ETHIO news

ETHIO news Streaming facts and news

11/08/2023

አዲስ እየተደረጃ በሚገኘዉ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ የዞኑ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያላስገኘ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የቢሮ ክፍፍል በመሆኑ ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ።

የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሂዷል።

በጉባኤውም አዲስ እየተደራጃ በሚገኘዉ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም ያለማግኘት እና ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል በመሆኑ በፍጹም መታረም ያለበት እንደሆነ ተገልጿል።

አባላቱ እኩል የመልማት ፣ የመበልፀግና የማደግ መብት እንዲከበርላቸው በራሳቸው እና በወከለዉ ህዝብ ስም ኢ-ፍትሃዊ የክላስተር አደረጃጀት ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ ጠይቀዋል።

አዲስ እየተደራጀ በሚገኘዉ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያለማግኘት እና ሚዛናዊ ያልሆነ ክፍፍል በመሆኑ ሊታረም እንደሚገባም ጭምር አንስተዋል።

በመጨራሻም የምክር ቤቱ አባላት በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል በክላስተር አደረጃጀት ያለዉን ኢ-ፍትሃዊ አደረጃጀቱን በሙሉ ድምፅ በመቃወም እና ይህም በቀጣይ ለሚመለከተው አካል እንዲቀርብ በመጠየቅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት 2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ተጠናቋል።

#ዘገባው የዱራሜ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ነው!

10/08/2023

የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ
***
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሶስት ህፃናት ላይ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡

የ43 ዓመት ዕድሜ ያለው ተከሳሹ ወንጀሉን የፈፀመው በክፍለ ከተማው ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ማር ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ግለሰቡ የጎረቤቱ ልጆች የሆኑ የ5፣ የ6 እና የ10 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ህፃናትን በተለያዩ ቀናት ከረሜላ እየገዛ በማታለል መኖሪያ ቤቱ ውስጥ አስገብቶ ወንጀሉን ፈፅሞባቸዋል፡፡

ወንጀሉ ከተፈፀመባቸው ህፃናት መካከል የ6 ዓመቱ ህፃን ስለሁኔታው ለወላጅ እናቱ በመናገሩ ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ይህንን ተከትሎ ሌሎቹ 2 ህፃናትም ተመሳሳይ ድርጊት እንደፈፀመባቸው በመግለፃቸው በሶስት የምርመራ መዝገቦች ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል፡፡

መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሹን ጥፋተኝነት በሰው እና በህክምና ማስረጃ በማረጋገጡ በ19 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

ህብረተሰቡ ከህግና ከማህበራዊ እሴቶች ያፈነገጡ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲያጋጥሙ ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡

ሀገራችን በህብረ ብሄራዊነቷ የምትታወቅና የተለያዩ ባህሎችና ወጎች ያላት ሀገር ነች፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከማክበረሰቡ ወግና ባህል ያፈነገጡ ድርጊቶች እያጋጠሙ መሆኑን የተመለከተ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑንየአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን ህግ ፍፁም የተከለከና በህግ የሚያስጠይቅ ተግባር በመሆኑ ከዚህ ጉዳይ ጋር የተያያዘ መረጃ እና ጥቆማ ያለው ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በግንባር በመቅረብ እንዲሁም በነፃ የስልክ መስመር 991 እና 987 እንዲሁም በ011-1- 11-01-11 እና 011-5-52-63-02 በመጠቀም መረጃና ጥቆማ መስጠት እንደሚችል የአዲስ አበባ ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

28/01/2023

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዋሽ አርባ ተገኝተው የተቀናጀ የውጊያ ልምምድ ተመልክተዋል።

የውጊያ ልምምድ አላማው የምድር እና የአየር ሀይል የውጊያ አቅሞች ተቀናጅተው በጋራ ግዳጅ የመፈጸም አቅም ማሳየት ነው። በውጊያ ልምምዱ ፣ ሜካናይዝድ ሀይል፣እግረኛ በክፍለ ጦር ደረጃ፣ የአየር ወለድ ልዩ ሀይል
እና አየር ሀይል ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ጦርነትን ማስቀረት የሚችል ሀይል እየገነባች ነው ብለዋል።

28/01/2023
27/01/2023

ግብፅን ያስደነገጠው የሱዳን መግለጫ

ሱዳን እየተጠናቀቀ ባለው የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ላይ ተቃውሞ እንደሌላት የሱዳን የሽግግር ሉአላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ተናግረዋል።

