Adis Tube

Adis Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Adis Tube, Media/News Company, Addis Ababa.

 #አዲስአበባ በልማት ጎዳና ላይ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💚💛❤ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
16/03/2023

#አዲስአበባ በልማት ጎዳና ላይ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💚💛❤ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ  የተቋማዊ ሪፎርም የዲጂታል ቴክኖሎጂ  መተግበሪያ ዘመናዊ ሕንፃ  እና ሌሎች የ90 ቀን ፕሮጀክቶች  ዛሬ ይመረቃሉ።      🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹   💚💛❤️  🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹በከን...
10/03/2023

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የተቋማዊ ሪፎርም የዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ዘመናዊ ሕንፃ እና ሌሎች የ90 ቀን ፕሮጀክቶች ዛሬ ይመረቃሉ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💚💛❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
በከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፍ እና ክትትል ሲደረግባቸው የነበሩ የተቋማዊ ሪፎርም የዲጂታል ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ዘመናዊ ሕንፃ እና ሌሎች የ90 ቀን ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ዛሬ ይመረቃሉ።

ከሚመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የለሚ ኩራ የቴክኖሎጂ ማዕከል ህንጻ ፥ G+4 የመኖሪያ ቤቶች፣ ሞዴል ጤና ጣቢያዎች፣የውሃና የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ እና መሰል ፕሮጀክቶች ይገኙበታል፡፡

በ 14-05-2013 ዓ.ም ለምረቃ ዝግጁ የነበረው የክፍለከተማ አስተዳደሩ ሕንፃ እና በሕንፃው ውስጥ ዝርጋታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ በሆኑ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶች ላይ በተከሰተው እሳት ጉዳት ደርሶ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ይሁን እንጂ በእሳት አደጋው ጉዳት ደርሶበት የነበረው ሕንፃ እና የቴክኖሎጂ ልማት ለሕዝብ በተገባው ቃል መሰረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የመልሶ ግንባታ ፥ጥገናና የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ዝርጋታው በአፋጣኝ እንዲስተካከል ተደርጎ ለሕዝብ አገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ90 ቀናት የተገነቡ ሁሉም ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ከመንግስትና ከባለሃብቱ በተገኘ የበጀት ድጋፍ የተገነቡ ናቸው።

ኢትዮዽያዊነት በተግባር የታየበትና: በዝቅታችን ወቅት ከፍታን ያየንበት ተግባር ነበር። ለኮሜዲያን እሸቱ: ለደጉ ቢንያም እና ተሳታፊውን በሙሉ አለማመስገን ንፉግነት ነው።     🇪🇹🇪🇹🇪🇹  ...
08/03/2023

ኢትዮዽያዊነት በተግባር የታየበትና: በዝቅታችን ወቅት ከፍታን ያየንበት ተግባር ነበር።

ለኮሜዲያን እሸቱ: ለደጉ ቢንያም እና ተሳታፊውን በሙሉ አለማመስገን ንፉግነት ነው።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

"ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ !!"- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት መልዕክት ፦"ለቦረና ህዝብ ያሰባሰብነውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት...
28/02/2023

"ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ !!"

- ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስተላለፉት መልዕክት ፦

"ለቦረና ህዝብ ያሰባሰብነውን ከ250 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ ለክልሉ መንግስት አስረክበናል::

በተለያዩ ግዜያት ከህዝብ ጎን በመቆም የሚታወቁ የከተማችን ባለሃብቶች ፣ ያስተባበራችሁ አመራሮች እንዲሁም የህብረተሰብ ክፍሎች ለቦረና ህዝብ ላሳያችሁት አለኝታነት እና ፍቅር ከልብ አመሰግናለሁ::

በቀጣይም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት እየሰራቸው ያለውን ስራዎች ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚደግፍ ለማሳወቅ እወዳለሁ።"

 #አብያችን   ዛሬም አኩርቶናልበዓለም አደባባይ ዛሬም በፊታውራሪነት ደምቋል  💚💛❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹  💚💛❤️የተስፋችን ምክንያት የሆነው  #አብይ ከአፍሪካ ምርጥ መሪዎች መሃል ግንባር ቀደሙ ለ...
24/02/2023

#አብያችን ዛሬም አኩርቶናል
በዓለም አደባባይ ዛሬም በፊታውራሪነት ደምቋል
💚💛❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💚💛❤️
የተስፋችን ምክንያት የሆነው #አብይ ከአፍሪካ ምርጥ መሪዎች መሃል ግንባር ቀደሙ ለመሆን ችሏል
OPEN Magazine እንዳወጣው መረጃ African Democratic Leaders ውስጥ #አብይን በአንደኝነት አስቀምጦታል ።
ለዚህ ክብር ያበቃው ብሎ ዶ/ር #አብይ የሰራቸው ስራዎች ሲጠቅስ
✔️ገበያ ተኮር የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣
✔️ወደ ግል የተዘዋወሩ የመንግስት ኢንተርፕራይዞች እና ✔️ሳቢ የሆነ የውጭ ኢንቨስትመንት በመተግበሩ ነው ብሎ አትቷል

