03/09/2025
#ዓባይ
ግድቡ ተጠናቋል ሲባል ምን ማለት ነው ?
~ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአጠቃላይ ከ13 ተርባይኖች 5,150 ሜጋዋት ማመንጨት የሚችልበት አቅም ላይ ይገኛል።
- እስካሁን ከ71 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ ተይዟል። ቀሪው 2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመጪዎቹ 7-10 ቀናት ውስጥ ይያዛል።
- በግድቡ የተያዘው ውሃ ወደኋላ ከ246 ኪሎ ሜትር በላይ ይተኛል፤ እስካሁን ባለው 240 ኪሎ ሜትር ላይ ተደርሷል። ርቀቱ ከአዲስ አበባ እስከ ሻሸመኔ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ገንብታ ባጠናቀቀችው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አማካኝነት ኃይል እያገኘች ትገኛለች።
የኃይል ማመንጫ ግድቡ ነሐሴ 24/2017 ላይ 2530 ሜጋ ዋት በማመንጨት ኃይል መስጠት ችሏል።
- ግድቡ ተጠናቋል ሲባል ምን ማለት ነው ?
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋናው ግድብ በ1.8 ኪሎ ሜትር እርዝማኔና 145 ሜትር ከፍታ ተገንብቶ ተጠናቋል።
በአጠቃላይ ከ10 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር ያህል ኮንክሪት (RCC) ሙሌት ተካሂዷል።
የግድቡ የስረኛው ክፍል 150 ሜትር ስፋት አለው። የላይኛው ክፍል ደግሞ 11 ሜትር ስፋት ሲኖረው ሁለት መኪኖችን ጎን ለጎን ማሳለፍ ይችላል።
ኃይል ማመንጨት የሚችሉ 13 ተርባይኖች ተከላ የተጠናቀቀ ሲሆን ከእነዚህ ተርባይኖች 5150 ሜጋ ዋት ኃይል ማመንጨት ይቻላል።
በግድቡ የውጨኛው ክፍል የሚታዩት የብረት አሸንዳዎች በግራ እና በቀኝ በኩል ላሉ ኃይል የሚያመነጩ ተርባይኖች ውኃ የሚተላለፍባቸው ሲሆን እያንዳንዳቸው 8.5 ሜትር ዲያሜትር ስፋት አላቸው። 300 ሜትር ኪዩብ በሰከንድ ማሳለፍ አቅም አላቸው።
በግራ የኃይል ማመንጫ 7 ተርባይኖች ሲኖሩ በቀኝ የኃይል ማመንጫ ደግሞ 6 ተርባይኖች ሙሉ ለሙሉ ተከላቸው ተጠናቋል።
ከዚህ ውስጥ 3ቱ የቅድመ ኃይል ተርባይኖች በመጠን አነስ ያሉ ሲሆን ቀሪዎቹ 10 ተርባይኖች እያንዳንዳቸው 400 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም አላቸው።
ግድቡ ያመነጨው ኃይል በሁለት መስመሮች ማለትም በጣና በለስ አድርጎ በደብረ ማርቆስ እንደዚሁም በአሶሳ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ብሔራዊ የኃይል ቋት በመግባት ላይ ይገኛል።
ከዋናው ግድብ በተጨማሪ የህዳሴ ግድቡ የኮሬቻ ግድብ (Saddle Dam) ከዋናው ግድብ በ15 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።
ርዝመቱ 5.2 ኪሎ ሜትር እና 50 ሜትር ከፍታ ላይ ሆኖ ሙሉ ለሙሉ በ15 ሚሊየን ሜትሪክ ኪዩብ ድንጋይ የተሞላ ነው። የተያዘው ውሃ ሾልኮ እንዳያልፍ ከ30-40 ሴንቲ ሜትር ውፍረት ባለው ኮንክሪት ተለብጧል።
እስካሁን ከ71 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሃ ተይዟል። አጠቃላይ ግድቡ የሚይዘው 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ነው፤ የሚቀረው ከ2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ያልበለጠ ነው።
ቀሪው 2.1 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በመጪዎቹ 7-10 ቀናት ውስጥ ይያዛል።
በግድቡ የተያዘው ውሃ ወደኋላ ከ246 ኪሎ ሜትር በላይ ይተኛል። እስካሁን ባለው 240 ኪሎ ሜትር ላይ ተደርሷል። ርቀቱ ከአዲስ አበባ እስከ ሻሸመኔ ያልፋል።
የኮሬቻ (saddle dam) 74 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ ለመያዝ ወይም የሚያመነጨውን 5150 ሜጋዋት ለማመንጨት የሚያስፈልገውን የውሃ መጠን ለመያዝ በጣም አስፈላጊ ነው።
#ታላቁየኢትዮጵያህዳሴግድብ