ሊቀመንበሩ ይህንን ማለታቸው የተገለጸው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በካርቱም ያደረጉትን የአንድ ቀን ጉብኝት ተከትሎ ምክር ቤታቸው ባወጣው መግለጫ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የካርቱም ጉብኝት ተከትሎ ሁለቱ መሪዎች በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ መነጋገራቸው የተገለጸ ሲሆን “ሱዳን እና ኢትዮጵያ የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከቱ ሁሉም ጉዳዮች ላይ እንደሚስማሙ እና እንደሚደጋገፉ. . . ቡርሃን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል” ብሏል መግለጫው።

በግድቡ ዙሪያ ለረጅም ጊዜ ግብፅ እና ሱዳን ግድቡ አብዛኛው ውሃው ከኢትዮጵያ የሚመነጨው ከአባይ የሚያገኙት የውሃ መጠን ላይ ተጽእኖ ስለሚኖረው በውሃ ሙሌቱ ላይ እና በግድቡ አስተዳደር ዙሪያ አሳሪ ሕጋዊ ስምምነት እንዲደረግ ሲጥሩ ቆይተዋል።

በአሁኑ ግን ግብፅ ብቻዋን የቀረች ይመስላል ፤ ያለ ያ ሁሉ የ ሱዳን ከግብፅ ጋር መስማማት እና ማበር ኢትዮጵያ ግድቡን ከመሙላትና ማመንጨት ከመጀመር ያገዳት ነገር ባይኖርም ሱዳን ወደኢትዮጵያ ሀሳብ መምጣቷ ግብፅን ሳያበሳጫት አይቀርም ።

19/01/2023

እናመሰግለን !!!

የዘንድሮ የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ በከፍተኛ ድምቀት ከሌላው ጊዜ በተለየ ልዩ በሆነ ሁኔታ በሰላም ተከብሮ ተጠናቋል፡፡

ይህ እንዲሆን ሃላፊነታችሁን የተወጣችሁ መላው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የእምነት አባቶች ፤ ላደረጋችሁት ሃላፊነት የተሞላበት አመራር ፣ መላው የእምነቱ ተከታዮችና ምእመኑ በጠቅላላ ይህ በዓል ደማቅ ያማረና ሰላማዊ እንዲሆን ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ እንዲሁም መላው የፀጥታ መዋቅርና የከተማው አመራሮች ፣ የከተማችን ወጣቶችም በከፍተኛ የሃላፊነት ስሜት እና በትህትና በዓሉ ሰላማዊና ያማረ ድባብ እንዲኖረው ከተማውን በማሳመርና በማፅዳት ብሎም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በህብረት በማስወገድ ላበረከታችሁ አስተዋፅኦ ያለአንዳች ችግር ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ ሌት ተቀን ያለረፍት ላሳያችሁ ትጋትና ርብርብ እናመሰግለን::

ከሁሉ በላይ የረዳንን ፈጣሪን እናመሰግናለን!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !!

19/01/2023

የጥምቀት በዓል በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገለፀ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከበረው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በሰላም ተጀምሮ በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ገለፀ።

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል ከሰላም ወዳዱ ሕዝብ ጋር በመተባበርና ባደረገው ቅንጅታዊ የፀጥታ ሥራ በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በመላው ሀገራችን በሰላምና በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ማለፉን ገልጿል፡፡

ለዚህ ስኬት ከግብረ-ኃይሉ የተሰጠውን መግለጫ ከግምት ውስጥ በማስገባት በዓሉ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ላደረጋችሁ ዜጎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የበዓሉ አስተባባሪዎች፣ የእምነቱ ተከታዮች፣ እንዲሁም የሀገራችን ወጣቶች ለፀጥታ አስከባሪ አካላት ያሳያችሁት ከፍተኛ ትብብር ዓርአያነት ያለው ተግባር በመሆኑ በነገው ዕለት የሚገቡ ታቦታትም እንደዛሬ ሁሉ በሰላም እንዲገቡ መላው ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እያቀረበ እስከአሁን ለአደረጋችሁት ቀና ትብብር ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች በሥራው ላይ የተሰማራችሁ የፀጥታና ደኅንነት አባላትም ከራሳችሁ በፊት የሕዝቡን ሰላምና ደኅንነት በማስቀደም የተሰጣችሁን ሀገራዊ ተልዕኮ ከህዝብ ጋር በመተባበር በብቃት በመወጣት የተፈለገውን ግብ በማሳካት ትልቁን ድርሻ ስለተወጣችሁ የጋራ ግብረ-ኃይሉ የላቀ ምስጋና አቅርቧል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ምአዲስ ወደ ዕዙ ለተቀላቀሉ የሠራዊት አባላት የህግ ግንዛቤ ማሥጨበጫ ትምህርት ተሠጠ፡፡የህግ ግንዛቤ  ማስጨበጫ ትምህርቱን የሠጡት የዕዙ ዐቃቢ ህ...
18/01/2023

