Mengistu Defere Info

https://youtu.be/bGqlXV_Fa_E
19/10/2022

https://youtu.be/bGqlXV_Fa_E

Ethiopia News | Eritrea news | Sudan news | Debretsion Gebremichael | Amhara Regional state | Tplf | Sudan Army | Jawar Mohammed | Eritrea news | Abey ...

19/10/2022

Ethiopia News | Eritrea news | Sudan news | Debretsion Gebremichael | Amhara Regional state | Tplf | Sudan Army | Jawar Mohammed | Eritrea news | Abey ...

18/10/2022

#ሰበር!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ማይጨውን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ቁልፍ ወታደራዊ ቦታዎች ያዘ።ሰራዊቱ በሽሽት ላይ የሚገኘውን ወራሪ እየጠረገ አዲ አባ ሙሳ የተባለ ቦታን አልፎ የአምባላጌ ተራሮችን በርቀት እያየ ወደ ማይጨው እየገሰገሰ ነው።

ወደፊት ብቻ‼የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ዛሬም ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ግስጋሴ በሁሉም አቅጣጫ አጠናክሮ ቀጥሏል።
18/10/2022

ወደፊት ብቻ‼

የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ዛሬም ወደ መቀሌ የሚያደርገውን ግስጋሴ በሁሉም አቅጣጫ አጠናክሮ ቀጥሏል።

የታባታችሁም አትወጧትም===========================“ማረጋገጫ ከተሰጠን ጦርነቱን አቁመን ሀገር ለቀን ለመውጣት ዝግጁ ነው” የህወሃት አመራሮችጦርነቱ ወደ መገባደዱ መድረሱን ተከ...
16/10/2022

የታባታችሁም አትወጧትም
===========================

“ማረጋገጫ ከተሰጠን ጦርነቱን አቁመን ሀገር ለቀን ለመውጣት ዝግጁ ነው” የህወሃት አመራሮች

ጦርነቱ ወደ መገባደዱ መድረሱን ተከትሎ የህወሃት ቁንጮዎች አነጋጋሪ ውሳኔ ላይ እንደ ደረሱ ከውስጥ አዋቂ የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከቀን ወደ ቀን፣ ከሰዓት ወደ ሰዓት የከበባው ቀለበት በሁሉም አቅጣጫ እየጠበበ መምጣቱን የተረዱት የህወሃት ሰዎች አለም አቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት መውጫ ካመቻቸልን ጦርነቱን ወዲያው አቁመን ከሀገር ለመውጣት ተዘጋጅተናል የሚል አቋም ላይ እንደደረሱና ይሄንንም አቋማቸውን በቴድሮስ አድሃኖም አማካኝነት ለአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ተደራሽ እንዳደረጉ ታውቋል። ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የህወሃት ሚዲያዎች በሙሉ ተኩስ አቁሙን እንደተቀበሉ ተደርጎ እንዲሰራጭ ከማዕከል ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ዛሬ ቴድሮስ አድሃኖም በርሊን ላይ ይህንኑ የህወሃት አመራሮችን ማስመለጫ መንገድ በተመለከተ ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንደተነጋገረና በቀጣይ ቀናትም ወደ ብራሰልስ እንደሚጓዝ ይጠበቃል። ዛሬ በርሊን ላይ ካነጋገራቸው አካላት መካከል የአሜሪካ ሰዎችም እንደሚገኙበት ነው ጀርመን ካሉ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች የተረዳነው።

ጦርነቱ መቀልበስ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ጠላትም ወዳጅም ተረድቷል። አሁን መፍትሄው፣ ውሳኔውም ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያ እጅ ነው። መከላከያ ሰራዊት ግዳጁን በሚገርም ኦፕሬሽን አፈፃፀም እየተወጣ ነው። ህወሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገዱ የማይቀር ብቻ ሳይሆን በጣም በፍጥነት የሚሆን ነገር መሆኑ ተረጋግጧል። ከአሁን በኋላ ከህወሃት በኋላ የሚኖረው የትግራይ ክልል አስተዳደርና የሰሜኑን የሀገራችን ክፍልን መልሶ ማቋቋም ላይ ትኩረት መደረግ አለበት!

