DAF news

DAF news business

ሱራ የምወድህ እንኮን ደስ አለህ
09/01/2026

ሱራ የምወድህ እንኮን ደስ አለህ

የኢትዮ-ህንድ ግንኙነት በስትራቴጂክ አጋርነት አዲስ ከፍታ ላይ ደርሷል - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤር...
19/12/2025

የኢትዮ-ህንድ ግንኙነት በስትራቴጂክ አጋርነት አዲስ ከፍታ ላይ ደርሷል - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ እና ህንድ ግንኙነት በስትራቴጂክ አጋርነት አዲስ ከፍታ ላይ ደርሷል አሉ፡፡

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዚህ ሳምንት የሁለቱን ሀገራት ትብብር ለማጠናከር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ያደረጉትን የኢትዮጵያ ጉብኝት አስመልክቶ ከዲዲኢንዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናከረ ነው ብለዋል።

ይህም ሀገራቱ ያላቸውን የልማት ትብብር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ወደ ላቀ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ከፍ አድርጓል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ እና ህንድ ግንኙነት ከዲፕሎማሲ ባለፈ በታሪክ እና በባህላዊ ትስስር ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸው፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጉብኝት ግንኙነቱን ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያሳደገ መሆኑን ተናግረዋል።

ጉብኝቱ ለጋራ ልማት ጅምሮች አዳዲስ ዕድሎችን ይከፍታል ያሉት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፤ ትብብሩ በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና እና በቴክኖሎጂ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ህንድ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በግብርና ቴክኖሎጂ ያላት እውቀት ጠቃሚ የመማር እድሎችን እንደሚሰጥም አብራርተዋል።

ህንድ ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በተለይም ለእናቶች ጤና ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸው፤ ይህም የእናቶች እና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ፍሬያማ እንደነበር ገልጸው ይህ ጉብኝት መጨረሻ ሳይሆን የታደሰ እና የተጠናከረ አጋርነት መጀመሪያ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

This is the official Fana Media Corporation S.C (FMC) YouTube Channel - where you can get all the latest videos in Amharic, Afan Oromo, Tigrigna and Arabic.Y...

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱዳን መንግስት በፖርት ሱዳን ለሩሲያ የባህር ኃይል ማዕከል ለመስጠት የጀመረውን እንቅስቃሴ በታህሳስ 2025 መጀመሪያ ላይ በጊዜያዊነት ማቆሙ፣ ሀገሪቱ ያላትን ጂኦ-ፖለቲካ...
19/12/2025

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱዳን መንግስት በፖርት ሱዳን ለሩሲያ የባህር ኃይል ማዕከል ለመስጠት የጀመረውን እንቅስቃሴ በታህሳስ 2025 መጀመሪያ ላይ በጊዜያዊነት ማቆሙ፣ ሀገሪቱ ያላትን ጂኦ-ፖለቲካዊ አቅም ለመጠቀም ያደረገችው ስትራቴጂካዊ ስሌት እንጂ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እርምጃ እንዳልሆነ ተገለጸ።

በዛዊት እሸቱ እና ሱራፌል ተስፋዬ የተባሉ ተመራማሪዎች "Port Sudan on Hold: Russia, Bargains, and Sudan’s Marketplace of Survival" በሚል ርዕስ ባወጡት የትንታኔ ጽሑፍ፤ የሱዳን መሪዎች ውሳኔ ከምዕራባውያን እና ከሌሎች የዓለም ኃያላን ጋር ለመደራደር የተጠቀሙበት ስልት መሆኑን አብራርተዋል።

በሱዳን እና በሩሲያ መካከል ሊደረግ ታስቦ የነበረው ረቂቅ ስምምነት፤ ሩሲያ በቀይ ባህር ዳርቻ ለ25 ዓመታት የሚቆይ የባህር ኃይል ማዕከል እንድትገነባ የሚፈቅድ ነበር። በስምምነቱ መሰረት ሩሲያ የተወሰኑ መርከቦችን እና ወታደሮችን በስፍራው የምታሰማራ ሲሆን፣ በምላሹ ለሱዳን ጦር (SAF) አስቸኳይ የአየር መከላከያ እና የጦር መሳሪያ አቅርቦት እንድታደርግ ይጠበቅ ነበር።

ይሁን እንጂ ካርቱም ይህንን ስምምነት "በጊዜያዊነት" በማቆም፣ ሩሲያን ሳታስቀይም፣ በሌላ በኩል ደግሞ አሜሪካን እና የምዕራቡን ዓለም ትኩረት ለመሳብ እየሞከረች እንደሆነ ጥናቱ አመልክቷል።

ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት፣ ሱዳን አሁን ባለችበት ከባድ የርስ በርስ ጦርነት እና የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ፣ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ "የጦር ሜዳ ሎጂስቲክስ እና የኢኮኖሚ ህልውና" ጉዳይ ሆኗል። አሜሪካ በዲሴምበር 2025 ባወጣችው የብሔራዊ ደህንነት ስትራቴጂ አፍሪካን የስትራቴጂካዊ ፉክክር ሜዳ አድርጋ መፈረጅዋ፣ ለሱዳን መሪዎች ተጨማሪ የመደራደሪያ ካርድ ፈጥሮላቸዋል።

የሩሲያን ስምምነት በማዘግየት፣ ጄኔራል አል-ቡርሃን ከአሜሪካ እና ከባለጸጋ የባህረ ሰላጤ ሀገራት የተሻለ የዲፕሎማሲ፣ የኢኮኖሚ እና የማዕቀብ እፎይታ ድጋፍ ለማግኘት እየሞከሩ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ አካሄድ በሱዳን ፖለቲካ አዲስ እንዳልሆነ የጠቀሰው ጥናቱ፤ ከጃፋር ኒሜሪ እስከ ኦማር አል በሽር የነበሩ መሪዎች ስልጣናቸውን ለማቆየት ተመሳሳይ "ተለዋዋጭ ጥምረቶችን" ሲጠቀሙ እንደነበር አስታውሷል። የአሁኑም የጄኔራል አል-ቡርሃን እርምጃ፣ የአገሪቱን ስትራቴጂካዊ መልክዓ-ምድር ወደ "የሚሸጥ እና የሚለወጥ ንብረት" በመቀየር የሥልጣን ዕድሜን ለማራዘም የሚደረግ ጥረት እንደሆነ ተመራማሪዎቹ ድምዳሜያቸውን አስቀምጠዋል።

19/12/2025

በአሉላ ጉዳይ ያለኝ ሀሳብ የሚከተለው ነው። ጋዜጠኛ ነው። ማንችስተርን መደገፍ መብቱ ነው። ግን እንደ ጋዜጠኛ የግል ስሜቱን ከሞያው መቀላቀል የለበትም። በተለይ በተለይ ደግሞ ከአርሴናል ደጋፊዎች ጋር ተራ ብሽሽቅ ውስጥ መግባት የለበትም። ሲዲ ስፖርቶችም ይህን ባህሪውን እንዲያርቅ ሊያደርጉት ይገባል።

ለማንችስተር ያለውን ደጋፊነት የሌላውን ክለብ ሳይነካ (በወረደ ደረጃ ተራ ብሽሽቅ ውስጥ ሳይገባ) መግለፅ ይችላል። ለምሳሌ በብስራት ስፖርት ላይ ካስዬ የሊቨርፑል ደጋፊ ናቸው። በዳኝነት ላይ ኮሜንት ሲያደርጉ ለማንም አይወግኑም። አሉላ የስፖርት ጋዜጠኛ ነኝ ይላል። ነገር ግን እንደኛ ወርዶ ይበሻሸቃል። ባልደረቦቹ በርግጠኝነት የሚደግፉት ክለብ አላቸው። እነሱ ይህን የአሉላ ብሽሽቅ ይርቁታል። አሉላ ወርዶ ይበሻሸቃል። ይህ ተግባሩን አልወድለትም። የስሜት ብልህነት ይጎለዋል።

እኔ ለምሳሌ ጋዜጠኛ አደለሁም። መከረኛው አርሴናል እያልኩ አበሽቃለሁ። የአርሴናል ደጋፊዎች የመረረ ተቃውሞ አያሰሙብኝም። ብሽሽቃችን የፍቅር እንደሆነ አድርጌ ነው የምጫወተው። የአርሴናል ሀቅንም አልክድም። ጥሩ ሲሆኑ እየመረረኝም እመሰክራለሁ። ማንችስተር ሲንዘላዘል ቅጥል እያልኩ እፅፋለሁ። የማልደብቀው ነገር አርሴናል ሲሸነፍ ደስ ይለኛል። ልክ ቤተመንግስት ለእራት የተጋበዝኩ ያህል ፈካ እላለሁ (😂) ደጋፊዎችን አበሽቃለሁ። ግን ከልኩ ላለማለፍ እጠነቀቃለሁ። በአካል የማገኛቸው የአርሴናል ደጋፊዎች በብሽሽቃችን እንደሚዝናኑ ይነግሩኛል። ጥቃት ፈርቼ አላውቅም።