የኢፌዴሪ መከላከያ ጥር 10 ቀን 2015 ዓ.ም

አዲስ ወደ ዕዙ ለተቀላቀሉ የሠራዊት አባላት የህግ ግንዛቤ ማሥጨበጫ ትምህርት ተሠጠ፡፡

የህግ ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቱን የሠጡት የዕዙ ዐቃቢ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ናቸው፡፡

ከማሰልጠኛዎች ስልጠናቸውን አጠናቀው ወደ ዕዙ ለተቀላቀሉ አዲስ የሰራዊት አባላት በከባድ እና ቀላል የዲስፕሊን ጥፋቶች በመመሪያዎች እና ደንቦች እንዲሁም በፍትሃ-ብሔር እና በወንጀል የህግ ድንጋጌዎች ዙርያ ትምህርት ተሰጥቷል ፡፡

ዳይሬክተሩ አዲስ የሰራዊት አባላት በማሰልጠኛ ቆይታቸው ስለ ውትድርና ሙያ ያገኙት ዕውቀት እንደተጠበቀ ሆኖ ሙያው ከፍተኛ የዲስፕሊን ስነ- ምግባርን የሚጠይቅ በመሆኑ ለሚሰጣቸው የግዳጅ አፈፃፀም ስኬት የወንጀልና የዲስፕሊን ህጎችን የበለጠ ማወቅ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

በተቋማችን የሚወጡት ደንቦች መመርያዎችን እና ህጎችን ጠንቅቆ በመረዳትና በመገንዘብ ተግባራዊ በማድረግ በወንጀል ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉትን አላስፈላጊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን መከላከል ያስፈልጋል ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ህጎችና ደንቦችን አለማወቅና አለመተግበር ከተጠያቂነት እንደማያድን በመገንዘብ ሰራዊቱ በሚሰማራበት ተልዕኮ ከተቋሙ የተጣለበትን ሃላፊነት በፍፁም ዲስፕሊን ሊተገብር ይገባልም ብለዋል ፡፡

18/01/2023

የሸኔ እንቅስቃሴ የታየባቸው አካባቢዎችን ወደ ቀደመ ሁኔታቸው ለመመለስ በቅንጅት እየተሰራ ነው - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ

በኦሮሚያ ክልል የሸኔ እንቅስቃሴ የታየባቸውን አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሁኔታቸው ለመመለስ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት የጸጥታ ሃይሎች ሁሉንም አይነት እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፥ የሽብር ቡድኑ ሸኔ በኦሮሚያ እና አጎራባች አካባቢዎች ህገ ወጥ ታጣቂዎችን በማሰማራት ከሌሎች የስጋት ሃይሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር በንጹሃን ዜጎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡

ሸኔ በአሮሞ ሕዝብ ስም የሚንቀሳቀስ ቢሆንም በዋነኛነት የሚያጠቃው የኦሮሞን ህዝብ ነው፤ የሽብር ቡድኑን የሚደግፉት ደግሞ ኢትዮጵያን ማዳከም የሚፈልጉ ሃይሎች ናቸው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሸኔ የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም እና ፍላጎት መሰረት ያደረገ አላማም ሆነ ምክንያት የለውም ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡

የሽብር ቡድኑን ስጋት ለመቀልበስም የተቀናጀ ሁሉን አቀፍ እርምጃ እየተሰወደ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ሲደረጉ የነበሩት የመንግስት የፖለቲካ እና የሰላም አማራጮች የመጀመሪያ አማራጭ መሆናቸውንም አስታውሰዋል፡፡

ሸኔ የሰላም ጥሪውን ተቀበሎ እኩይ ተግባሩን እንዲያቆም እና የኦሮሞ ወጣት እልቂት ማብቂያ እንዲያገኝም መላው ሕዝብ ግፊት ማድርግ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

መንግስት በየደረጃው ካሉ የመንግስት አካላት ጋር በየቀበሌው የሰላም ውይይት እያደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ሽብር ቡድኑ የተቀላቀሉ ወጣቶች በሰላም ለመንግስት እጃቸውን እንዲሰጡ እና የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ህብረተሰቡን እንዲቀላቀሉ የቅድሚያ ቅድሚ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም በርካታ ወጣቶች ጥሪውን እየተቀበሉ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

