Abs news ethiopia

Abs news ethiopia News,

13/06/2023

ቤተል ዛጎራ ሆቴል ጋር ላይ መኪና ተሰርቆብናል አፋልጉን
♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️♦️

ታርጋ ቁጥር 89680 አ አ ፣ ኮድ 3 አይሱዙ መኪና ትላንት ምሽት ቤተል ዛጎራ ሆቴል አካባቢ ከቆመበት ተሰርቆብናል፣

መኪናውን ያየ በስልክ ቁጥር 0982546530 አይሻ ወይም በስልክ ቁጥር 0916821642 በመደወል እንድትጠቁሙን እንለምናል ፣

ሼር ሼር ሼር በማድረግም ተባበሩን‼️

ጥቆማውን በዚህ ፔጅ በውስጥ መልዕክት ማስቀመጥም ይቻላል

ስለምትተባበሩን እናመሰግናለን 🤗

07/06/2023

የአዲስ አበበ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኢማሞች ህብረት የተሰጠ የአቋም መግለጫ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ በመቃወም በአዲስ አበባ ከተማ በታላቁ አንዋር እና ኑር መስጅዶች ህዝበ-ሙስሊሙ ድምፅ በማሰማቱ ምክንያት በተከሰተዉ ችግር በሰዉ ሕይወት እና አካል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎች በህግ ጥላ ስር ይገኛሉ፡፡
በሸገር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘዉ የመስጆዶች ፈረሳ ፍፁም ተገቢ ባለመሆኑ የምናወግዝ መሆኑን እየገለፅን የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የኢማሞች ሀብረት ጥያቄውን ያቀርባል፣
በተጨማሪም የኢማሞች ሀብረት በሸገር ከተማ እየተፈፀመ የሚገኘዉን የመስጅድ ፈረሳ እና ከዚህ ጋር በተያያዘ በምዕመናን ላይ የተወሰደዉን ተገቢ ያልሆነ እርምጃ በፅኑ እያወገዘ የሚከተሉትን ባለ 5 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡
1. ከዛሬ ቀን ጀምሮ እስከ ዙልቂዕዳ ወር መጨረሻ ድረስ በሁሉም መስጅዶች ቁኑት እና ዱዓ አንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣
2. በሁሉም መስጂዶች የፊታችን ጁሙዓ የኩጥባ ይዘት በሠላም፣ በአንድነት እና በሰብር ላይ እንዲያተኩር እና ህብረተሰባችን ይበልጥ በሚረዳው በአማርኛ ቋንቋ ዳዕዋ እንዲደረግ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
3. በነገዉ እለት ሐሙስ ዙልቂዕዳ 19 ፤ 1444 ዓ.ሂ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመፆም፤ በሰደቃ፣ በዱዓ እና በኢስቲግፋር ወደ አላህ በመቃረብ እና አላህ የተፈጠረውን ችግር እንዲያነሳልን እንዲለምን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
4. በተፈጠረዉ ችግር ሕይወታቸዉ ያለፈ እና የተጎዱ ቤተሰቦችን ሙስሊሙ ማህበረስብ የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባዘጋጀው የባንክ ቁጥሮች እንዲረዳ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፡፡
5. በመጨረሻም የጁምዓ ሰላታችን በሠላም ተሰግዶ አንዲጠናቀቅ እና ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲመለስ ጥሪያችንን እያቀረብን አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ የመጣውን በላእ እንዲያነሳልን እና እንዲመልስልን እንለምነዋለን፣

አላሁ አክበር !!!

03/06/2023

ይህ ወንድማችን አንዋር ይባላል።ከ4 ቀን በፊት ሸሂድ አላህ እንዲያደርገውና ከሞትኩም እድለኛ ነኝና ማንም እንዳያዝን ብሎ ነበር።መንግስትም ያፈረሳቸውን መስጂዶች መልሶ እስኪሰራቸው ድረስ እንታገለዋለን ብሎን ነበር።

03/06/2023

ስንቱን በልተው የስንቱን ለጋ እድሜ ቀምተው የስንቱን ወላጆች ልብ አድመተው የስንቱን ህልም በቀብር ላይ እንዲያልፍ አድርገው እነሱ ስንት አመት እንደሚኖሩ አብረን እናያዋለን። ሰላማዊዮን ህዝብ ነው በግድ ጦርነት ካልገጠማችሁኝ ብለው እራሳቸው ነገር የፈለጉት። ጦርነት ለፈለገ ግን ወደ ጉጅ ወይም ወደ ምዕራብ ወለጋ ብቅ ቢል አፍንጫቸው ስር ሽምቅ ተዋጊ አለላቸው ነበር። በድሀ ላይ ሁሉም ጀግና ነው። ድሀን ድሮም የተሸነፈ ነው። አንደኛ ድሀ ነው። ሁለተኛ ደካማ ነው። ሦስተኛ ምንም ቢደረግ ምን ያመጣል? ድሀን ብትገለው ብታፈናቅለው ብትዘርፈው ብትሰድበው ምንም አያመጣም። የዚህ መንግስት ትልቁ ጀግንነት እመሀል ከተማ ውስጥ ያለን ድሀ ማሸነፍ ነው። ለዚህ ነው በድሀ ጠንካራ ሆኖ የታየው። በገዛ እጃቸው ፍፅም ከዕውቀት ነፃ በሆነ የአስተዳደራዊ ፖሊሳቸው አለም እየሳቀባቸው ዞረው ምንም ብቃት የለለውን የስለላና የፖሊስ ሀይላቸው ጠንካራ እንዲመስል ሀሰተኛ ዶክመንተሪኢ እየሰሩ ሙድ የሚያዝባቸው።

