
28/08/2023
ይድነቃቸው ከበደ ታስሮ ቀረ። ኤርሚያስ መኩሪያ ታስሮ ቀረ። በላይ በቀለ ታስሮ ቀረ። ሌላም ብዙ ሰው ታስሮ ቀረ። ከትናንት የከፋ ጊዜ ላይ መሆናችን የሚታወቀው፣ በፊት ሰው ሲታሰር መደንገጥ፣ "ፍቷቸው" ማለት ነበረ።
አሁን ሁሉንም ዓይነት ግፍ ተለማምደነው ለብዙ ነገር ግድ የሌለው ይበዛል። ሰው ሲሞት፣ ቁጥሩ እና አገዳደሉም የማይደንቀን ጊዜ ላይ ደርሰናል። ደጅ እንደተሰጣ እቃ ሰው ጠፋ ሲባል ሁሉ መደነቅ እየቀነሰ፣ ሰብዓዊነት ቀስ በቀስ እየቀዘቀዘ መጣ።
በርግጥ መከራ እና ግፍ አዲስ አይደለም። ነገር ግን የአሁኑን የከፋ የሚያደርገው፣ ሁሉንም ከስር ከስር እየጋቱ ያለማምዱናል። ያደነዝዙናል። :-/
Yohanes Molla - ዮሐንስ ሞላ