Tour Gurage

Tour Gurage የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራት ነው

አቶ ጌታቸው ረዳ የስምረት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
25/10/2025

አቶ ጌታቸው ረዳ የስምረት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

በጉራጌ ዞን የመስህብ ሥፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ የተጀመሩ ተግባራት ውጤት እያመጡ ነው ጥቅምት 5/2018 (ወልቂጤ )  በጉራጌ ዞን የቱሪዝም መስህብ ሥፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወ...
15/10/2025

በጉራጌ ዞን የመስህብ ሥፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ የተጀመሩ ተግባራት ውጤት እያመጡ ነው
ጥቅምት 5/2018 (ወልቂጤ ) በጉራጌ ዞን የቱሪዝም መስህብ ሥፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት ውጤት እያመጡ መሆኑን የዞኑ ባሕልና የቱሪዝም መምሪያ አስታወቀ ።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ መሠረት አመርጋ፤ ዞኑ ካላው እምቅ የቱሪዝም አቅምና መዳረሻዎች አንፃር ይገኝ የነበረው ጥቅም አነስተኛ ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን መቀየር የሚያስችል ሥራ በተቀናጀና ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በዞኑ ያሉ የተፈጥሮ፣ ሰው ሰራሽና እና ታሪካዊ የመሥህብ ሥፍራዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል ።

በተለይም በዞኑ ያሉ የቱሪዝም መሥህቦችን ለማስተዋወቅ እና ለማስጎብኘት ከግሉ ዘርፍ፣ ከመገናኛ ብዙኃንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ውጤት እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በዘንድሮው የመስቀል በዓል ከሃገር ውስጥ እና ከተለያዩ ዓለም ሃገራት በርካታ ጎብኚዎች ወደ ዞኑ መምጣታቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም 230 ሚሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን አንስተዋል ።

ከውጭ የሚመጡ ጎብኚዎች የ"ጀፎረ" የገጠር ኮሪደር ልማት ላይ የብስክሌት ሽርሽር ማድረግ እየተለመደ መምጣቱ እና በየአካባቢውም የሕዝቡ እንግዳ ተቀባይነት የቱሪስቱን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም እያስቻለ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

በዚህም የእደ ጥበብ ወጤቶች ተፈላጊነት መጨመር እና ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት መነቃቃት መፍጠሩን አውስተው፤ ለቱሪስቶች ማረፊያ የሚሆኑ የሆቴሎችና ሌሎች አመቺ ሥፍራዎችን የማስፋፋት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን ገልጸዋል።

ዞኑ በዘርፉ ካለው አቅም አንጻር ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ ያነሱት ሃላፊዋ፤ ለዚህም ይረዳ ዘንድ አዳዲስ የመሥህብ ሥፍራዎችን የማልማትና የማስተዋወቅ እንዲሁም መሰረት ልማት የማሟላት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል
መረጃው የኢዜአ ነው

02/10/2025

02/10/2025

ወገን መረጋጋት ሳይሻል አይቀርም

የ2018 የዳመራ በዓል ወልቂጤ
26/09/2025

የ2018 የዳመራ በዓል ወልቂጤ

24/09/2025


እንግዶቻችን ወደ ከተማቸው ወልቂጤ በሰላም እየገቡ ነው!! የጉራጌ ዞን ዋና ከተማና የጉራጌዎች ቤት ወልቂጤ ከተማ እንግዶቿን ከወትሮው በተለየ መልኩ እየተቀበለች ትገኛለች!!ተጓዦች ከኦሮሚያ ...
24/09/2025

እንግዶቻችን ወደ ከተማቸው ወልቂጤ በሰላም እየገቡ ነው!!

የጉራጌ ዞን ዋና ከተማና የጉራጌዎች ቤት ወልቂጤ ከተማ እንግዶቿን ከወትሮው በተለየ መልኩ እየተቀበለች ትገኛለች!!

ተጓዦች ከኦሮሚያ ክልል ጀምሮ እየተደረገላቸው ባለው አቀባበል መደሰታቸውና ቤታቸው ወልቂጤ ሲደርሱ ደግሞ የተለየ ስሜት እንደተሰማቸው እየገለፁ ይገኛሉ!!

