በዘላለማዊው ላይ እናድርግ። ❤ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ብቻ ይሁን!!❤ ያን ጊዜ ሁሉ 🥰መልካም ይሆናል።

🥰🥰🥰 ኑ እንሰባሰብ ፥ እንመካከር!!

👉ለበለጠ መረጃ፦

0910733710

👉አዲስ አበባ ሀያት አደባባይ

🥰🤝 ይምጡ 🧎‍♂️🧎‍♂️🧎‍♂️ ይጸልዩ ይባረኩበት🙌🙌🙌

🥰 Share 🤝 Share 🤗ይደረግ!!

18/06/2025

HAEMS አስደሳች ዜና ለስነ መለኮት ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

ከሐርቨስት አፍርካ ኢቫንጄልካል ሚሽን ሴሚናሪ ( HAEMS )

ሐርቨስት አፍርካ ኢቫንጄልካል ሚሽን ሴሚናሪ ( ) ለ2018 ትምህርት ዘመን ተማሪዎችን በተለያየ የስነመለኮት ትምህርት ዲፓርትመንቶችና Levelሎች ወይንም ደረጃዎች ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በታላቅ አከብሮት ያበስራል።

ሐርቨስት አፍርካ ኢቫንጄልካል ሚሽን ሴሚናሪ ( HAEMS )

- Masters of Divinity በBibilical Studies,
- Masters of Divinity በMissiology, እና
- Masters of Divinity በPastorial Studies

በመደበኛ፣ በሳምንቱ መጨረሻ፣ በማታ፣ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ በእንግልዘኛ ቋንቋ ብቻ የሚያሰለጥን መሆኑን አሁንም በታላቅ አከብሮት ያበስራል።

ታዲያ

ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ቅርንጫፎች

አድስ አበባ
ወላይታ
በሀዋሳ
ዳውሮ እና
አርባምንጭ እንድሁም ጎፋ ሳውላ ስሆን

ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ቅርንጫፎቻችን ደግሞ

ኬኒያ ናይሮቢ
ኬኒያ ኤልዶሬት
ኬንያ ኪሲ እና
ዩጋንዳ ካምፓላ

መሆናቸውን አሁንም በታላቅ አክብሮት እናበስራለን።

ልብ ይበሉ

ሐርቨስት አፍሪካ ኢቫንጄልካል ሚሽን ሴሚነሪ ልየት የሚያደርጋቸው

1. አለም አቀፍ እና አገር አቀፊ እውቅና ያለው መሆኑ

2. በአለማችን ስነመለኮት ትምህርት ስመጥር ከሆነው ከአሜሪካው ጆርጂያ ሴንትራል ዩኒቨርስቲ አብሮ የሚሰራ መሆኑ

3. AETA ማለትም Association of Education and Training in All-Tribes ከተሰኘው ከአለም አቀፍ የስነመለኮት እውቅና ሰጪ ተቋም ሙሉ እውቅና ያገኘ ያለው

3. በአገር አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስትያናት ካውንስል የስነ መለኮት ተቋም ሙሉ እውቅና ያለው መሆኑ

4. ከእትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ጋር እንዲሁም ከሁሉም ከወንጌል አማኝ ቤተእምነቶች ጋር አብሮ የሚሰራ መሆኑ

5. አስተማሪዎቻችን ኢቫንጄሊካል የሆኑ እውቅ ፕሮፈሰሮች ከተለያዩ አገሮች በቴክኖሎጂ በመታገዝ ከያሉበት አገር ሆነው እስካለንበት ደርሰው የሚያስተምሩበት ሁኔታ መመቻቸቱ

6. በተመጣጣኝ ክፊያ ከፍተኛ ጥራት ያለውን ትምህርት በአቅራቢያው ሆነው የማሚያገኙበት መሆኑ

7. ትምህርት ቤታችን Harvest Africa Evangelical Mission Seminary
( HAEMS) በአፍሪካ እና በተለያዩ አገራት ከሚገኙ መንፈሳዊ ተቋማት ጋር አብሮ የሚሰራ በመሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ከአገር ወጥተው የሚማሩበትንና የሚያገለግሉበትን ዕድል የሚያመቻች መሆኑ

