ቆቅ ሚዲያ - Qoq Media

ቆቅ ሚዲያ - Qoq Media ❝ያላወቁ አለቁ፤ ያልጠረጠሩ ተመነጠሩ‼️❞

ሰበር ዜና‼️በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በፋኖ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መከላከያ፣ ሚሊሻና ፖሊስ ምንም ጉዳት ሳያደርሱ በጀግናው የወሎ አማራ ፋኖ ድባቅ ተመተዋል። የተወ...
03/06/2023

ሰበር ዜና‼️

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በፋኖ ላይ እርምጃ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ መከላከያ፣ ሚሊሻና ፖሊስ ምንም ጉዳት ሳያደርሱ በጀግናው የወሎ አማራ ፋኖ ድባቅ ተመተዋል። የተወሰኑት በፋኖ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከምርከኞቹ በተጨማሪ 3 ብሬን/መትረየስ፣ 17 ክላሽ፣ 2 M14 ገቢ ተደርጓል።

ዐምሐራ▮ትግሉ ላይቀለበስ ተቀጣጥሏል‼️************ ከጎጃም እስከ ጎንደር ከወሎ እስከ ሸዋ የኦሮሙማው ጨፍጫፊ ቡድን በኪሳራ የታጀበ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ትግራይ መሬት በህፃናት፡ ...
03/06/2023

ዐምሐራ▮ትግሉ ላይቀለበስ ተቀጣጥሏል‼️
************

ከጎጃም እስከ ጎንደር ከወሎ እስከ ሸዋ የኦሮሙማው ጨፍጫፊ ቡድን በኪሳራ የታጀበ ዘመቻ እያደረገ ይገኛል። ትግራይ መሬት በህፃናት፡ ሴትና ሚኒሻ ብቻ ግባተ መሬቱ የተፈፀመውና ቀሪው ተገርፎ የወጣው መኬ እንደተለመደው ከትቅ ማስፈታት ወደ ትጥቅ ማስረከብ ተሸጋግሯል። አስቀድሞ የተፈራው እየደረሰ ነው፤ ከገበሬ እስከ ከተሜ ልቡ ሸፍቷል፤ በየቦታው ወደጫካ የሚገባው ቁጥር አሻቅቧል።

በመላው ዐማራ አልገዛም የሚለው ቁጥር እየጨመረ መጥቷል ጫካወች የህዝባዊ ሰራዊቱ መኖሪያ ቤት እየሆኑ ነው ኦሮሙማው ትጥቅ ማስፈታቱን ከማወጁ አስቀድሞ ክልሉን የጦርነት ማእከል በማድረግ በሰው ሃይልም በኢኮኖሚም አድቅቆ ከጥይት ያመለጠውን በረሃብ ለመፍጀት በማሰብ የተጀመረው ጉዞ በታሰበው ልክ አልተጓዘም ጠቅላዩና ሰልቃጩ ኦሮሙማ ማዳበሪያውን ለባሌና አሩሲ ገበሬ ካልሆነ ለዐማራ ገበሬ አይገባውም በማለት ከልክሎ የመታነቂያ ገመዱን እያጠበቀው ይገኛል ።

የብልጽግናው ፊልድ ማርሻል ጦርነቱን በይፋ ሲጀምሩት ስኬት አልባ እንደሚሆኑ የተናገሩ በርካቶች ነበሩ የጥይት ድምጽ ሰምቶ የማያውቅ ግለሰብ ከዚህ ሰውየ የተሻለ ነገሮችን መረዳት የሚችል ይመስለኛል ከጠቅላዩ ጀመሮ ኦሮሙማው የተናገረው ሰምሮለት አያውቅም ዱቄት ያሏትን ወያኔን ተንበርከው ለምነው ታርቀዋል እንዲህ አይነት ውርደት በዘራችሁ አይደረስ በማለት ከተሳለቁባትን ተሃት ታጣቂ ተውሰው ዐማራ ክልል ላይ አሰማርተዋል ።

በጎጃምና ሸዋ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ገጠሩ ክፍል ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆኗል የቀበሌ አመራሮችና ፋኖወች ተግባብተው እየሰሩ ነው በሰሜን ሸዋ ከግርማ የሽ ጥላ መገደል ማግስት ጀመሮ ከፍተኛ ውጊያ የተደረገበት ይፋት የሚባለው ምስራቁ የሸዋ ክፍል ሲሆን ከአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ ጀምሮ ኤፍራታና ግድም ወረዳ በተለይ ማጀቴ አጣየ ቀወት ወረዳ ሸዋሮቢት አስቸጋሪ ጊዜ ያሳለፉ አካባቢወች ቢሆኑም የኦሮሙማን አከርካሪ ሰብረውታል ለማለት ያስደፍራል ።

