The Voice of Amhara

The Voice of Amhara Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from The Voice of Amhara, Media/News Company, Addis Ababa.

https://youtu.be/a3kPmuHCe_c?si=9QUfjWrTpjVN1zvT
24/12/2024

https://youtu.be/a3kPmuHCe_c?si=9QUfjWrTpjVN1zvT

ለኤቢሲ ቴሌቪዥን የጥቆማ መረጃዎችን ለማድረስ በኤቢሲ የTelegram እና WhatsApp ስልክ ቁጥር +17203093725 ያድርሱን። የኤቢሲ ቴቪ መረጃዎችን በአማራጭ ይከታተሉ:-1) You tube - ➻ የኤቢሲ እለታዊ የዜና ዘ....

https://youtu.be/w-y7_7Wq9eg?si=jyABMgshdoreE_WG
24/12/2024

https://youtu.be/w-y7_7Wq9eg?si=jyABMgshdoreE_WG

ለኤቢሲ ቴሌቪዥን የጥቆማ መረጃዎችን ለማድረስ በኤቢሲ የTelegram እና WhatsApp ስልክ ቁጥር +17203093725 ያድርሱን። የኤቢሲ ቴቪ መረጃዎችን በአማራጭ ይከታተሉ:-1) You tube - ➻ የኤቢሲ እለታዊ የዜና ዘ....

የአገዛዙ ታጣቂዎች በአማራ ተፈናቃዮች ካምፕ  ገብተው  አምስት ሠዎችን ገደሉ። ከወለጋ ተፈናቅለው በራያ ቆቦ አቧሬ  በሚገኘው የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የአገዛዙ ታጣቂዎች ገብተው አምስት ሰዎ...
24/08/2024

የአገዛዙ ታጣቂዎች በአማራ ተፈናቃዮች ካምፕ ገብተው አምስት ሠዎችን ገደሉ።

ከወለጋ ተፈናቅለው በራያ ቆቦ አቧሬ በሚገኘው የተፈናቃዮች ካምፕ ውስጥ የአገዛዙ ታጣቂዎች ገብተው አምስት ሰዎችን እንደገደሉ ከጥቃቱ የተረፉ ተፈናቃዮች ለአማራ ድምፅ ተናገሩ።

የአገዛዙ ታጣቂዎች ወደ ካምፑ የገቡት """ከወለጋ ኦሮሞ አፈናቀለን በሚል የኦሮሞን ህዝብ ስም ታጠፋላችሁ አሁንም በቂም በቀል ከፋኖ ጋር ወግናችሁ እየወጋችሁን ነው"" እንዳሏቸው ከጥቃቱ የተረፉ ተፈናቃዮች ገልፀውልናል።

የኦሮሙማ ብልፅግና ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አማሮች ከኦሮሚያ እና አዲስ አበባ ዙሪያ ተፈናቅለው በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ ካምፖች ተጠልለው በችግር ውስጥ ይገኛሉ።

ሞት የተፈረደባቸው እስረኞች ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን ዘውዴን በደብዳቤ ተማፀኑ። በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙና የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ታራሚዎች ቅጣቱ እንዲፈጸም የሀ...
21/08/2024

ሞት የተፈረደባቸው እስረኞች ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን ዘውዴን በደብዳቤ ተማፀኑ።

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኙና የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ታራሚዎች ቅጣቱ እንዲፈጸም የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት በለጠ አሰፋ አምሜ፣ ጀበሳ ድንቁ ኦርዶፋ፣ ባዩ ጌታነህ ዜና፣ ግርማ ገዛኸኝ ማሞ እና መስታወት ጌታነህ ወ/የስ ናቸው።

ታራሚዎቹ ከ17 ዓመታት በላይ በእስር መቆየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምጽ ተናግረዋል።