እነዚህ ሁኔታዎች ባልተቻሉባቸው አካባቢዎችም የሽብር ቡድኑ የሚያደርሰውን ሁሉን አቀፍ ጉዳት ለመቀልበስ መንግስት የሃይል እርምጅ እየወሰደ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

በዚህም በቡድኑ ታጣቂዎች፣ አባላት እና የሎጂስቲክ አቅራቢዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ነው ያሉት፡፡

እነዚህ አካባቢዎች ከሸኔ ወረራ ነጻ በመሆን ዳግም እንዲደራጁ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡

18/01/2023

በወረኢሉ ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁ ተገለጸ
*****************************

በአማራ ክልል የአባይ ተፋሰስ አካል በሆነው ወረኢሉ በተደረገ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት ከ2 ቢሊየን በርሜል በላይ ድፍድፍ ነዳጅ በከርሰምድር እንደሚገኝ በጥናት መታወቁን ኢንጅነር ታከለ ኡማ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ወረኢሉ አካባቢ ከዚህ ቀደም አንድ ኩባንያ የፍለጋ ስራ እያከናወነ የነበረ ቢሆንም በአቅም እጥረት ምክንያት ስራውን ለማቋረጥ መገደዱን የማዕድን ሚኒሰትሩ ኢ/ር ታከለ የገለጹ ሲሆን ይህንን ጨምሮ በኢትዮጵያ አራት ተፋሰሶች ላይ የነዳጅ ፍለጋ ጥናት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

አሁን መንግስት የነዳጅ ሀብቱ በአፋጣኝ ጥቅም ላይ የሚውልበትን መንገድ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኝ ኢ/ር ታከለ ኡማ በጹሑፉቸው ገልጸዋል።

18/01/2023

"ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል አደረሳችሁ!"

የጥምቀት በዓል መሰባሰቢያችን በአብሮነት መድመቂያችን እና በፍቅር መተሳሰርያችን የሆነ ዉብ በዓላችን ነው፡፡
በአለም አደባባይ ስማችንን የሚያስጠራ ፤ውበታችንን የሚገልፅ ፤ አንድንታችንን የሚሳይ ፤ ታይተው የማይጠገቡ ኢትዮጵያዊ የአብሮነት ጥበቦች በህብራዊ ቀለማት አሸብርቀው በአደባባይ የሚገለጡበት ፤እኛነታችንን የሚጎላበት፤ አለም ድምቀቱን
ለማየት ከየአቅጣጫው የሚጎርፍበት ፤ውብና ድንቅ ሀይማኖታዊ እሴቶቻችን እና ከባሀላዊ ሃብቶቻችን ዉስጥ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

አዲስ አበባችን በጥምቀት በዓል በውበት ላይ ውበት የምትጎናፀፍበት ፤ነዋሪዎቿ ተሰባስበው በጋራ የሚያሳልፉበት ፣ በርካታ የውጪ ቱሪስቶችን የምታስተናግድበት ፣ከተማዋ በሁሉም አቅጣጫ እንደ አበባ የምትፈካበት ፣በዝማሬ በአምልኮ በወጣቶችና ሴቶች የምታሸበርቅበት ፣በአባቶችና እናቶች አብሮነትና ምርቃት የምትደምቅበት ልዩ ጊዜ ነው፡፡

በአብሮነታችን ለዘላቂ ሰላማችንን እንትጋ ፤ በፍቅራችንና መከባበራችን ኢትዮጵያን እናፅና ፤በትብብራችንና በጠንካራ ስራችን ኢትዮጵያን ከፍ እናድርግ!!

መልካም ያማረ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን!!
አብሮነታችን ያጠንክርልን፤
ፍቅራችንን ያበርታልን ፤
ሰላማችንን ያብዛልን!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!

18/01/2023

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የጥምቀት በዓል ብዙ ትርጉሞችን ይዞ የሚከበር በዓል ነው። በአንድ በኩል ለክርስቲያኖች ትኅትናን የሚማሩበት፣ በእግዚአብሔር ማመናቸውን የሚያውጁበት፣ ንስሐና ድኅነት የሚያገኙበት ምልክት ሆኖ ያገለግላል። በሌላ በኩል እንደ ሀገር የጥምቀት ክብረ በዓል መልከ ብዙ የሆንን ኢትዮጵያውያን ኅብር ፈጥረን የምንደምቅበት በመሆኑ ታላቅ ቦታ ሰጥተን እናከብረዋለን።