ሌላኛው ወረራ የተደረገበት ጣርማ በር ወረዳ ሲሆን ደብረ ሲና ሾላ ሜዳ አርማንያ ጭራ ሜዳ ማፉድ አጋም በር ጋሹ አንባ ዋይሎ በተባሉ ቦታወች ለግዳጅ የወጣው ሰራዊት ከግማሽ በላይ የሚሆነው ትጥቅ በማስፈታት ፋንታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎችን እያስረከበ ከፊሉ ከፋኖ ጎን ተሰልፎ ለመታገል ሲወስን ያልቻለው ልብሱን እየቀየረ አምልጧል ።

መንዝ፡ መሀል ሜዳ፡ ጓሳ፡ ሞላሌ ጫካ አካባቢ የሰራዊቱን ቁመና ወደ ተራ ታጣቂነት ዝቅ ያደረገ ንጹሃንን ኢላማ በማድረጉ የተበሳጩ የዐማራና የደቡብ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላቶች በገፍ ከነትጥቃቸው እየከዱ በማስቸገራቸው ከመሀል ሜዳ ጀምሮ እስከ ታችኛው ይፋት አካባቢ የተበታተነውን ሰራዊት በመሰብሰብ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ ላይ ተደረሶ መሀል ሜዳ ሞላሌ መዘዞ ባሽ መንዝ ጌራ መንዝ ማማ አስከ ግሸ ራቤል የነበረው የስርአቱ ወታደር ተኖ ከመጥፋቱ በፊት ሰብሰብው ለማስወጣት ተገደዋል በዚህ አካባቢ ህዝባዊ ሰራዊቱ ተደራጅቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ።

የሰርአቱ ወታደር ከጣርማ በር ወረዳም ተለቃቅሞ ወጥቷል ኤፍራታና ግድም ወረዳ የሰፈረው በተለይም ማጀቴ ከተማ የሚገኘው ሰራዊት በይፋ ከግምጃ ቤት መሳሪያ እያወጣ በመሸጥ ጠላ ሲለጋ ከመዋል ያለፈ ሳባራ መሳሪያ እንኳን ማግኘት አልቻለም በአንጻሩ እስከ ቅርብ ጊዜ በተሰማ መረጃ ከ200 በላይ የሰራዊቱ አባላት ትጥቃቸውን ለፋኖ እያስረከቡ ከአካባቢውና ከገዳይ አዛዦቻቸው መዳፍ አምልጠዋል ተሰውረዋል ።

ቀወት ወረዳ ግንቦት 21 የታላቋ ገዳም የጻድቃኔ ማርያም ገዳም ለ10 ዓመት የተገነባውን ህንጻ መመረቁን አስመልክቶ በርካታ አርሶ አደር ወደ አካባቢው እንደሚያቀና ከብአደን ተላላኪወች ጥቆማ የደረሰው የብልጽግና ሰራዊት በመከናይዝድ ታግዞ በቱርክ መንገድ ነጌሶ በሚባል ቦታ በማቋረጥ ከመረጃ አድራሾች ውጭ በሆነ ጉዞ በኦሮሞ ብሄረስብ አስተዳደር በኩል በሌሊት በመጓዝ በሸዋ አመራሮች በድሮን ካልሆነ በእግረኛ የሚችላቸው የለም በማለት እንዲጠፋ ከተፈረደበት የራሳ ገበሬ ምድር ኩሬ በረት ከሚባል ከአፋር ክልል ድንበር ላይ የሚገኝ አካባቢ ሰፍሮ ነበር ።

