
30/11/2022
ኳታር ዛሬም ግብረ ሰዶማውያንን ማባረር ቀጥላለች
(እለታዊ የኢትዮ7 መረጃ)
የትናንት ምሽቱን የኢራን እና አሜሪካን እግር ኳስ ጫወታ ለመታደም የመጣ አሜሪካዊ የግብረሰዶሞች አርማ ያለበትን ምልክት በክንዱ ላይ ለብሶ በመገኘቱ ወደ ሜዳ እንዳይገባ አና ከሀገረ እዲወጣ ተደርጓል።
የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊ የሆነው አሜሪካዊ ግለሰብን የኳታር የፀጥታ አስከባሪዎች አስገድደው ወደ ሜዳ እንዳይገባ አድርገዋል በ24 ሰአት ውስጥ ሀገሪቱ ለቆ እዲወጣም ትዛዝ ተላልፏል።
በዚህ አይነት ጉዳይ ኳታር ወደ ሜዳው ሊገቡ ሲሉ እንዲመለሱ ያደረገችው ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ፤ ኳታር የግብረሰዶም ምልክት ይዞ ወይም ለብሶ በሀገሯ መንቀሳቀስን በጥብቅ ትከለክላለች።