31/07/2025
ኤስፍሳክ ( ) ያዘጋጀው ይህ የወጣቶች አግሮኢኮሎጂ ስታርትአፕ ውድድር ከሀሳብ በዘለለ በተግባር ክንውን ላይ ለሚገኙ የአዲስ አበባ ወጣቶች የቀረበ ነው።
ግብዓቶችን ማቅረብ፣ ማምረት፣ ማቀነባበር፣ ማሸግ፣ ማስተዋወቅ፣ ሽያጭን ማቀላጠፍ፣ ወዘተ . . . በየትኛውም የምግብ ሥርዓት ክፍል ላይ ወይም የምርት ሠንሰለት ላይ የሚሰሩ ወጣቶች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።
ዋናው ነገር፦ ሥራችሁ በጤናማ እና ሀገር-በቀል ምግቦች ላይ ወይም በአግሮኢኮሎጂ ግብርና ላይ ያተኮረ ሊሆን ይገባል።
የማመልከቻ ጊዜው እስከ ነገ ዓርብ፣ ሐምሌ 25/2017 ብቻ ነው።
በውድድሩ ገጽ ላይ የሚገኘውን ኦንላየን ፎርም በመሙላት እና የአንድ-ደቂቃ ቪዲዮ መበላክ ተሳተፉ።
የውድድሩን ገጽ ይጎብኙ፦
https://esfsac-ethiopia.org/competition/