የአካባቢው ነዋሪ ንጋት ከቤቱ ሲወጣ ሰራዊቱ ከየበራቸው ተገትሯል አርሶ አደሩ ያለ ምንም መደናገጥ ትጥቁን አሰማሮ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይጓዛል የሰራዊቱ አዛዦች በከፍተኛ መርበትበት ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመሄድ እንዳትዋጉን ተውን ሂዱና ግጠሙ ሽፍታና ነፍሰ ገዳይ የተከማቸበት አካባቢ ነው ተብለን ነው በዓሉን ተጠቅመን የመጣነው በማለት ይገልጻሉ የአካባቢው ሽማግሌዎች በጨዋ ደንብ ነፍሰ ገዳይ የሚባል የለም የላኳችሁ ሌባና ነፍሰ ገዳይ ባንዳና ተላላኪ ዐማራ ያልሆኑ ስለሆኑ አካባቢውን ዐቢይ አህመድን እንኳን ይዘው ቢመጡ መምራት እንደማይችሉ ቁርጡን በመናገር ትጥቅ ለማስፈታት ካሰባችሁ ህዝቡ እየገደለ ለመሞት ማንም እንደ ማያቆመው ፋኖ ማለት ቄሱም ሸሁም መሆኑን አስረድተው የተራበውን ወታደራችሁን አምጡና ለበዓል ከመጣችሁ ተጋበዙ በማለት ለበዓሉ የታረደውን ከ5 በላይ በሬ በልተው አመስግነው በየቀኑ እራሳ ካልገባችሁ እእያለ ጦር የሚያዝባችሁ ኤልያስ አበበ የሚባል ባለስልጣን ነው በማለት ሚስጥር አውጥተው ወደኋላ በመመለስ ሰፊ በረት የሚባል አካባቢ ላይ ሰፈርዋል ።

በዛሬው እለት እራሳ ጉባ ወደሚባል ተራራ ዙ 23 አጥምደው የተንቀሳቀሱ ሲሆን ደመቀ ክብረትና ወንድሙ ሽመልስ ክብረት የተባሉ አርበኞች ሰፍረዋል እርምጃ ውሰዱ ተብለን ነው ማለታቸውን ተከትሎ እስከ ነገ 6 ሰዓት አካባቢውን ለቀው ካልወጡ ከሳምንት በፊት ከደረሰባችሁ በላይ ዋጋ ትከፍላላችሁ የሚል መልእክት ከህዝቡ ተሰምቷል ለማስታወስ ያህል ደመቀ ክብረት ማለት ወያኔ ጣርማበር ደርሳ በተመለሰች ጊዜ ከሸዋ ሮቢት መሻገር እንዳትችል ያደረጋት ኢቢሲና ፋና በዓንድ ቀን ዊጊያ 16 የትህነግ ታጣቂ መግደሉን በዜና የነገሩን 27 ዓመት በአርበኝነት መኖሩን የመሰከሩለት አምሳለ በላይ ዘለቀ የሆነ አርበኛ ነው ክህደት በዓንድ ዓመት መሆኑ ነው ።

ሌላኛው ሸዋ መርሃ ቤቴ ዓለም ከተማ ካራ ምሽግ እንሳሮ ለሚ ሚዳ መራኛ ዘመሮ ጸሃየ ስነ የሚባል ቦታ ያልታሰበ ከበባ በማድረግ ለወራት የሚበቃ ተተኳሽ ትጥቅ ወደ ህዝባዊ ሰራዊቱ ገብቷል ከበባ ውስጥ የገቡ የስርአቱ ወታደሮችም እስከ አሁን መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ።

በጎጃም የሆነውን በሰፊው አወራለሁ ተቀዛቅዞ የከረመው የሰሜን ወሎው ትግል ውስጥ ውስጡን ስር ሰዷል የብልጽግና ሰራዊት ከራያ ምድር እየወጣ ነው መንገድ መሪ ፋኖ ጠቋሚ የነበሩ እቃቸውን መጫን ጀምረዋል ።

ድሽቃውም ስናይፐሩም መትረጌሱም በሬኑም ተኳሹም አስትኳሹም በየቦታው ተዘጋጅቶ መቀመጡን አያውቁም አፍንጫቸው ስር ከተማው ገጠሩ ልቡ የሸፈተ መሆኑን የዘነጉ ከጠላት ወግንው ህዝባቸውን ያስመቱ ፋኖውን እንደወራሪ በየጫካው ያንከራተቱ ቁርጥ እየበሉ ብስኩት ያስከለከሉ አሁንም ከስህተታቸው እንድማሩ መምከር ያስፈልጋል ከሸዋ ፋኖ ትምርት መውሰድ ያስፈልጋል ባንዳወችን በዘመድ በስልክ ምክር በመስጠት በርካቶችን አቅርቧል።