አሉላ ከጋዜጠኝነት እና ከተራ ተበሻሻቂ አንዱን መምረጥ አለበት። ይህን ብዬ ሳበቃ፣ የአርሴናል ደጋፊ እሱ እንዳለው አጥቅቶት ስልኩን ከወሰደበት ስህተት ነው። አካላዊ ጥቃት ድረስ መሄድ አያስፈልግም።

ኳስ እየተደሰትንበት በትዕግስት እና በመከባበር የምንዝናናው ነው። ልኩን አይለፍ እንጂ ብሽሽቅ ኳስን ያደምቃል። ለምሳሌ እኔ በኳስ ምክንያት ብሽሽቅ ፅፌ ሳበቃ ለምን ተሰደብኩ ብዬ አልበሳጭም። ስሜቱን የማይቆጣጠር ደጋፊ እንዳለ እረዳለሁ። ዛሬ ተበሳጭቶ ነገ ሊስቅ እና ሊያበሽቀኝ እንደሚመጣ አስባለሁ።

አሉላ ሀሳብ ያለው ጋዜጠኛ ነው። እርግጠኛ ነኝ ይህ ተራ ብሽሽቁን ከተወ የአርሴናል ደጋፊዎች አፉ ይሉታል። ብሔራዊ ቡድናችን ተሻሽሎ በጋራ የምንቆም ያድርገን።

ሰላም ለሀገራችን። ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር🙏

19/12/2025

የኦሮሚያ ክልል ከአማራ ክልል Amhara Revenue Bureau ልምድን ሊወስድ ይገባል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በክልሉ በየቦታው የተዘረጉ ህዝብን ለምሬት ኑሮን ለውድነት የዳረጉ የቀረጥ ኬላን ያነሳበት ቁርጠኝነት ለኦሮሚያ ክልል በመማሚያነት ሊቀርብ የሚገባው ነው።

የኦሮሚያ ክልል ሚኒሻ ከቀበሌ ከከተማ ሹም ጋር በጋራ መሳሪያ ይዞ እያስፈራራ ሾፌር እየደበደበ የተሽከርካሪ መስታውት እየሰበረ በማናለብኝነት ቀረጥ እያስከፈለ ያለበት ሂደት የህግ የበላይነት መላላት ማሳያ ምልክት ነው።

የፌደራሉ መንግስት የቀረጥ ኬልላዎች የመንግስት ፍላጎት ሳይሆን የግለሰቦች የግል ጥቅም ማጋበሻ ነው ባለበት ሂደት ኦሮሚያ ክልል ላይ ብዙ ቦታዎች ያልተነሱ ኬላዎች መታየቱ የሚያሳዝን የአዛዢ ታዛዢ ሰንሰለት መላላት የሚያመላክት ነው። ኦሮሚያ ክልል ከአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሊማር ይገባል።

Amhara Revenue Bureau በየቦታው ያልተነሱ እንደ ሞጣ ቁንዝላ ወልድያ ሊበን ያሉ ሌሎችም ቦታዎችን በማየት የማስነሳት ተግባሩን እንዲቀጥል እያሳሰብን ለስራችሁ ምስጋናን እናቀርባለን።

አንድ ሾፌር ኬላዎች በአማራ ክልል በመነሳታቸው ደስታን ሲገልፅ ከሁሉ ከሁሉ ቡሬ ላይ የነበሩ በዱላ ብዙዎቻችን የደበደቡ ኬላ ላይ የነበሩ ሚኒሻዎች መነሳታቸው ትልቅ ነገር ነው እንደ ጠላት ነበር የሚያዩን ነበር ያለ።

19/12/2025

ውድ የባንካችን ደንበኞች፡
******
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ መሠረት፤ ሁሉም የባንካችን ደንበኞች የባንክ አገልግሎቶች ለማግኘት እና ሒሳብ ለማንቀሳቀስ የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::

ስለሆነም እርስዎም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥርዎን በማቅረብ የባንክ ሂሳብ ቁጥርዎን ከፋይዳ መታወቂያዎ ጋር ያስተሳስሩ::

ስለትብብርዎ እናመሰግናለን።
******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

08/12/2025

በክልሉ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት( አፋሕድ) መካከል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ወገራ ወረዳና አካባቢው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የአፉሕድ አባላት እየገቡ ነው።

ስምምነቱን ተከትሎ ዛሬ ከገቡት 18 ባለመሳርያ 6 ጀሌ ሲሆኑ በድምር 24 አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ሌሎችም ለመግባት በመንገድ እንደሆኑ ማረጋገጥ ተችላል ሲል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

