Aregahagn Loyal Gunner

Aregahagn Loyal Gunner –በኢትዮጵያ ትልቁ የአርሰናል ቻናል ነው። ስለ አርሰናል አዳዲስና ትኩስ መረጃዎች የዝውውር ፣ ዜናዎች ፣ኃይላይቶች፣ቪዲዬች፣ ትንታኔ በቀጥታ ያገኛሉ።
___________________


https://t.me/

26/02/2026

Manchester City's Point Deduction.

ቼልሲ ከአርሰናል የተገናኙበት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቀቀ*************በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ ቼልሲ እና አርሰናል ነጥብ ተጋርተዋል፡፡በስታምፎርድ ብሪጅ...
30/11/2025

ቼልሲ ከአርሰናል የተገናኙበት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቀቀ
*************

በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ ቼልሲ እና አርሰናል ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

በስታምፎርድ ብሪጅ በተደረገው ጨዋታ ሞይሰስ ካይሴዶ ሚካኤል ሜሪኖ ላይ በሰራው ጥፋት 38ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ቢወጣም ቼልሲ አንድ ነጥብ አግኝቷል፡፡

ትሬቨር ቻሎባህ ቼልሲን ቀዳሚ ያደረገች ግብ ሲያስቆጥር ሚካኤል ሜሪኖ ደግሞ የአርሰናልን የአቻነት ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

መድፈኞቹ ከተከታያቸው ያላቸውን የነጥብ ልዩነት የሚያሳፉበትን አጋጣሚ ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል፡፡ በውድድር ዓመቱ ለ3ኛ ጊዜ አቻ የተለያየው አርሰናል በ30 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡

ቼልሲ ከአርሰናል የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ…በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከአርሰናል ዛሬ የሚያደርጉት የለንደን የደርቢ በጉጉት ይጠበቃል፡፡ምሽት...
30/11/2025

ቼልሲ ከአርሰናል የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ…

በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በስታምፎርድ ብሪጅ ቼልሲ ከአርሰናል ዛሬ የሚያደርጉት የለንደን የደርቢ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በሚከናወነው ጨዋታ ሁለቱ የለንደን ክለቦች የሚያደርጉት ፍልሚያ ተጠባቂ ነው፡፡

በሊጉ 1ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሁለቱ ክለቦች በሳምንቱ አጋማሽ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፋቸው ጨዋታውን ተጠባቂ አድርጎታል፡፡

አርሰናል በሊጉ ባደርጋቸው12 ጨዋታዎች ዘጠኙን በማሸነፍ እና ሁለቱን አቻ በመውጣት እንዲሁም አንድ ጊዜ ብቻ በመሸነፍ በ29 ነጥብ ሊጉን እየመራ ይገኛል፡፡

የምዕራብ ለንደኑ ቼልሲ በበኩሉ በ23 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን÷ በትላልቅ ጨዋታዎች ላይ የሚያሳየው እንቅስቃሴ ለአርሰናል ብርቱ ተፎካካሪ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

የከተማ ተቀናቃኞቹ በታሪካቸው195 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ÷77 ጊዜ አርሰናል ሲያሸንፍ፣ ቼልሲ 66 ጊዜ አሸንፏል፤ 56 ጊዜ ደግሞ በአቻነት ጨዋታውን አጠናቅቀዋል፡፡

አርሰናል የነጥብ ልዩነቱን ለማስቀጠል እንዲሁም ቼልሲ በሊጉ የፉክክር ሒደት ውስጥ ለመቆየት የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡

ባለፉት ዓመታት 6 ጊዜ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ ያቀኑት መድፈኞቹ አንድም ጊዜ ሽንፈት ያላስተናገዱ ሲሆን÷ አርሰናል ለመጨረሻ ጊዜ በቼልሲ ሽንፈት የገጠመው በ2021 ነሐሴ ወር ላይ ነበር፡፡

የሊጉ መርሐ ግብር ቀደም ብሎ 9 ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከማንቼስተር ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል፡፡

ምሽት 11 ሰዓት ከ05 አስቶንቪላ ከወልቭስ፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከሊቨርፑል እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ከብራይተን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ቼልሲ ከ አርሰናል የሚያደርጉትን ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል*************በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ ቼልሲ ከ አርሰናል የሚገናኙበት ጨዋታ የሳምንቱ ትል...
25/11/2025

ቼልሲ ከ አርሰናል የሚያደርጉትን ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል
*************

በ13ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በለንደን ደርቢ ቼልሲ ከ አርሰናል የሚገናኙበት ጨዋታ የሳምንቱ ትልቁ መርሀ ግብር ነው።

እሁድ በስታምፎርድ ብሪጅ ሁለቱ የለንደን ክለቦች የሚያደርጉትን ጨዋታ አንቶኒ ቴይለር በዋና ዳኝነት እንደሚመሩት ፕሪሚየር ሊጉ አሳውቋል።

አንቶኒ ቴይለር በዚህ ዓመት ቼልሲ ሊቨርፑልን 2 ለ 1 ያሸነፈበትን ጨዋታ እና አርሰናል ፉልሀምን 1 ለ 0 ያሸነፈበትን ጨዋታ መርተዋል።

ሊጉን በ29 ነጥብ እየመራ የሚገኘው አርሰናል በ23 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ቼልሲ የሚያደርጉትን ጨዋታ VAR ላይ ጆን ብሩክስ ተመድበዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aregahagn Loyal Gunner posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share