Goffa Media Network - ጎፋ ሚድያ ኔትወርክ

Goffa Media Network - ጎፋ ሚድያ ኔትወርክ በ ብሮድካስት ሚድያው ዘርፍ ትልቅ ህልም ሰንቆ በመመስረት ላይ ያለ የሚድያ ተቋም።

07/03/2025
ገራሚ የሆነ የበቆሎ ገንፎ በተፈጨ ሥጋ እና ቦሎቄ  በአንድ ወገን ሌላው ዲሽ የበቆሎ ገንፎ አብሽ በቅቤ እኔና ባዮ  ሰርተን ምሳችንን አጣጣምን
25/08/2023

ገራሚ የሆነ የበቆሎ ገንፎ በተፈጨ ሥጋ እና ቦሎቄ በአንድ ወገን ሌላው ዲሽ የበቆሎ ገንፎ አብሽ በቅቤ እኔና ባዮ ሰርተን ምሳችንን አጣጣምን

እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት የሆነችው ትርፍ አምራቿ የጎፋ ዞን➖➖➖➖➖➖➖➖➖የጎፋ ዞን አድስ በሚመሠረተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ ዞኖች አንዱ ሲሆን ዞኑም በ 7 ወረዳዎች እና በ4 የከ...
15/08/2023

እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ባለቤት የሆነችው ትርፍ አምራቿ የጎፋ ዞን
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
የጎፋ ዞን አድስ በሚመሠረተው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካሉ ዞኖች አንዱ ሲሆን ዞኑም በ 7 ወረዳዎች እና በ4 የከተማ አስተዳደሮች የተዋቀረ ነዉ፡፡

የጎፋ ዞን አጠቃላይ የቆዳ ስፋት 4 ሺህ 551 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ሲሆን፣ የዞኑ ጂኦግራፍያዊ አቀማመጥ፣ በሰሜን ከደቡብ ምዕራብ ክልል ዳውሮ ዞን እና ከኮንታ ዞን ፣ በደቡብ ከደቡብ ኦሞ ዞን እና ከጋሞ ዞኖች ፣ በምስራቅ ከዳውሮ ዞን እና ከጋሞ ዞን፣ በምዕራብ ከደቡብ ኦሞ ዞን እና ከባስኬቶ ልዩ ወረዳ ጋር ይዋሰናል፡፡

የዞኑ መቀመጫ የሣውላ ከተማ ከአምስት በላይ የመውጫና የመግቢያ በር ያላት ሲሆን ከተማዋ ከአዲስ አበባ በ 526 ኪ.ሜ፣ ከሀዋሳ 300 ኪ.ሜ፣ ከወላይታ ሶዶ 135 ኪ.ሜ፣ ከአርባምንጭ 151 ኪ.ሜ፣ ከደቡብ ኦሞ ጂንካ ከተማ 99 ኪ.ሜ ፣ ከላስካ 53 ኪ.ሜ እንዲሁም ከማጂ 220 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች።

የጎፋ ዞን የጎፋ ፣ የኦይዳ እና የሌሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች መኖሪያ ሲሆን በዞኑ ዉስጥ በዋናነት ከሚነገሩት ቋንቋዎች መካከል ጎፊኛ፣ ኦይዴኛ እና አማርኛ በስፋት ከመነገራቸዉ በተጨማሪም የሌሎችም ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎች ይነገሩበታል፡፡

በዞኑ ከጎፋ እና ከኦይዳ ብሔረሰቦች በተጨማሪ ለሎች በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረዉ፣ ተዋደዉ ፤ በአንድነት ተቻችለዉ የሚኖሩበት የአብሮነት ተምሳሌት እና ሕብረብሔራዊነት ከሚታይባቸዉ ዞኖች መካከል የጎፋ ዞን አንዱ ነዉ፡፡

የጎፋ እና የኦይዳ ብሔረሰቦች የራሳቸዉ የሆነ የማንነት መገለጫዎች ቋንቋ ፣ ባሕል ፣ ታሪክ እና ወግ ያላቸዉ ሲሆኑ ዘመናዊ የአስተዳደር ሥርዓት ወደ አከባቢዉ ከመምጣቱ በፊት የራሳቸዉ የሆነ ጠንካራ ሀገረሰብ ባሕላዊ የአስተዳደር ሥርዓት የነበራቸው ፣ ከአፄ ሚኒልክ የግዛት ማስፋፊያ
ዘመቻ በኋላም ወደ ማዕከላዊ መንግሥት ከተካለሉ በኋላ በሀገር አንድነት እና ለዓላዊነት ላይ ከፍተኛ
መስዋዕትነት የከፈሉ ሕዝቦች ናቸዉ፡፡

የጎፋ ዞን ሕዝቦች ኑሮሯቸዉን መሠረት ያደረጉት በግብርና ሥራ ላይ ነዉ፡፡ አጠቃላይ የጎፋ ዞን ሕዝብ ብዛት ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

መልከዓ ምድሩንም ስንመለከት ሁሉንም የተፈጥሮ ዓይነቶች የታደለች ለእርሻ ሥራ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለቱሪዝም ኢኮኖሚ በጣም ማራኪ እና ለኑሮም ምቹ የሆነ ነው፡፡

የዞኑ ከፍታ ከባሕር ጠለል በላይ በአማካይ 1 ሺህ 976 ሜትር ከፍታ ያለው ሲሆን በዞኑ በርካታ የቱሪዝም መዳረሻዎች ይገኛሉ ከእነዝህም ውስጥ በጎፋ እና በጋሞ ዞኖች አዋሳኝ ላይ የሚገኘው የማዜ ብሔራዊ ፓርክ ፣ የሳኣ ጉልኣ ተራራ ፣ የአልባ ዙማ ተራራ ፣ የብልቦ ፍልውሃ ፣ የቱሩሞ ዋሻ እና ፏፏተ ሌሎች የቱሪዝም መስህቦችና የተለያዩ ማዕድናት ይገኛሉ።

በዞኑ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርቡ በርካታ የግብርና ምርቶች የሚመረቱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በቆሎ፣ የጎፋ ቡና ፣ ኮረሪማ ፣ አሪቲ ፣ ዝንጀብል ፣ ሰሊጥ ፣ ማሾ እና ሌሎች በርካታ ምርቶች ሲመረቱ በአትክልት እና ፍራፍሬም የሙዝ ፣ የማንጎ ፣ አቮካዶ ፣ አናናስን ጨምሮ ሁሉም የሚገኙባት ድንቅ ዞን ነች።

በቁም እንሰሳት ምርት በርካታ ኮርማዎች ፣ ሰንጋዎች ፣ ፍየሎች እና በጎች ለሀገር ውስጥ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ ታቀርባለች።

በታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የተከበበች ሲሆን ከእነዚህም በኢትዮጵያ በግዝፈቱ 2ኛ የሆነው የኤሌክትርክ ኃይል ማመንጫ የኮይሻ ፕሮጀክት ተጠቃሾች ነው።

በአጠቃላይ ለዓይን ታይተው በማይጠገቡ የተፈጥሮ ስጦታዎች የተከበበች ለኑሮ ምቹ የሆነች ለምለም የምድር ገነት የሆነች ሥፍራ መሆኗን ያዩ ሁሉ መስክረውላታል።

!

13/08/2023

💪

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Goffa Media Network - ጎፋ ሚድያ ኔትወርክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Goffa Media Network - ጎፋ ሚድያ ኔትወርክ:

Share