የሲቪልና ፖለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ቃል ኪዳን፤ ማንኛውም የሞት ቅጣት የተፈረደበት ሰው ይቅርታ የመጠየቅ ወይም የሞት ቅጣቱ ወደ እስራት እንዲቀየርለት የመጠየቅ መብት እንዳለው ይደነግጋል። በተጨማሪም በሁሉም ጉዳዮች ይቅርታ ወይም ምህረት ማድረግ ወይም የሞት ቅጣቱን ወደ እስራት ቅጣት መለወጥ ይቻላል ይላል።

የሞት ቅጣቱ እንዲፈጸምባቸው የጠየቁት እስረኞቹ ፤ የሞት ፍርዱ ወደ ቁጥር እስራት እንዲቀየር ቢያመለክቱም ምላሽ እንዳላገኙ ነው ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምጽ የገለፁት ።

ታራሚዎቹ ፤ አሁን ላይ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በሚሰጠው ምህረትና ይቅርታ ተጠቃሚ አለመሆናቸውንና ነገ የሚሉት ተስፋ እንደሌላቸው በመግለጽ የሞት ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅን በደብዳቤ ጠይቀዋል።

በይቅርታና በምህረት ተጠቃሚ ካለመሆናቸውም በላይ በማረሚያ ቤቱ የሚቀርበው ምግብና ያለው አያያዝ አስከፊ በመሆኑ በሕይወት ከመቆየት መሞትን መምረጣቸውን ገልጸዋል።

በወሎ ግንባር ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ የተላለፈው መመሪያ  ተግባራዊ ሆኖ መዋሉን የወልድያ ፣ የመርሳ ፣ የሀይቅ እና የደሴ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ  ገለፁ።ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ትናንት ...
19/08/2024

በወሎ ግንባር ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ የተላለፈው መመሪያ ተግባራዊ ሆኖ መዋሉን የወልድያ ፣ የመርሳ ፣ የሀይቅ እና የደሴ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ትናንት በወሎ ግንባር የሚገኘው የፋኖ እዝ ከአምቡላንስ በስተቀር ሌላ ተሽከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ ያወረደውን መመሪያ ተከትሎ በዋና ዋና አውራ ጎዳናዎች የነበረው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ተገትቶ መዋሉን ነው የገለፁልን።

በከተማ ውስጥ ለውሰጥ አገልግሎት የሚሰጡ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ግን አገልግሎት ሲሰጡ ውለዋል።

ይሁን እንጂ ከኮምቦልቻ እስከ ደሴ ያለው አውራ መንገድ ለተሽከርካሪዎች ክፍት እንደነበር የደሴ እና የኮምቦልቻ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ ቢልልኝ ባዩ በፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ ተወሰደ ። ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባልታወቁ የፀጥታ ኃይሎች በኃይል ታፍኖ መወሰዱን የዐይን እማኞች ለአማራ...
17/08/2024

ጋዜጠኛ ቢልልኝ ባዩ በፀጥታ ኃይሎች ታፍኖ ተወሰደ ።

ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ ቦሌ አራብሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባልታወቁ የፀጥታ ኃይሎች በኃይል ታፍኖ መወሰዱን የዐይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የአዲስ አበበባ ፖሊስ ሰሌዳ የለጠፈ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ድንገት ወርደው በኃይል ገፍተው እንዳስገቡት በስፍራው ነበርኩ ያሉ አንድ የዐይን እማኝ ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

ቢልልኝ ባዩ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ውስጥ ለአምስት አመታት ያህል በሪፖርተርነት ፣ በፕሮግራም አቅራቢነት እና የዜና መሪ( አንከር) ሆኖ አገልግሏል።

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈፅሙትን ጭፍጨፋ ሲያጋልጥ መቆየቱም ይታወሳል።

የአማራ ብሔር ንቅናቄን( አብን) ወክለው የአማራ ክልል ምክር ቤት  እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሀብታሙ በላይነህ ዛሬ የት እና በምን ሁኔታ እንደቆዩ እንዳይናገሩ በማስጠንቀ...
14/08/2024

