
17/10/2024
ሙሉ የመግለጫ ቃል!!
➢ ረቡዕ ጥቅምት 06/02/2017 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመንፈስ ልጆቻቸው መኖሪያ ቤት ይቆያሉ፤
➢ ከቀኑ 10፡00 እስከ 11፡00 ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ ርዕሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ወደተዘጋጀው የደብሩ ስብከተ ወንጌል የወልድ ዋሕድ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ማረፊያ ቦታ ይወሰዳል (ይጓዛሉ) ሌሊቱን በሰዓታት ጸሎት ሲታሰቡ ያድራል፤ ➢ ጥቅምት 7 እና ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 እስ ምሽት 1፡00 ሰዓት ድረስ በደሴ ከተማ ባሉ አብያተ ክርስቲያናት በሰዓታት እና በጸሎት ሲታሰቡ አድረው ይውላሉ!
➢ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም ለጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 10፡00 ድረስ የማህሌት ስነስርዓት በርዕሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ስብከተ ወንጌል ወልድ ዋሕድ ሰንበት ት/ቤት አዳራሽ የደሴ ከተማና ከተለያዩ ገዳማት በመጡ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን የማህሌት ሥነ ስርአት ይፈጸማል !
➢ የሀዘን መግለጫ እና የአበባ ጉንጉን በማቆያ ቦታ የማስቀመጥ መርህ ግብር ይክናወናል ➢ በተዘጋጀው የባህር መዝገብ ላይ የሀዘን መግለጫ በጽሑፍ እንዲቀመጥ ይደረጋል
> ከሌሊቱ 10፡00 አስከ 10፡30 አስከሬኑ በክብር ወደ ርዕሰ አድባራት ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ይገባና ጸሎተ ኪዳን ተደርሶ የቅዳሴ ስነስርዓት እስክ ማዳው 12፡00 ድረስ ይከናወናል፤
ጥቅምት 9/2017 ዓ.ም ክርዕስ አድባራት ደብረ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ከማለዳው 12:00 ጀምሮ እስከ ጧቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ በሊቃነ ጳጳላት፤ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ በአባቶች ካህናትና መዘምራን በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና በደሴ ከተማ አካባቢ ከተለያዩ ልዩ ቦታ በመጡ ህዝበ ክርስቲያንና ወዳጆቻቸው አማካይነት ታጅበው ወደ ደሴ ደብረ ቤቴል ቅ/ሥላሴና ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በሰልፍ ይደርሳሉ
> ከጧቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት የጸሎተ ፍትሐት በተመረጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መዘምራን ይካሄዳል!
➢ የህይወት ታሪክ፤ቅኔ፤ ትምህርተ ወንጌል የተለያዩ ባስልጣናትና የኃይማት መሪዎች ተወካይ የሐዘን መግለጫ እና የአበባ ጉንጉን ማስቀመጥ መርሀ ግብር ይከናወናል፣
➢ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 8፡30 ድረስ ጉዞ ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ተደርጎ ከቀነ- 8:30- 9:00 ስርዓተ ቀብሩ ይፈፀማል፡፡