ገዳዩም ሟቹም ዐማራ እንዳይሆን በትእግስትና በአስተውሎት መጓዝ ያስፈልጋል በእርግጥ ትግሉ ግማሽ መንገድ ተጉዟል ስርአቱ ሽባ ሆኗል የማስፈጸም አቅሙ ወርዷል ዘረፋው ሌብነቱ ሊደፋው ተቃርቧል የዐማራ ዲያስፖራ ጉሮሮውን አንቆታል እዳው መፈናፈኛ አሳጥቶታል ህዝባዊ መሰረቱ ከስሩ ተገንድሷል ተረባሮ የመቅበሩ ስራ ይቀራል።

መረጃውን ሸር ያድረጉ ‼️
ግንቦት 25 /2015

29/04/2023

ሰበር_መረጃ‼️

የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ችሮታው ከአጣዬ ወደ ሸዋሮቢት ማረሚያ ቤት በአብይ ሰራዊት ታፍነው መወሰዳቸው ተሰማ።

ዋና አስተዳዳሪውን የአብይ ሰራዊት አዛዥ በፋኖ ፈርጀዋቸዋል ነው የተባለው።በኦሮሚያ ብልፅግና ሰዎች አጣዬን ለማውደም በሚያደርጉት ጥረት ምርጥ አማራ ሆነው የሚመክቱት ዋና አስተዳዳሪው በሽመልስ ሰራዊት ታግተው ሸዋሮቢት ማረሚያ ይገኛሉ‼️

©ያሬድ አላዩ

29/04/2023

ከኢትዮጵያ መፍረስ በኋላ የዐምሐራ ህልውና እንዴት ይቀጥል⁉
(ለማይቀረው የአባት ሐገር ዐምሐራ ምስረታ እንዘጋጅ ‼)

#ክፍል➋
*****
በክፍል አንድ ግልፅ ለማድረግ እንደሞከርሁት ሀገሪቱ "An empire in a terminal collapse" በሚባለው የአይቀሬው የመፍረስ ዋዜማ ላይ ብትሆንም፥ የአማራ ህዝብ ግን ከገባበት ጥልቅ ድንዛዜ ወጥቶ የራሱን አባት ሀገር እውን ለማድረግ እየሞከረ አለመሆኑ፤ ለዚህም በምክንያትነት ያስቀመጥኋቸው ነጥቦች ሲኖሩ፥ በዚህ ሁለተኛ ክፍል በይደር ካቆምንበት እንደሚከተለው እንቀጥላለን። መልካም ንባብ!

2. "The Chosen People" Analogy፦

* የዐምሐራን ህዝብ "ብፅዕት ኢትዮጵያ" በሚል ቅዠት አስረው በዚህ መጠን እንዲደነዝዝና "Idolatry of Ethiopia" የህዝባችን መገለጫ Trademark እንዲሆን ካደረጉት ዋነኛ ተግዳሮቶች መካከል ራሱን በሃይማኖት በተለይም በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናችን ጉያ ለበርካታ መቶ አመታት የደበቀ የ Neuro-Pirates መሠሪ ቡድን በህዝባችን ላይ በከፈተው የ Cognitive Warfare አማካኝነት ነው። የአማራ ህዝብ የ Cognitive Warfare ሰለባ መሆኑን አምነን መቀበል ይኖርብናል‼‼‼ መፍትሔ ማምጣት የምንችለውም ከዚህ መራራ እውነት ስንነሳ ብቻ ነው‼‼‼

የዐምሐራን ህዝብ የ Cognitive Warfare ሰለባ ማን አደረገው⁉

"When you control a man's thinking you do not have to worry about his actions. You do not have to tell him not to stand here or go yonder. He will find his 'proper place' and will stay in it. You do not need to send him to the back door. He will go without being told. In fact, if there is no back door, he will cut one for his special benefit. His education makes it necessary."