በዓለ ጥምቀትና ትኅትና ተነጣጥለው የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም። ምክንያቱም ጥምቀት ፈጣሪ በፍጡር፣ አምላክ በሰው፣ ጌታ በአገልጋዩ የተጠመቀበት እለት ነውና። ከነበረበት ከፍታ ወርዶ ከሰው የተስተካከለበት፣ ከቆመበት የጌትነት ስፍራ ዝቅ ብሎ ትኅትናን ያሳየበት፣ ትእቢትን ሽሮ ለሰው ልጆች ትኅትናን ያስተማረበት አጋጣሚ ነው - ሥርዓተ ጥምቀቱ። በሥርዓተ ጥምቀቱ አጥማቂው ዮሐንስም ያሳየው ትኅትና እንዲሁ በምሳሌነት ይጠቀሳል። ፈጣሪው የሰጠውን ክብር እንደሚገባው ቆጥሮ በተዓብዮ ሳይታጠር፤ ‘እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?’ ብሎ ማከላከሉ የመከበር ምሥጢሩ ትኅትና እንደሆነ፣ የኃይልና የብርታት ቁልፍ ታዛዥነት ውስጥ እንዳለ፣ የበላይነት መገኛውም ወደታች ወረዶ እያገለገሉ ጽድቅን መፈጸም እንደሆነ ያስተምረናል።

ሰዎች ከላይ የሆኑ ሲመስላቸው የታቹን የማያዩና የገዘፉ ሲመስላቸው በቅንነት ጎንበስ የማይሉ ከሆነ እነሱ የጥምቀቱ ትርጉም አልገባቸው። ትኅትናን ንቀው ትዕቢትን የመረጡ፣ ዝቅ ማለት ከብዷቸው ራሳቸውን ከፍ ከፍ ያደረጉ፣ ቅንነትን ጠልተው ግፍ መሥራት የወደዱ መጨረሻቸው ዕድገት ሳይሆን ቁልቁለት፣ ክብር ሳይሆን ውርደት መሆኑን በብዙ አጋጣሚዎች ዓለም አሳይታናለች።

በተቃራኒው የተሰጣቸውን ኃይል ለመልካም ዓላማ የተጠቀሙ ዘወትር ሥማቸው በጥሩ ሲነሣ ይኖራሉ። እንደ ሙሴ ያሉት የተሰጣቸውን በትር ባሕር ከፍለው ሕዝብን ወደ ተስፋ ሲያሻግሩ፤ እንደ ጎልያድ ያሉት ከሰው ሁሉ በላይ መግዘፋቸውን ለበደል ተጠቅመውታል፤ በዚህም ምክንያት ሙሴዌች ሲወደሱ ጎልያዶች በቀላሉ በጠጠር ወድቀዋል። ዓይናችንን ገልጠን ብንመለከት በዙሪያችን ከፍታቸውን ለክፋት፣ ኃይላቸውን ለጭቆና በመጠቀማቸው አሳዛኝ ውድቀት የገጠማቸው ጎልያዶችን በአቅራቢያችን እናገኛለን። ተመሳሳዩ ዕጣ እንዳይገጥመን ሁላችንም ትኅትናና መልካምነትን ገንዘባችን ልናደርግ ይገባል።

ሌላኛው የጥምቀት ምሳሌ የመዳንና የንስሐ ምልክት መሆኑ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ፈለገ ዮርዳኖስ ከመውረዱ በፊት በኃጢአት የተሸፈነውን አዳም የኃጢአቴ ልብሱን ከላዩ ላይ ሊጥልለት የሞከረ አልነበረም። ጌታ ኢየሱስ በማዕከለ ዮርዳኖስ የመቆሙ ምክንያት የአዳምን ውርደት ለመቀበል፣ ኃጢአቱን ወስዶ ከመከራው ለማዳን፣ የሚነትበውን ልብስ ጥሎ በማይነትብ ዘላለማዊ ልብስ ለመተካት ነበር። በየዓመቱ ጥምቀቱን የምናከብረውም ከፊት-ቀድሞ ከመከራ የታደገን ክርስቶስን እያሰብን ነው።

ዛሬ የምናያቸውና የምንረማመድባቸው መንገዶች በአንድ ወቅት ጢሻ የነበሩና በፊት ቀደሞች መሥመር የወጣላቸው ናቸው። ዛሬ የሠለጠኑ ሀገሮች የሥልጣኔ ከፍታ ላይ የደረሱት በአንድ ወቅት ፊት አውራሪዎቻቸው በመከራ ውስጥ አልፈው፣ ችግርና ፈተናውን ተሻግረው መሠረት ስላኖሩላቸው እንጂ አዲስ ተዓምር ተፈጥሮላቸው አይደለም። ድኅነት፣ መታደስና ብልጽግና የሚመጣው

Address

Addis Ababa
GFDS

Telephone

+251703724820

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ETHIO news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share