ኢትዮጵያ ያለ ህወሃት
ትግራይ ያለ ህወሃት ሁሉም ጥሩ ይሆናል!

ሱሌማን አብደላ

ወላጅ አባቱን ገድሎታል======================በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በባቄሎ ቀበሌ ወላጅ አባቱን የገደለው ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ❗️==============...
16/10/2022

ወላጅ አባቱን ገድሎታል
======================

በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በባቄሎ ቀበሌ ወላጅ አባቱን የገደለው ወንጀለኛ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ❗️
=====================
ይህ ከታች በፎቶ ግራፍ የምትመለከቱት ግለሰብ አቶ አለሙ ልዑልሰገድ ይባላል ነዋሪነቱ በጣይቱ ክፍለ ከተማ ስር ባቄሎ ቀበሌ ሎዬ አገር ጎጥ ሲሆን ከወላጂ አባቱ ጋር በነበረው የመሬት አለመግባባት ግጭት ሆን ብሎ ለመግደል በማሰብ ጥቅምት 3ቀን 2015 ዓ.ም ከለሊቱ 6:30 ሰአት በሚሆንበት ጊዜ ወላጂ አባቱ አቶ ልዑልሰገድ የሽዳኛ የ74 አመት እድሜ ያላቸው አባቱ በእንቅልፍ ላይ እያሉ በሩን ገንጥሎ በመግባት በባህርዛፍ ፍልጥ እንጨት ጭንቅላታቸውን በተኙበት ቦታ ደጋግሞ በመምታት ሊገላቸው ችሏል።

የድብደባ ድምፅ የሰማ ጎረቤት ነአቆ ሃ/ማርያም በቦታው ደርሶ ለመያዝ ቢሞክርም እሱንም በያዘው ፍልጥ እንጨት መሃል አናቱን ፈንክቶት ለጊዜው የተሰወረ ቢሆንም በተሰራው ጥብቅ ክትትልና የደፈጣ ስራ ተጠርጣሪው ጫካ ውስጥ በማደር ከጠዋቱ 12:30 ከደፈጠበት ተነስቶ ለመሰወር ሲንቀሳቀስ ደፈጣ ላይ ባሉ የፀጥታ ሀይሎቻችን በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራውን በቡድን እያጣራን የምንገኝ ሲሆን ተጠርጣሪውን ለመያዝ በተደረገው ጥረት ለተሳተፋችሁ አመራርና የፀጥታ አባላት ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው። ለሟች ነፍሳቸውን ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያኑርልን።
ወንጀልን እንፀየፍ!!

መረጃው:- የእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ነወ።

16/10/2022

የአሜሪካኑ ከፍተኛ ዲፕሎማት ማይክ ሀመር ተንጨረጨሩ

ጣና ፎረም ላይ የአሜሪካውን ከፍተኛ ዲፕሎማት ያበሳጨው እና ያንጨረጨረው የአፍሪካ ምሁራን ጥያቄ ምንድን ነው?

ምሁራኑ ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከልም አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ ለምን አትተዋትም? የሚል ይገኝበታል፡፡

በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስር ያለው የሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዪት የተዘጋጀው 10ኛው የጣና ፎረም በባህርዳር ተካሂዷል።

በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ላይ ባተኮረው በዚህ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የሰላም፣ ፖለቲካ እና ደህንነት ምሁራን፣ መሪዎች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈውበታል።

የዚህ ጉባኤ አንድ አካል የሆነው "የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ በተደረገው የፓናል ውይይት ላይ አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ ዌበር (ዶ/ር) ፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ የተመድ የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር ሀና ቴተህ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎችም ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት ታዋቂው ኬኒያዊው የህግ እና ፖለቲካ ተንታኙ ፕሮፌሰር ፓትሪክ ሉሙምባን ጨምሮ ሌሎችም አፍሪካዊያን ምሁራን ለአምባሳደር ሀመር ጥያቄ አቅርበዋል።