( Carter G. Woodson)

* በዐምሐራ ህዝብ ላይ የተራዘመ የ Cognitive war በመክፈት ከውስጥ ሲገዘግዘው የኖረው ኃይል ራሱን በቤተክርስቲያን ጉያ የደበቀ ከግል ጥቅም በዘለለ አንዳችም ራዕይ የሌለው አቴና-ወጊ የ Neuro-Pirates ስብስብ ነው‼‼‼

ይህ በቤተክርስቲያን ጉያ የተሸሸገው Neuro-Pirates ኃይል ከቤተክርስቲያኗ ዶግማዊ አስተምህሮ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው፣ ለቤተክርስቲያናችንም እንዲሁም 80% ለሚሆነው የእምነቱ ተከታይ ለሆነው የአማራ ህዝብም ዋነኛ ጠላት ሲሆን የዚህ ቡድን ከትናንት እስከ ዛሬ ብቸኛ ፍላጎት በሃይማኖቷ ታዛ ተጠልሎ ህዝባችንን "የተመረጠችው ኢትዮጵያ ጠባቂ ነህ" በማለት መንፈሳዊ ሽፋን በመስጠት ህዝባችንን አደንዝዞ የግል ጥቅሙን ማሳደድ ነው።

ይህ በዘመን ቅብብሎሽ ራሱን እየተካና እያባዛ የሚሄድ አቴና-ወጊ የ Neuro-Pirates ቡድን ፥ የአማራ ህዝብ ጄኖሳይድ ሲፈፀምበት ወይ ዝምታን ይመርጣል አልያም ጉዳዩን የሃይማኖት ቅርፅ ያለው ለማስመሰል ይጥራል (በሻሸመኔና ሐረር በአማራ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ወደ ሃይማኖት ለመቀየር የሄደበትን ርቀት እያሰብን) ይህም ካልተሳካለት "ቅድስት ኢትዮጵያ ልትፈተን ግድ ነው" ብሎ በአማራ ህዝብ እልቂት ይሳለቃል።

ይህ ኃይል በቤተክርስቲያን ውስጥ ይመሽግ እንጂ ቤተክርስቲያናችን ራሷ አደጋ ላይ ስትወድቅ ድምፁን ማሰማት አይፈልግም። ለዚህም ነው ይህ አቴና-ወጊ የ Neuro-Pirates ቡድን የአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የቤተክርስቲያናችንም ጠላት ነው የምንለው‼‼

ይህ አቴና-ወጊ ቡድን ምናባዊ አይደለምና ከግብሩና ጎልተው ከሚታዩ መሪዎቹ ጋር በማያያዝ መጠሪያ ስም ሰጥተነው ልናልፍ ይገባል‼

በመሠረታዊነት ይህ አቴና-ወጊ ቡድን ህዝባችንን "በቅድስት ኢትዮጵያ" ተረት ሲያደነዝዝ የኖረው በሁለት መልኩ ነው፤

1. Numerology የሚባልን ነገር እንደ አዲስ ግኝት በማስተጋባት "ይህ ቁጥር ቅዱስ ነው፣ የኢትዮጵያ ቁጥር ምስጢራዊው ቅዱስ ቁጥር በመሆኑ አትፈርስም" የሚል ተረትና ባዶ ጥንቆላ ሲሆን ይህንን ተረት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲቀባበሉት መጥተው አሁን ዶክተር ሮዳስ ታደሰ በሚባል ተላላኪ ባንዳ በዋናነት እየተቀነቀነና ህዝባችን በዚህ ተረት ደንዝዞ ሀገር አልባ እንዲሆን እየተሰራበት ይገኛል።

ይህንን በቁጥር የሚጠነቁል አቴና-ወጊ ኃይልና ግብረአበሮቹን ከዚህ በኋላ "ሮዳሳዊያን" በሚል ልንጠራው ግድ ይላል።

2. ሌላኛው ህዝባችንን በተረት አደንዝዞ ሀገር አልባ ሊያደርግ እየሰራ የሚገኘው አቴና-ወጊ ኃይል "Ethiopia is a spiritually mysterious land" ብሎ ከመስበክ አልፎ "ኢትዮጵያ የተሰወሩ ከተሞች ያላት፣ እግዚአብሔር ከሌላው ዓለም በተለየ ልዩ ጥበቃ እንደሚያደርግላት" የሚሰብክ፣ መፅሐፍ የሚፅፍና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ህዝባችንን ሲያደነዝዝ የኖረ ኃይል ነው። እንደ ሮዳሳዊያን ክንፍ ሁሉ፥ ይህም ቡድን ከትውልድ ወደ ትውልድ ይህንን ተረት ሲያስቀጥል ኖሮ ዛሬ አውራ መሪ አለው፦ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ የተባለ የብአዴን "የአማራ መልሶ ማቋቋም ድርጅት" መሪና በቤተክርስቲያን ጉያ የተሸሸገ ተላላኪ ባንዳ። ስለሆነም ይህንን ክንፍ "አለማየዋዊያን" ብለን ልንጠራው ግድ ይላል።