በሌላም በኩል የዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች ከሃምሳ በመቶ እስከ ሙሉ ስኮላርሽፕ እድል የሚያገኙበት መሆኑ

8. ቤተመጻሕፍቶቻችን ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ ቅርብ ጊዜ የታተሙ እና ለለሚወስዱዋቸው ኮርሶች የተመረጡ ሶፍት ኮፒ በዲጂታል ላይብረሪ ባሉበት ሆነው መጠቀም የሚችሉ መሆኑ ለየት ያደርገዋል።

የሚዝገባ ጊዜ

ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 30 የሚቆይ ስሆን የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው ነሐሴ 3 እና 4/ 2017 ዓ.ም መሆኑን በታላቅ አከብሮት እናበስራለን።

ለመመዝገብ ጎግል ዶክ ፎርም ኦንላይን መሙላት እንድሁም በሪጅስትራል ቢሮ ስልክ ቁጥር ደውለው በማሳወቅ መመዝገብ የሚትችሉ መሆኑን በታላቅ ደስታ በድጋሚ እናበስራለን።

ለበለጠ መረጃ በስክሪን ላይ በተገለጹ ስልክ ቁጥሮች ላይ በመደወል ተጨሪ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።

በስልክ ቁጥር፤

09 11 00 76 53
09 10 09 74 29

ለኢንተርናሽናል ኦፊስ

+254723686597
+2519 01 50 91 45

አፍርካዊያንን በማብቃት አለምን በወንጌል እንድረስ!!

HARVEST AFRICA EVANGELICAL MISSION SEMINARY!!

Google Doc form Link:

https://forms.gle/MS8iajfCCZyCgdfP8

ኤፍታህ ቲዩብ
Christian tube - ክርስቲያን ቲዩብ
Nikodimos Christian Show
HAEMS
Harvest Nations Hnmi
Christ Army Tv Worldwide


Highlights

18/06/2025

የሶዶ ከተማ አቀፍ መዘምራን

 ...መጋቢ ትዝታው ታላቅ ፀጋ ያለው ዘማሪ ፣ የቃሉ ሰባኪ፣ ለገባው የወንጌል እውነት አንቱታን እና ክብርን ጥሎ መሰደብን የመረጠ፣ በክፉዎች አንደበት ሲብጠለጠል የሚውል የዘመናችን የወንጌል...
17/06/2025

...
መጋቢ ትዝታው ታላቅ ፀጋ ያለው ዘማሪ ፣ የቃሉ ሰባኪ፣ ለገባው የወንጌል እውነት አንቱታን እና ክብርን ጥሎ መሰደብን የመረጠ፣ በክፉዎች አንደበት ሲብጠለጠል የሚውል የዘመናችን የወንጌል አርበኛ ነው። ማንም ሰው ከህግ በላይ ስላይደለ፣ በሀገሪቷም ህግ ስላለ መክሰስ ፍርድቤት ማቆም መብት ነው። ነገር ግን እውነትን በማስረጃ መናገርና፣ ብዙዎች ከሲኦል በኢየሱስ አምነው እንዲድኑ ማድረግ ወንጀል አይደለም። መጋቢ ትዜ እመኑኝ በከባድ ሞገስ በከተማው ትልቅ አደባባይ የመዝሙር ድግስ ያቀርባል፣ በክርስቲያን ፖድካስትም ቀርቦ ጌታ እንዴት ወደህይወቱ እንደመጣ፣ እንዴት እንዳዳነው ይመሰክርልናል ፣ ቃሉን ያካፍለናል።
በክስና በማስፈራራት የማታስቆመው እሳት የላሰ ወንጌል ሰባኪ ትውልድ መጥቷል...

17/06/2025

ድንቅ የወላይተኛ መዝ/ር በዘማሪ አበል

Address


Telephone

+251910733710

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prophet Misganu Milkias posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Prophet Misganu Milkias:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share