Esea Tube

Esea Tube አዳዲስ መረጃዎች
-ማህበራዊ
-ፖለቲካዊ
-ምጣኔሃብታዊ
@ሚዛናችን ቲዩብ(Mizanachn Media)

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአብን እና የምክርቤቱ አባል ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ - ጠ/ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫ...
06/07/2023

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአብን እና የምክርቤቱ አባል ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ - ጠ/ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል ፣ ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል።

"ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ። ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል። በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ(የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ።" የተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔለ ጠ/ሚ አብይ ካነሷቸዉ ጉዳዮች መካከል።

ለ60 ዓመታት እንቅልፍ ያልተኙት አዛውንት መነጋገሪያ ሆነዋልበቬትናም የሚኖሩት የ80 አመቱ አዛውንት ታይ ንጎክ በወጣትነታቸው ዘመን ያጋጠማቸውን የትኩሳት በሽታ ተከትሎ ላለፉት ከ60 አመታት...
05/07/2023

ለ60 ዓመታት እንቅልፍ ያልተኙት አዛውንት መነጋገሪያ ሆነዋል

በቬትናም የሚኖሩት የ80 አመቱ አዛውንት ታይ ንጎክ በወጣትነታቸው ዘመን ያጋጠማቸውን የትኩሳት በሽታ ተከትሎ ላለፉት ከ60 አመታት በላይ እንቅልፍ እንዳልተኛ ተናግረዋል። ይህ ከባድ እንቅልፍ ማጣት ከመላመድ ብዛት ህይወታቸውን እንዳልረበሸው ግን ይገልጻሉ።

ብዙ ሰዎች ለጥቂት ሰአታት እንቅልፍ ሳይወስዱ ቀኑን ሙሉ መዋሉ ይከብዳቸዋል። ነገር ግን እኚህ ቪየትናማዊ አዛውንት ያለፉትን 60 ዓመታት በንቃት አሳልፌያለሁ ይላሉ። ታይ ንጎክ ደስተኛ እና ንቁ ህይወት ለመምራት ምንም እንቅልፍ እንደማያስፈልጋቸው ከገለፁበት ጊዜ አንስቶ በትውልድ ሀገራቸው የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አግተዋል።

ሚስታቸው፣ ልጆቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና ጎረቤቶቻቸውን ጨምሮ አንድም ቀን እንቅልፍ ሲወስዳቸው አይተው እንደማያውቁ ይናገራሉ። እኚሁ አዛውንት ሙሉ በሙሉ እንቅልፍ ማጣታቸው በእሳቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳላሳደረባቸው አጥብቀው ይናገራሉ።

እንቅልፍ ማጣት በጤንነቴ ላይ ምን ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አላውቅም፣ ነገር ግን አሁንም ጤነኛ ነኝ መደበኛ ሥራዬን እንደሌሎች መሥራት እችላለሁ ሲሉ ይደመጣሉ።እ.ኤ.አ. በ1942 የተወለዱት ታይ ንጎክ በ20 ዓመታቸው በከባድ ትኩሳት መሰቃየት እንደጀመሩ ይናገራሉ ። ምንም እንኳን ከዚህ ከባድ ስቃይ በህይወት ቢተርፍም ፣ እንደገና መተኛት ግን አልቻሉም። እኚህ ቬትናማዊው ሰው የተለያዩ መድሃኒቶችን፣ ባህላዊ መድሃኒቶችን ጨምሮ እና ከፍተኛ መጠን ያለው አልኮል መውሰድ ቢሞክሩም እንቅልፍ ግን ዳግመኛ መተኛት አልቻሉም። የእንቅልፍ እጦቱ ጊዜያዊ እንደሆነ ተስፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን ለስድስት አስርት ዓመታት እንቅልፍ አጥቻለሁ ብለዋል።

05/07/2023

ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት በኃላ ወደ አፋር ለጉብኝት የሚያቀኑ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ ተነገረ

በሰሜናዊ የኢትዮጵያ ክፍሎች የነበረዉ ጦርነት ከቆመ ወዲህ የቱሪዝም እንቅስቃሴዉ መነቃቃት እየታየበት መሆኑ ተጠቁሟል። የጦርነቱን ዳፋ በዋነኛነት ከቀመሱት ሶስቱ ክልሎች አንዱ የአፋር ክልል ፤ እንደ ሀገር በስፋት በዉጭ እና በሀገር ቤት ጎብኚዎች የሚመረጡ መዳረሻዎች ያሉበት ክልል ነዉ።

ጦርነቱ ከቆመ ወዲህ ወደ ክልሉ ለጉብኝት የሚያቀኑ ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን የአፋር ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሀላፊ አቶ መሀመድ አሊ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ከተፈረመዉ የሰላም ስምምነት ወዲህ ክልሉን ለመጎብኘት የሚያቀኑ ሰዎች ቁጥር ለዉጥ ማሳየቱን ተናግረዋል። ለአብነትም ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የአፋር ክልልን ለመጎብኘት የመጡ የዉጭ ዜጎች ቁጥር 48 ብቻ እንደነበር አቶ መሀመድ አንስተዋል።

ሆኖም የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ ወዲህ ባሉት ጥቂት ወራት ግን 1 ሺህ 430 የዉጭ ጎብኚዎችና 206 የሀገር ዉስጥ ጎብኚዎች ክልሉን ጎብኝተዋል ብለዋል።ከጦርነቱ በፊት ተከስቶ የነበረዉ የኮቪድ 19 ቫይረስ በክልሉ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ ተጽዕኖ አሳድሮ የነበረ መሆኑን ሀላፊዉ አንስተዉ ፤ እርሱን ተከትሎ የመጣዉ ዉጊያ ደግሞ የበለጠ ኢንዱስትሪዉን ጎድቶት እንደነበር አስረድተዋል።

በጥቂት ወራት ዉስጥም ከተጠቀሱት የጎብኚዎች ቁጥር ከ 12 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ክልሉ ማግኘቱን አቶ መሀመድ ገልጸዋል። የአፋር ክልል እንደ ዳሎል ፣ ኤርታሌ ፣ የአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ እና ሌሎች ተፈጥሯዊ መስህቦችን የያዘ መሆኑን ተናግረዋል። የሀገር ዉስጥ ጎብኚዎችም ወደ ክልሉ በመጓዝ መስህቦችን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Esea Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share