* ሮዳሳዊያንና አለማየዋዊያን ዛሬ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀሙ ያሉትን አይነት ማደንዘዣ የእስራኤል ራባዮች (Rabbis) በአይሁድ ህዝብ ላይ ለሁለት ሺህ አመታት ሲፈፅሙት የነበረው አይነት ማደንዘዣ ነው። የእስራኤል ራባዮች የአይሁድ ህዝብን "እስራኤል በአንዳች መንፈሳዊ ተአምር ሀገር ሆና ትመሰረታለች፣ በቀጣዩ አመት ፀሎታችንን በኢየሩሳሌም እናደርጋለን" እያሉ ከመስበክ አልፈው የፀሎታቸው መቋጫ እንዲሆን አሳምነውት ነበር። የራባዮቹ "የቀጣይ አመት በኢየሩሳሌም ..." ተረት ግን አይሁድን ለሁለት ሺህ አመታት ከዘግናኝ እልቂትና ሰቆቃ አልታደገውም። አይሁድን የታደገው የፅዮናዊያን ብሔርተኛ እንቅስቃሴ ነው‼የአይሁድን ህዝብ ባለ ሀገር ያደረገው የራባዮች ተረት ሳይሆን የቴዎዶር ሄርዝልና ጓደኞቹ በተግባር የተደገፈ የፅዮናዊያን ብሔርተኛ ንቅናቄ ነው‼

ያዕቆብ (የአብርሃም የልጅ ልጅ) "እስራኤል" የሚለውን ስያሜ ካገኘ ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ራዕይ ድረስ ይህ ስም በመፅሐፍ ቅዱስ ያልተጠቀሰበት ቦታ የለም። ያ ማለት ግን ሀገር አልባ ላለመሆን ወይም ተሳዳጅ ላለመሆን ዋስትና ነው ማለት አልነበረም።

በተመሣሣይ፥ ሮዳሳዊያንና አለማየዋዊያን "ኢትዮጵያ በመንፈሳዊው ዓለም ፍፁም የተለየ ስፍራ ያላት፣ ህዝቦቿም በፈጣሪ የተመረጡ" አድርገው የሚያስተምሩት ተረታቸው ህዝባችንን ክፉኛ በማደንዘዝ አላስፈላጊ ዋጋ እንዲከፍል ሲያደርገው ኖሯል፤ ዛሬም እያስከፈለው ይገኛል።

ህዝባችንን ከዚህ የ Neuro-Pirates Cognitive warfare ነፃ ማድረግ ካልቻልን የአማራን ህዝብ ከፈፅሞ መጥፋት መታደግም ሆነ እፎይታ የሚያገኝበትን አባት ሀገር ምስረታ እውን ማድረግ ፈፅሞ አንችልም‼

ስለሆነም ለዘመናት በህዝባችን ላይ ተከፍቶበት የቆየውን cognitive war ለመቀልበስ Reverse Social Engineering መጠቀም ይኖርብናል ‼ ይህንን ስናደርግ ሰለባ ከሆነው vast majority የህዝባችን ክፍል ብቻ ሳይሆን "ብሔርተኛ" ናቸው ከምንላቸው የቅርብ ጓዶቻችን ሳይቀር ቀላል የማይባል Cognitive Inertia እንደሚጠብቀን ለአፍታም ቢሆን መጠራጠር የለብንም‼

እንደ አማራ ህዝብ ለረጅም ዘመናት የ Cognitive warfare ሰለባ ሆኖ በኖረ ህዝብ ላይ የ Reverse Social Engineering Programme ተግባራዊ በሚደረግበት ጊዜ ነባሩን የጥፋት እሳቤ የሚተካ ገንቢ እሳቤ አስቀድመን ለህዝባችን በሰነቅንለት ራዕይ ልክ ካላዘጋጀን Paradigmatic Vacuum መፈጠሩ አይቀሬ ነው‼ ይህ አይነቱ Paradigmatic Vacuum ሳይፈጠር በህዝባችን ልብና አዕምሮ ላይ በፍጥነት እኛ የምንፈልገውን አምሐራዊ Ultranationalism (in its refinest form) ማስረፅ ይኖርብናል‼