👉 ከዚህ በተጨማሪም የተፈጥር ሀብት እንክብካቤ ላይ የሰራው ስራ ለዓለም ትልቅ ትምህርት መሆን የቻለ ታላቅ ድል የተመዘገበበት ስራ መሆኑንም ያትታል።

👉የታላቁ ህዳሴው ግድብንም አበቃለት ከተባለበት አዘቅጥ ውስጥ አውጥቶ ያለ ማንም ዕርዳታ ሊያገባድደው ከጫፍ መድረሱን የአፍሪካዊያን ታላቅ ድል ነው ብሏል።

👉 ስለ Green Legacy አንስቶም ታላቅ ስራ መሆኑን በስፋት አትቶለታል።
👉 አጠቃላይ የሀገሪቱን GDP ማሳደግ መቻሉን፣ Export ላይ ትልቅ ስራ ሰርቶ ማሳደግ መቻሉን፣ import መቀነስ እና ብዙ ብዙ #የአብይን ድሎች አትቶ አስቀምጧል።

እናም #አብይ ምርጡ የአፍሪካ መሪ ሲል በዓለም አደባባይ አወድሶታል‼️
#አብይ ዛሬም አንገታችንን አቀናልን🙏 በእሱ አፍረን አናውቅም ፤ ድል ነው ቀለቡ!!

የወጣውን ብርሀን ችላቹ ላታጨልሙት ለማደብዘዝ አትጋጋጡ! ፈቀደህለት ያልበራን ስላልፈለክ አታጨለምውም በ4ኪሎ መዝነህ በዙፋን ልክ አስበህ ግዙፉን ሰው ለመጣል መጋጋጥ የሚያመጣውን ውርደት እነ...
24/02/2023

የወጣውን ብርሀን ችላቹ ላታጨልሙት ለማደብዘዝ አትጋጋጡ! ፈቀደህለት ያልበራን ስላልፈለክ አታጨለምውም በ4ኪሎ መዝነህ በዙፋን ልክ አስበህ ግዙፉን ሰው ለመጣል መጋጋጥ የሚያመጣውን ውርደት እነ ጠይቃቸየው‼
🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
#ከፍታ
#ኢትዮጵያ
#ድል
#ሰውየው💪💪💪
Ⓒ Moha

22/02/2023

አዉቶቢሶችን 3.8 ቢሊየን ብር አዉጥቶ መግዛት ለምን አስፈለገ?

17/02/2023


የአፍሪካውያን አህጉራዊ ትብብር ለአፍሪካ ብልጽግና!
16/02/2023

የአፍሪካውያን አህጉራዊ ትብብር ለአፍሪካ ብልጽግና!

" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል " - ቅዱስ ሲኖዶስ    💚💛❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹  💚💛❤️ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጥ የተወሰደ ፦" ... በዛሬው ዕለት...
16/02/2023

" ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል " - ቅዱስ ሲኖዶስ
💚💛❤️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💚💛❤️
ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ውስጥ የተወሰደ ፦

" ... በዛሬው ዕለት የቤተ ክርስቲያን ጸሎቷ፣ ሐዘኗና ጩኸቷ ተሰምቶ ወደ ነበረችበት ልዕልናዋና አንድነቷ ተመልሳለች፡፡ ይህ አንድነቷና ልዕልናዋ እስከ ዓለም ፍጻሜ ተጠብቆ ይኖራል፡፡

በቅርቡ በቤተ ክርስቲያናችን ተከስቶ የነበረው ችግርም በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተፈትቷል፡፡
.. በችግሩ አፈታት ወቅት መንግሥት በተለይም ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ፖለቲካዊ ችግሩን በፖለቲካዊ መንገድ ከመፍታታቸውም ባሻገር የቤተ ክርስቲያን ችግር በቀኖናና በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት እንዲፈታ ታላቁን አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀደም ሲል ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ በማድረግ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አሁንም የቤተ ክርስቲያን አንድነት ተጠብቆ እንዲኖር ላደረጉት መልካም ተግባር ቤተ ክርስቲያን ከልብ ታመሰግናለች፡፡
.. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሦስቱ አባቶች መመለስ ታላቅ ደስታ ተሰምቷታል፡፡ ካህናት፣ ምእመናን በሀዘናችን ተካፋይ የነበራችሁ በሙሉ የዚህ ደስታ ተካፋዮች በመሆናችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ቅድስት ቤ ክርስቲያን ደስታዋን ትገልጻለች፡፡ "

"ምሁራን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ለሉዓላዊነቷ እና ለዘላቂ ሰላሟ ተገቢውን ሚና መጨዋት አለባቸው። የሁላችንም ችግሮች የሚፈቱት በሁላችንም የትብብር ትግል ነው። ዕውቀትና ዐዋቂ ...
07/12/2022

"ምሁራን የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በመገንዘብ ለሉዓላዊነቷ እና ለዘላቂ ሰላሟ ተገቢውን ሚና መጨዋት አለባቸው። የሁላችንም ችግሮች የሚፈቱት በሁላችንም የትብብር ትግል ነው። ዕውቀትና ዐዋቂ የሚከበርበት ማኅበረሰብ ለመገንባት እንድንችል መንግሥት እና ምሁራን ተቀራርበው ለአንድ ሀገር መሥራት አለባቸው።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adis Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share