የአማራ ብሔር ንቅናቄን( አብን) ወክለው የአማራ ክልል ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሀብታሙ በላይነህ ዛሬ የት እና በምን ሁኔታ እንደቆዩ እንዳይናገሩ በማስጠንቀቂያ ከእስር መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ አቶ ሀብታሙ የት እና በምን ሁኔታ ስድስት ወራትን እንደቆዩ ከመናገር ተቆጥበዋል ። ስድስት ወራት አፍኖ ያቆያቸው የአገዛዙ የፀጥታ ኃይል ስለቆይታቸው ምንም ነገር እንዳይናገሩ አስጠንቅቆ እንደላካቸው ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል

ሰሞኑን የአማራ ድምፅ አቶ ሀብታሙ በአገዛዙ በፀጥታ ኃይሎች ከተወሰዱ ስድስት ወራት እንዳለፋቸው እና እስካሁን የት እንዳሉ እንደማይታወቅ መዘገባችን ይታወሳል።

የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ከስልጣናቸው ተነሱ በሚል የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች በአደባባይ ደስታቸውን ሲገልፁ ማምሸታቸውን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ገለፁ ።  ይሁ...
13/08/2024

የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ከስልጣናቸው ተነሱ በሚል የጋምቤላ ከተማ ወጣቶች በአደባባይ ደስታቸውን ሲገልፁ ማምሸታቸውን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ ገለፁ ።

ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንቱ ከስልጣናቸው ይነሱ አይነሱ እስካሁን በግልፅ የታወቀ ነገር የለም የሚሉት ነዋሪዎቹ ፣ የከተማዋ ወጣቶች በተሽከርካሪ በመታገዝ ደስታቸውን ሲገልፁ ማምሸታቸውን ተናግረዋል።

ይህንኑ ተከትሎ የጋምቤላ ከተማ ከክልሉ የፀጥታ ኃይል ውጭ በአገዛዙ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ጥበቃ ስር መሆኗን ከስፍራው የደረሠን መረጃ ያመላክታል።

አሰግድ መኮነን የት እንደገባ አለመታወቁ እንዳሳሰባቸው  ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ገለፁ።የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ  ዋና አዛዥ አሰግድ መኮንን ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም  በአገዛዙ እጅ ከወደቀ ...
13/08/2024

አሰግድ መኮነን የት እንደገባ አለመታወቁ እንዳሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ገለፁ።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና አዛዥ አሰግድ መኮንን ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም በአገዛዙ እጅ ከወደቀ በኋላ እስካሁን የገባበት አለመታወቁን የገለፁት ቤተሰቦቹ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል ወደተባሉት የመንግስት ተቋማት በአካል ተገኝተን ብንጠይቅም አድራሻውን ልናገኝ አልቻልንም ብለዋል።
ይሁን እንጅ አንዳንድ የመከላከያ አዛዦች በግላቸው ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ቢነግሩንም የት እንደሆነ ግን ከመግለፅ ተቆጥበዋል ይላሉ።

በአገዛዙ ቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ በመንግስት መገናኛ ብዙኃንበራሱ አንደበት አዲስ አበባ መምጣቱን የገለፀ ቢሆንም የት እንዳረፈ እና በየትኛው ተቋም እጅ እንደሚገኝ የተገለፀ ነገር የለም።

አሰግድ መኮንን ከሰሜን ሸዋ ወደ ደቡብ ወሎ ሲጓዝ ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም ድንገት በአገዛዙ እጅ መውደቁ ይታወቃል ።

በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የቆሰሉ ፋኖዎችን አክመዋል በሚል አንድ የህክምና ባለሙያ መታሰራቸውን  የዐይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ። ሰማው ታከለ የተባሉት  የህክምና ባለሙያ አርብ ነ...
12/08/2024

በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የቆሰሉ ፋኖዎችን አክመዋል በሚል አንድ የህክምና ባለሙያ መታሰራቸውን የዐይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ገለፁ።