** ህዝባችን የገባበትን ጥልቅ ድንዛዜ La Belle Indifférence ("Beautiful Ignorance") በሁለት ክፍል በአጭሩ ያየንበትን በዚህ እንቋጭና አይቀሬው የኢምፓየሯ ኢትዮጵያ መበተን in what form ሊከናወን ይችላል የሚለውን፤ እንዲሁም በእያንዳንዱ አማራጭ የኢምፓየሯ የፍርሰት ሁኔታ ውስጥ የአማራ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውን በክፍል ሶስት የምናየው ይሆናል ለዛሬው በዚህ ይብቃን።
:
:
:
:
:
:
:

=========== ይቀጥላል ==========

እግዚአብሔር የአማራን ህዝብ አብዝቶ ይባርክ‼‼‼

የጠራ ራዕያችንና ቅዱሱ ተልዕኳችን አባት ሀገር አማራን መመስረት ነው‼️
__________
ቅዳሜ፣ መጋቢት 16ቀን 2015 ዓ.ም
ቆቅ ሚዲያ - Qoq Media
❝ያላወቁ አለቁ፤ ያልጠረጠሩ ተመነጠሩ‼️❞

ከአማራ ህዝባዊ ትግል የጋራ ጥምረት የተላለፈ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ!አማራውን አዋርዶ ልዩ ሀይላችን እና ፋኖን ለመበተን፣ለመግደል፣አፍኖ ለመውሰድ፣ ትጥቅ ለመግፈፍ ተልዕኮ ይዞ ከሚሰራ ማንኛውም ...
12/04/2023

ከአማራ ህዝባዊ ትግል የጋራ ጥምረት የተላለፈ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ!

አማራውን አዋርዶ ልዩ ሀይላችን እና ፋኖን ለመበተን፣ለመግደል፣አፍኖ ለመውሰድ፣ ትጥቅ ለመግፈፍ ተልዕኮ ይዞ ከሚሰራ ማንኛውም አደረጃጀት ጋር ትብብር ከማድረግ እንድንቆጠብ የአማራ ህዝባዊ ትግል የጋራ ጥምረት ጥብቅ ማስጠንቂያ ተላልፏል።

መረጃ በመስጠት፣ የትራንስፖርት፣ የሆቴል፣ የህትመት፣ የአዳራሽ፣ የፕሮፖጋንዳ፣ የቁሳቁስ፣ የግብይት፣ የምግብና መጠጥና መሰል ትብብር ወይም አገልግሎት ተከፍሎንም ሆነ ሳይከፈለን አገልግሎት ከመስጠት ፍፁም እንድንቆጠብ በጥብቅ እናሳስባለን።

የተላለፈውን ማስጠንቀቂያና ገደብ ተላልፎ ከጠላት ጋር ማንኛውም ትስስር ፈጥሮ በሚገኝ ከሃዲ ግለሰብ፣ቡድንና ድርጅት ላይ ያነጣጠረ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን የአማራ ህዝባዊ የጋራ ጥምረት በፅኑ ያስጠነቅቃል።

የአማራ ህዝባዊ ትግል የጋራ ጥምረት!

🔥🔥 የመረጃ ምንጭ CMN ETHIOPIA ፌስቡክ ቻናል እንዲሁም ከ YouTube

እንቢኝ‼️

ኢትዮጵያውያን  እንቢይ በሉ። አብሩ።ተነጋገሩ። መብታችሁን ለማስከበር አንድ ላይ ቁሙ። ለህዝባዊ እንቢተኝነት ተዘጋጁ። መንግስት ውሳኔውን ቀልብሶ፣ ሁኔታዎችን በሰላማዊ መንገድ ነገሩ እንዲፈታ...
12/04/2023

ኢትዮጵያውያን እንቢይ በሉ። አብሩ።ተነጋገሩ። መብታችሁን ለማስከበር አንድ ላይ ቁሙ። ለህዝባዊ እንቢተኝነት ተዘጋጁ። መንግስት ውሳኔውን ቀልብሶ፣ ሁኔታዎችን በሰላማዊ መንገድ ነገሩ እንዲፈታ ካላደረገ የሚመጣው ጦስ በታሪክ የሚያስጠይቀው ነው። = አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ

💚💛❤️ 💚💛❤️አማራ

የሶማሌ ህዝብ አይዞን ዐማራ ከጎንህ ነው‼️ #ሰበር  #ሼርትናንት ፕረዘደንት ሙስጠፌ በልዩ ኃይሉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል። በልዩ ኃይሉ ውሳኔ የተቆ*ጣው የሶማሌ ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ...
12/04/2023