ምሁራኑ ለአምባሳደር ማይክ ሐመር ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከልም አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ ለምን አትተዋትም? አሜሪካ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው፤ እንዲሁም ቻይና ለአፍሪካ ከአሜሪካ በተሻለ መንገድ እየሰራች ነው እና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተዋል።

በውይይቱ ባህርዳርን እና አካባቢዋ ያላትን ውበት በማድነቅ የጀመሩት አምባሳደር ማይክ ሀመር በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉ አካባቢዎች በርካታ ንጹሀን ዜጎች በጦርነቱ እየተጎዱ እና ህይወታቸውን እያጡ በመሆኑ ጦርነቱ ሊያበቃ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከአፍሪካ ምሁራን ለተነሳላቸው ጥያቄ ስሜት በተቀላቀለበት መንገድ ሀገራቸውን በሚከላከል መንገድ ምላሽ ሰጥተዋል።
አፍሪካ ችግሯን በራሷ እንድትፈታ አሜሪካ ለምን አትተወንም? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም "አፍሪካ በራሷ ችግሯን መፍታት ትችላለች?" ሲሉ ጥያቄ በመጠየቅ ምላሽ የሰጡት አምባሳደር ማይክ ሀመር " እንደዛ ማድረግ እምትችል አይመስለኝም" ሲሉም አክለዋል።

" እኔ ባህርዳር የተገኘሁት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለመንገር አይደለም። አፍሪካም ሆነች አሜሪካ ችግራቸውን ለመፍታት በጋራ መስራት ግን አለባቸው ብለዋል" ሲሉም አምባሳደሩ ተናግረዋል።

አምባሳደር ማይክ ሀመር አክለውም " በአፍሪካ እንደ አሜሪካ ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረገ ሀገር ወይም ተቋም የለም፣ የአፍሪካዊያንን ህይወት በመታደግ ከአሜሪካ በላይ የሰራ ሀገር የለም፣ ፍጹም ላንሆን እንችላለን፣ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ሀላፊነት ታውቃለች ነገር ግን በብዙ መንገድ ለአፍሪካ ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን" በሚል ከምሁራኑ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው "አሜሪካ ለአፍሪካ ድጋፍ እያደረገች ቢሆንም አፍሪካ ራሷን በምትችልበት መንገድ ድጋፍ እያደረገች አይደለም" ሲሉ ለአምባሳደር ማይክ ሐመር ምላሽ ሰጥተዋል።

አሜሪካ በተለይም ስንዴ እና መሰል የሰብዓዊ እርዳታዎችን ለአፍሪካ ድጋፍ ብታደርግም አፍሪካ ከተረጅነት እንድትወጣ የሚያደርግ ፖሊሲ የላትም ሲሉም ዋሸንግተንን ተችተዋል።

16/10/2022

የህወሓት ታጣቂዎች አላማጣን ለቀው በመኾኒ አቅጣጫ እየወጡ እንደሆነ የደረሰኝ መረጃ አመላክቷል።

16/10/2022

መቀሌ‼

ህውሃት እስረኞችን መሳሪያ አስታጥቆ ወደ ግንባር እያስገባ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

15/10/2022

እውነታው ይኸው ነው እናመሰግናለን መምህር ... የሚጠቅመን የሚበጅን የሚያሻግረን ይኸው አንድነታችን ህብረታችን ነው!!!

" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴርየትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል።ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰ...
12/10/2022

" ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ምንም አይነት እድል አይሰጥም " - ትምህርት ሚኒስቴር

የትምህርት ሚኒስቴር ፈተና አቋርጠው ለወጡ ምንም አይነት እድል አይሰጥም ብሏል።

ሚኒስቴሩ ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ፤ በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን ገልጿል።

ፈተና አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥ አሳውቋል።
Tikvah

Address

Addis Ababa

Telephone

+251903104805

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mengistu Defere Info posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Mengistu Defere Info:

Share