Boolee Aanna 05 Komminkishiin

Boolee Aanna 05 Komminkishiin Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Boolee Aanna 05 Komminkishiin, Media/News Company, Addis Ababa.

09/07/2025

የወረዳዉን ነዋሪ ሰላም ለማስጠበቅ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የወረዳውን ነዋሪዎችን ሰላም ለማስጠበቅ ሰላም ለሁሉም በሚል መርሕ ከባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት ተግተን እያሰራን ነው ሲሉ የጽ/ ቤቱ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ተስፋዬ ገልፀዋል።

ኃላፊው በ2017 በጀት ዓመት ከሰሯቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል ለዝግጅት ክፍላችን በሰጡት መረጃ የ2016 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ከባለሙያና ባድርሻ አካላት ጋር በመገምገም የ2017 በጀት የጽ/ቤቱ መሪ እቅድ እና ሌሎች አጋዥ እቅዶችን ከማዘጋጀት ጎን ለጎን በርካታ ዝርዝር ተግባራት ተከናዉነዋል ፤ በጽ/ቤቱ ዋና ዋና ግቦች ዉስጥት ትኩረት አድርገን የሰራንባቸዉ ግቦች የሕዝቡን የሰላም ባለቤትነትን ማሳደግ ፣የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ማጎልበት ፣የሕብረተሰቡን የጸጥታ ስጋት መቀነስ ፣የወንጀል ድርጊቶችን መቀነስ ፣የጸጥታ ተቋማትን ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት የቅድመ ወንጀል መከላከል እና ግጭት አፈታት እንዲሁም የሐይማኖት እሴቶች ላይ መሆኑን በመግለጽ በዋናነት በቅድመ ወንጀል መከላከል ግጭት አፈታት የስጋት ቦታዎችን በመለየት ከሕብረተሰቡ ጋር በመወያየት የአደባባይ በአላትን ከማከበር በፊት ቅድመ ዝግጅት በመድረግ በአላቶች ካለምንም የጸጥታ ችግር ተከብረዋል፤ለምሳሌ ፣ የአዲስ አመት፤ መስቀል ፣ የእሬቻ ፣የጥምቀት ኢድ አል ፈጥር ፣አረፋ የህዝባዊና ሐይባኖታዊ በዓላት በወረዳው ካለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ የሰላም ሰራዊቶችን ስምሪት በመስጠት፣ በማነቃቃት፣ ከፖሊስና ደምብ ማስከብር ጽ/ቤት እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከፍተኛ ርብርብ መደረጉ፣የሰላም እሴትን ለመገንባት ግንዛቤ የመፍጠር ሽፋን ከነበረዉ 4000 ወደ 12500 ማሳድግ መቻሉን፣ ወንጀልን በመከላከል ፣በመቆጣጠር እና እርምጃ በመውሰድ የወንጀል ድርጊቶችን ከነበረው 57% መቀነስ መቻሉን ፣በ10 የወንጀል ዓይነት (ሰው መግደል ፣መኪና ስርቆት ፣በጦር /መሳ/ዘረፋ ፣ለመግደል ሙከራ ፣የመ/ዕቃ ስርቆት ፣ቤት ሰብሮ ስርቆት ፣ቅሚያ ፣ሌብነት እና ከኪስ ስርቆት)የመለየት ፣መከላከል እና እርምጃ በመውሰድ ችግሩን 60% መቀነስ መቻሉን ጠቁመዋል።

በመጨረሻም አሁን ያለው ሰላም ሕብረተሰቡ ደከመኝ ሰለቸኝ ፣ደሞዝ ይኸፈለኝ ፣ እጅ መንሻ ይሰጠኝ ሳይል 7/24 ከአስተዳደሩና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ተገናጅቶ በመስራት ያመጣዉ ሰላም መሆኑን አዉቆ አስከ አሁን ሲያደርግ የነበረዉ ተግባር ሳይቀንስ ማስቀጠል እንዳለበት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በዉይይት በያገባኛል ስሜት መፍታት እንደሚገባው በመግለጽ ፤ይሕን ስራ ስንሰራ የነበሩ ባለ ድርሻ አካለት ሰላም አንድ ጊዜ ተሰርቶ የሚያበቃ አለመሆን አዉቀዉ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ከጎናችን እንዲሆኑ በወረዳ አስተዳደሩና በጽ/ቤቴ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ በማለት በትግበራ ወቅት ከጎናቸዉ ሆነዉ በቅንጅት ሲሰሩ ለነበሩ ባለድርሻ አካላት ቀጣይ ከጎናቸዉ እንዲሆኑ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።

ቦሌ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን
ሀምሌ 02/2017ዓ.ም

24/06/2025
19/06/2025
31/05/2025

Address

Addis Ababa

Telephone

+251940220144

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Boolee Aanna 05 Komminkishiin posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share