ሰማው ታከለ የተባሉት የህክምና ባለሙያ አርብ ነሐሴ 3 /2016 ዓ/ም ሠራዊቱን ሲዋጉ የቆሰሉ ፋኖዎችን አክመዋል በሚል በአገዛዙ ሰራዊት ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን ነው የዐይን እማኞች የተናገሩት።

አቶ ሰማው ታከለ የ72 አመት የእድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ በወልድያ ከተማ በግል የህክምና ክሊንክ ከፍተው ህዝብን እያገለገሉ ይገኛል ።

በዘመነ ኢህአዴግ ወቅት የግንቦት ሰባት አባል ነህ በሚል በተደጋጋሚ ለእስር መዳረጋቸውን የቅርብ ጓደኞቻቸው ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት ሀብታሙ በላይነህ የት እንደ ገቡ ሳይታወቅ ስድስት ወር ሞላቸው።  የአማራ ብሔር ንቅናቄን (አብን) ወክለው  የአማራ ክልል ምክር ቤት  እና የፌዴሬሽን ም...
12/08/2024

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት ሀብታሙ በላይነህ የት እንደ ገቡ ሳይታወቅ ስድስት ወር ሞላቸው።

የአማራ ብሔር ንቅናቄን (አብን) ወክለው የአማራ ክልል ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ሀብታሙ በላይነህ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ታግተው ከተወሰዱ ስድስት ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን የት እንደገቡ አልታወቀም።

የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የፌዴራል ፍትሕ ሚኒስቴር ስለ ሀብታሙ ቢጠየቁም የምናውቀው ነገር የለም ማለታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ከተወሰዱ ጀምሮ ለስድስት ወራት ያህል በየ እስር ቤቱ ብንጠይቅም አየሁ የሚል ተቋም አላገኘንም ይላሉ የሀብታሙ ቤተሰቦች።

ገድለውትም ከሆነ ሞቷል ብለው ቢነግሩን አንድ ነገር ነው የሚሉት የሀብታሙ ቤተሰቦች በበህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይቀር ስለ ሀብታሙ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ሳይሰጡ ማለፋቸው ምናልባት አቶ ሀብታሙን ገድለዋቸው ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ገብቶናል ይላሉ ቤተሰቦቻቸው።

መንግስት አለ ተብሎ በሚነገርበት አገር ህዝብን ወክለው በሁለቱም ምክር ቤቶች አባል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ሀብታሙ በላይነህ የካቲት 22/2016 ዓ/ም ጧት ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከታፈኑ በኋላ አድራሻቸው ሲጠፋ በእጅ ስልካቸው ሲደወል ስልኩ እንደማይነሳ እና ስልኩ በሚጠራበት ሎኬሽ ሲፈተሽ ግን አዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ እንደሚያመለክት ቤተቦቻቸው ማረጋገጣቸውን ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

"የምሽግ ጨዋታ"በሚል ጀግና ሴት የግንባር  ፋኖዎች ጋር  ስንጨዋወት ወለናል። የአማራ ድምጽ በተደጋጋሚ ከዩቱብ እንዲወርድ መደረጉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ "የአማራ ዜና አገልግሎት" በሚል አ...
18/05/2024

"የምሽግ ጨዋታ"በሚል ጀግና ሴት የግንባር ፋኖዎች ጋር ስንጨዋወት ወለናል።

የአማራ ድምጽ በተደጋጋሚ ከዩቱብ እንዲወርድ መደረጉ ይታወቃል። ይሁን እንጂ "የአማራ ዜና አገልግሎት" በሚል አዲስ የዩቱብ አካውንት ከፍተናል። በእየለቱ ይከታተሉ።

Share and subscribe!!

#የአማራዜናአገልግሎት

Address

Addis Ababa

Telephone

+17207207808

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when The Voice of Amhara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to The Voice of Amhara:

Share