“መስቀል በጉራጌ” ዓመታዊ ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ“መስቀል በጉራጌ” ዓመታዊ ፌስቲቫል ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።የመስቀል በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስ...
22/09/2025

“መስቀል በጉራጌ” ዓመታዊ ፌስቲቫል መካሄድ ጀመረ
“መስቀል በጉራጌ” ዓመታዊ ፌስቲቫል ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

የመስቀል በዓል በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበ የዓለም የማይዳሰስ ቅርስ ነው። የመስቀል በዓል ሐይማኖታዊ ሲሆን፤ በተለያዩ ማህበረሰቦች ዘንድ መንፈሳዊ ይዘቱን ሳይለቅ በባህላዊ ኩነቶች ጭምር ይከበራል።

መስቀል በጉራጌ በሥራ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ርቀው የሚኖሩ የሚገናኙበት፣ በቀዬአቸው የልማት አሻራቸውን የሚያኖሩበት ታላቅ በዓል ነው ሲሉ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገልጸዋል።

በአገር ቤትም ሆነ በከተማ የሚኖረው የጉራጌ ማህበረሰብ ለዘመናት ባዳበረው የገንዘብ እና የዓይነት የቁጠባ ሥርዓት ላይ ተመስርቶ ለወራት በበቂ ሁኔታ የሚዘጋጅበት በዓል መሆኑም አቶ ላጫ አንስተዋል።

እናቶች የመስቀል ቆጮ በመፋቅ እንዲሁም የቂቤ ‘ውጆ’ ወይም ዕቁብ በመሰብሰብ፤ ወንዶች የማገዶ እንጨትና የእርድ ከብት በማዘጋጀት፤ ወጣቶች በበኩላቸው ቤት እና አካባቢን በማስዋብ፣ ሚጥሚጣ በመውቀጥ እና ቤት በማስጌጥ የየድርሻቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አክለዋል።

የጉራጌ ማህብረሰብ የመስቀል በዓልን ከመስከረም 12 እስከ ጥቅምት 5 ቀን ቆጮ እና ክትፎን ጨምሮ ለበዓሉ ተብለው የተዘጋጁ ባህላዊ ምግቦችና መጠጦችን ከቤተሰብ እና ከጎረቤት ጋር በጋራ እየተቋደሱ ባህላዊ ጭፈራን ጨምሮ በልዩ ልዩ ክዋኔዎች በታላቅ ደስታ ያከብሩታል።

ይህን የመሰለ የማህበረሰብ እሴትን ለማልማትና ሳይሸራረፍ ለትውልድ ለማስተላለፍ የጉራጌ እና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር ጋር በመተባበር እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል

07/09/2025

Released the new song

07/09/2025

እንኳን ለ2018 በሰላም አደረሳችሁ

ባህላዊ የኢንጅነሪንግ ጥበብ የጉራጌ ጎጆ ቤት አሰራር የጉራጌ ብሄረሰብ እጅግ የሚደነቅ የበርካታ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ነዉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ ባህላዊ የሳር ቤት(ጎጆ ቤት) አሰራር አንዱ ነዉ፡...
03/09/2025

ባህላዊ የኢንጅነሪንግ ጥበብ የጉራጌ ጎጆ ቤት አሰራር

የጉራጌ ብሄረሰብ እጅግ የሚደነቅ የበርካታ ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ነዉ፡፡ ከዚህ ዉስጥ ባህላዊ የሳር ቤት(ጎጆ ቤት) አሰራር አንዱ ነዉ፡፡

በጉራጌ ብሄረሰብ የጎጆ ቤት ሥራ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን ተግባር ሲሆን አባቶች ዘመናዊ የምህንድስና ትምህርት ምን እንደሆነ ሳያዉቁ የሳር ቤት አወቃቀርና የመንደር አመሰራረት እንዲሁም የቤት አያያዝና አጋጌጥ እጅግ የሚገርም ነዉ።

የጉራጌ ባህላዊ ቤት አንዲት ሚስማር ወይም የፋብሪካ ዉጤት ሳይገባበት ተሰርቶ እስከ 100 ዓመት ምንም ሳይሆን አገልግሎት መስጠት እንደሚችል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የጉራጌ ባህላዊ ቤቶች በአራት ደረጃ የሚከፈሉ ሲሆን እነሱም ጎየ(ትልቅ ቤት)፣ ኸራር(እልፍኝ ቤት)፣ ዘገር(የሙሹሮች ቤት) እና አራተኛው ደረጃ ቀለል ባለ መልኩ የሚሰራ እና ለከብቶች ገለባ ማስቀመጫነት የሚያገለግል "ሰንቃላ" በመባል የሚታወቀው ነው።

የጎጆ ቤት የዉስጡን ገጽታ ስንመለከት የጉራጌ ባለሙያዎች ተጠበዉና ተጨንቀዉ በሚሰሯቸዉ የእደ-ጥበብ ዉጤቶች የሚያሽቆጠቁጡት ሲሆን በተለይም ከስንደዶ፣ ከሸክላ፣ ከእንጨት፣ እንሰት ዉጤቶች(ቃጫና ገመድ) በመጠቀም እንዲሁም ከእንስሳት ተረፈ ምርቶች ማለትም ከቆዳ፣ከቀንድ ፣ከጭራና ከመሳሰሉት የተዘጋጁ ቁሳቁሶች በአግባቡና በሚያምር መልኩ ተደርድረዉ አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ጥቅም ላይ ይዉላሉ፡፡