የሶማሌ ህዝብ አይዞን ዐማራ ከጎንህ ነው‼️ #ሰበር #ሼር

ትናንት ፕረዘደንት ሙስጠፌ በልዩ ኃይሉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል። በልዩ ኃይሉ ውሳኔ የተቆ*ጣው የሶማሌ ህዝብ ወደ አደባባይ ወጥቶ ቁ*ጣውን እየገለፀ ይገኛል። አፋርም እያጉረመረመ ነው። አሁን ትጥቅህን ነገ ቀበቶህን ፍታ ለሚልህ የአስመሳዩ የአብይ አህመድ ኦሮሙማ ኃይል እጅህን እንዳትሰጥ‼️

የራያና ወልቃይትን ጉዳይ የሚወስነው  59+ (አምሳና ከዚያ በላይ) የሚሆነው  ሚሊዮን ዐማራ እንጂ ብአዴንም፣ የፌደራል መንግሥትም፣ አንዳች ምድራዊ ኃይል አይደለም። በሕገመንግሥቱ መሠረት አ...
25/03/2023

የራያና ወልቃይትን ጉዳይ የሚወስነው 59+ (አምሳና ከዚያ በላይ) የሚሆነው ሚሊዮን ዐማራ እንጂ ብአዴንም፣ የፌደራል መንግሥትም፣ አንዳች ምድራዊ ኃይል አይደለም። በሕገመንግሥቱ መሠረት አስረክቡን የሚለውም በፍጹም አይሠራም - ብአዴን ቢስማማም ባይስማማም። ብአዴኖች ጥሩ አማካሪ ካላቸው የስምምነት ፊርማቸውን አያስቀምጡም፤ ልዩ ኃይሉንና ፋኖን ውጡ ብለው አያስረክቡም።

ምክንያቱም የእነሱን ስምምነት የሚያከብር ሕዝብና ፋኖ የለም። የምክንያት ምክንያቱ ደግሞ የዐብይን ትእዛዝ የሚቀበሉ ከሆነ በፍርሓት የተነሳ ነው፤ ነገር ግን ወልቃይትንና ራያን አሳልፈው ከሰጡ ብአዴን የእውነት ያከትምለታል፤ ስለዚህ ከየፌደራል መንግሥቱ ይልቅ ለብአዴንና ብአዴኖች አስፈሪም ግብዓተ መሬታቸውን የሚፈፅመው ህዝቡ/ፋኖ ነው። ይኸ እንዴት ይሆናል? ካልን እነሱ ተስማምተው ለማስረከብ ሲሞክሩ ዝም የሚል ህዝብም ፋኖም ስለማይኖር ወዲያውኑ ጦርነቱ ይፈነዳል። ያኔ የሚፈነዳው ጦርነት ብአዴንን ከጠላት ጎራ የመደበና የሚጠርግ ይሆናል። መጀመሪያ ብአዴንን ካልተወገደ ትግሉ አይሠምርም ሲባል ያልሰማው ወይም በተስፋ የታገሰው ኃይል ያኔ የግድ ይቆርጣል።

ዘገየም አልዘገየም፣ ከዘገዬ በመዘግቱ እልቂቱ የከፋ ቢሆንም ። በዚህ ዐይነት (ሁኔታ) ወደ ጦርነት ከተገባ ደግሞ ፋኖ በህዝቡ ይጥለቀለቃል፤ ከዚያም ትግሉ እየጠነከረ ሲሄድ ራያና ወልቃይትን፣ መተከልና ሸዋን እያካተተና እየሰፋ አባት አገር ዐማራ የግድ እውን ይሆናል - ምክንያቱም የጠላቶቻችን ፍላጎት አገር መገንባት ስለሆነ። ኢትዮጵያ በገሐድ መፍረሷ እውን ይሆናል። ድኅረ መበታተን በኋላ ርስት የማስመለስ ጦርነት የግድ ይሆናል - ያኔ ዐባት ዐገር ዐማራን የሚገዳደር ምድራዊ ኃይል በፍፁም አይኖርም።

_______
ቅዳሜ፣ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም
ቆቅ ሚዲያ - Qoq Media
❝ያላወቁ አለቁ፤ ያልጠረጠሩ ተመነጠሩ‼️❞

Address

Haile G/Selassie
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቆቅ ሚዲያ - Qoq Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ቆቅ ሚዲያ - Qoq Media:

Share