በዚህ ቅፅፈት ቢሊዮን ዶላር በህገወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ነው። እርግጠኛ ነኝ አሁን በዚህ time ወደጅቡቲ በህገወጥ መንገድ ወርቅ ተጭኖ
እየሄደ ነው። እና የቱ የስለላ ሀይላቸው ነው የሚይዘው የቱ ፖሊሳቸው ነው የሚያድነው.? የለም። ምክኒያቱም በብቃት የተመለመለ ሀይል የላቸውም። በብሄር በአደግዳጊነት የተመለመለ ማዋቅር ነው ያላቸው። አይማሩም እንጅ ልክ እንደዮንቨርቲ ሆነን ሁሉንም ነግረናቸው ነበር።

ለማንኛውም ሟቹ ወንድማችን አንተና የመሰዋት ጓደኞች አብራችሁ ምህረቱን ይስጣችሁ። ለቤተሰቦቻችሁ መፅናናትን እመኛለሁ።

ሱሌማን አብደላ

❤❤❤❤❤
01/06/2023

❤❤❤❤❤

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይሆናል፦የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላ...
01/06/2023

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ወቅታዊ ጉዳይን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይሆናል፦

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፈረሱ 19 መስጂዶች አስመልክቶ ግንቦት 19/2015 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በጉዳዩ ዙሪያ በሰፊው በመወያየት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ይሄው፦
1. ከፌ/እ/ጉ/ጠ/ም/ቤት፣ከኦሮሚያ እ/ጉ/ከ/ም/ቤት እና ከአዲስ አበባ እ/ጉ/ከ/ም/ቤት የተውጣጡ 9 ዓባላት ያሉት ኮሚቴ ማዋቀሩ የሚታወቅ ነው

2. ጠቅላይ ም/ቤታችን በተዋቀረው ኮሚቴ አማካኝነት ከፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተጠናከረ ሁኔታ እየተወያየን መሆኑን ህዝበ ሙስሊሙ እንዲገነዘብ እናሳውቃለን፡፡ይህንንም ተከትሎ ማህበረሰባችን የጀመርነው ውይይት እልባት እስከሚያገኝ በትእግስት እንዲጠባበቅ

3. የኦሮሚያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ያውጠው መግለጫ ፍፁም ሙስሊሙን ማህበረሰብ የማይመጥን ስለሆነ ጠቅላይ ም/ቤታችን የማይቀበለው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

4. በአሁኑ ወቅት የተከሰተውን የመስጂዶች መፍረስ ከላይ በተጠቀሱት ሁኔታዎች ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ አንዳንድ አካላት ጉዳዩን ለፖለቲካ አላማቸው መጠቀሚያ ለማድረግ እየሞከሩ ስለሆነ ህዝበ ሙስሊሙ ይህንን በመገንዘብ አላማቸው በመጥፎ ጎኑ እንዳይጠቀሙበት ሰላሙን አጠናክሮ የጠቅላይ ም/ቤታችንን ውሳኔ እንዲጠባበቅ እየጠየቅን ከእንደዚህ ዓይነት ችግሮች እራሱንና ተቋሞቹን እንዲከላከል በተለመደው ጨዋነትና እስላማዊ አደብ በተላበሰ መልኩ ከማንኛውም ህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ተቆጥቦ የጠቅላይ ምክር ቤቱንና የ9ኙን ኮሚቴ ውጤት እንዲጠባበቅ አንጠይቃለን ሲል ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዘግቧል።
ምንጭ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት

01/06/2023
ዛሬ አንዋር መስጂድና በተለያዩ አካባቢዎች በነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ ከተጎዱት በርካታ ሰዎች የአንድ ሰው ህይወት ሊያልፍ ችሎዋል።
26/05/2023

ዛሬ አንዋር መስጂድና በተለያዩ አካባቢዎች በነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ ከተጎዱት በርካታ ሰዎች የአንድ ሰው ህይወት ሊያልፍ ችሎዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abs news ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share