ጎጆ ቤት ሲገነባ በአንድ ጀንበር ታስቦ የሚከናወን ተግባር ሳይሆን ቤት የሚሰራዉ አባወራ ለቤቱ መስሪያ የሚሆኑ ቁሳቁስ ለማሰባሰብ ጊዜ ወስዶ የሚንቀሳቀስ ሲሆን የአከባቢው ህብረተሰብ ደግሞ አንድ አባወራ ቤት ሲሰራ ሌላው ዳር ሆኖ መመልከት የማይታሰብና እንደ ነዉር የሚታይ ስለሆነ ሁሉም ተረባርበዉ ቤቱን በጋራ መስራት የተለመደ ባህላዊ እሴት ነው።

በጉራጌ ባህል አንድ አባወራ ጎየ (ትልቅ) ቤት ለመስራት ሲያስብ የመጀመሪያ እርምጃዎቹ ለግንባታው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ከአካባቢው መሰብሰብ ነው። በዚህም መሰረት የበሰለ ቀይ በሀርዛፍ ወይም ጥድ መርጦ ለግድግዳ የሚሆኑ ቋሚ ፍልጦች(ጐርደራ) ማስፈለጥ፣ ለበር የሚቆሙ ዋና ቋሚዎች(ወፈንቻ) በሙያተኛ በወፍራሙ ማስጠረብ፣ ለቤቱ ጣራ መወጠሪያ የሚሆኑ ቀጥ ያሉ ረጃጅም ወራጆች ቆርጦ መሰብሰብ፣ ከወራጅ ጋር ከላይ ወደታች የሚደረደሩ ባሀርዛፎች በረዥሙ ጠርቦና ልጎ በብዛት ማዘጋጀት፣ ለቤቱ የውጭ ጣራና የውስጥ ጣራ መማገሪያ ቀርከሃ ሸንሽኖና ብዙ ቁጥር ያለው የዘንባባ ዛፍ ቅርንጫፍ በመመልመል ማዘጋጀት፣ ለጣራ ማሰሪያ የሚሆን የተመረጠ ገመድ (ወደረ) ለ2 ዓመት ያህል ጊዜ በመሰብሰብ በጥንቃቄ ማከማቸት፣ የውስጥና የውጪ ግድግዳ መማገሪያ ጌጠኛ ቀርከሃ እና የተጠረበ ማገር ገዝቶ ማከማቸት፣ የግድግዳ ማገር ማሰሪያ ጠንካራ ሀረግ(አብታ) ከጫካ በደቦ ማሰባሰብ፣ ቀጥና ዘለግ ብሎ የአንድ ጎልማሳ እቅፍ የሚሞላ የበሰለ ቀይ በሀርዛፍ ወይም የጥድ ዛፍ ለምሰሶ ማዘጋጀት፣ በላይኛው ጫፍና በመሀል የቤቱን ጣራ በመወጠር ለዓመታት የቤቱ ሚዛን እንዳይዛነፍ በምሰሶ ላይ ተተክለው ዙሪያውን የሚደግፉ ቀጥ ያሉና በሙያተኛ ተጠርበው ጌጥ የወጣላቸው ወጋግራዎች(ወካ) የማዘጋጀት ስራ ይሰራል፡፡

ከላይ ያየናቸው ቁሶችን የማሰባሰብ ስራ እንደተጠናቀቀ ቤቱ የሚያርፍበት የተመረጠው ቦታ (ሸመነ) የአካባቢው ህዝብ በጋራ ወጥቶ ውሀ ልኩን ያስተካክላል፡፡ የቦታው ውሀ ልክ መስተካከሉን ሙያተኛው እንዳረጋገጠ በራሱ መሪነት ግድግዳ ለማቆም ምሰሶ የሚቆምበት ቦታ የቤቱን መሐል በማድረግ ዙሪያውን በክብ ቅርፅ ይቆፈራል፡፡

የቤቱ የጣራ ግንባታ ተጠናቅቆ በወጋግራ (ወካ) እስከሚቀየር ድረስ ጣራው ከቤቱ በውስጠኛው በኩል ከመሬት ወደ ጣራው በሚወጠሩ ረጃጅም ወራጆች(ጡቃ) በጊዜያዊነት ይደገፋል። የጣራው ስራ እንደተጠናቀቀ በሙያተኛ አማካይነት መጠነኛ ውፍረት ያላቸው ቀጥ ያሉ የጥድ/ቀይ ባህር ዛፎች ተልገውና ተጊጠው በወጋግራነት (ወካ) በምሰሶው ወገብ ላይ ተተክለው የቤቱን ጣራ እንዳይዛነፍ ደግፈው እንዲይዙ የሚደረግ ሲሆን የውስጥ ስራ እንደተጠናቀቀ የቤቱ ጣሪያ በሳር ክፍክፍ ይከደናል፡፡

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tour Gurage posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tour Gurage:

Share