11/01/2025

ለነጋዴዎች እና ሱቅ ፈላጊዎች ፒያሳ ታክሲ ተርሚናል ፊትለፊት❗️

ፒያሳ ሀገር ፍቅር ቲያትር እና ሚኒሊክ አደባባይ መሀል የንግድ ሱቆች

* የግል የሚያደርጉት የንግድ ሱቆች ፒያሳ ላይ ብቸኛው እየሸጠ ያለው ቴምር ሪልስቴት ነው

* ሚኒሊክ አደባባይ ጋር በመንግስት የሚሰራው የ አውቶብስ እና የታክሲ ተርሚናል አጠገብ

* በከተማው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚደረግበት ቦታ ከተማው ላይ ሱቅ የፈረሰባቸው ነጋዴዎች የከተሙበት

* 4700 ካሬ ላይ ያረፈ ዘመናዊ እስኬሌተር የሚገጠምለት G+5 የሆነ የገበያ ማዕከል

* በ 1 ዓመት ከ 6 ወር የሚያልቅ ከፍለው እስኪጨርሱ በዶላርም ሆነ በግንባታ እቃዎች ግሽበት ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አይደረግም

* በወር ከ80,000 ብር በላይ የኪራይ ገቢ የሚኖራቸው

* ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ

ቴምር ሪልስቴት.......

ከሀገር ውጪ ለምትኖሩ ወገኖቻችን በሙሉ ካላችሁበት ሀገር ሆናችሁ ፕሮሰስ ማድረግ የምትችሉበትን እና መግዛት መዋዋል የምትችሉበትን መንገዶች አመቻችተናል!

ለበለጠ መረጃ በቀጥታ ወይም በዋትሳፕ ዋናው ቢሮ ይደውሉ

☎️ 0908770077
0967770077

ዋትሳፕ ሊንክ -

18/12/2024

የባንክ ስራ አዋጅ ቁጥር 1360/2017 ጸደቀ

- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መግለጫ

ባንኮች ከአገር ዉስጥና ከዉጭ አገር ገንዘብ በማሰባሰብና ለኢንቨስትመንትና ለልማት በማዋል እንዲሁም የክፍያ ሥርዓትንና የገንዘብ ፖሊሲን በማሳለጥ ለአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዓይነተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ከዚህም አኳያ የባንክ ዘርፍ ከሌሎች ዘርፎች በተለየ መልኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል የሚደረግበት ሲሆን ይህንንም ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ ጊዜዉን የዋጀ፣ ከዓለም ዓቀፍ ደረጃ እና አሰራር ጋር የተጣጣመ እንዲሁም የተሟላ የሕግ ማዕቀፍ በማዉጣት ተግባራዊ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ነዉ፡፡

ከዚህ አኳያ የባንክ ዘርፍን በዘመናዊ ዕዉቀት እና ቴከኖሎጂ ለመደገፍ፤ ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያለዉን ትስስር ለማጠናከር፤ የዘርፉን ተወዳዳሪነት፣ ዉጤታማነትና ቀልጣፋነት ለማሳደግ፣ በቂ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና የዉጭ ምንዛሪ አቅርቦት እንዲያድግ እንዲሁም ቀጣይነት ያለዉ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ እንዲያስችል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1360/2017 በኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጸድቋል።

ይህ ህግ ጸድቆ ትግበራ ላይ ሲውል በመሰረታዊነት ከዚህ የሚከተሉትን ዓላማዎች እንደሚያሰካ ይጠበቃል፡

አዳዲስ ባንኮች ወደ ባንክ ዘርፍ ሲቀላቀሉ ሊያሟሉ ስለሚገባዉ መስፈርት እና የፈቃድ አሰጣጥ ሂደት ለመወሰን

አደጋን መሠረት ያደረገ የተጠናከረ የቁጥጥር ሥርዓት ዘርግቶ ተከታታይነት ባለዉ አግባብ ተግባራዊ ለማድረግ፤

የሀገራችን የባንክ ዘርፍ ለዉጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ እና የዉጭ ባንኮች እና ኢንቨስተሮች በዘርፉ ተሰማርተዉ ለኢኮኖሚዉ ቀጣይ ዕድገት የበኩላቸዉን አበርክቶ እንዲሰጡ የሚያስችል የህገ ማዕቀፍ ለመዘርጋት፣እና

በአንድ ባንክ ላይ የፋይናንስ ቀዉስ በሚከሰትበት ጊዜ ባንኩ ከቀዉሱ እንዲወጣ እና እንዲያገግም ይህም ካልተቻለ በባንክ ዘርፍ እና በአጠቃላይ ኢኮኖሚዉ ላይ አለመረጋጋት ሳይፈጠር አንዲሁም የገንዘብ አስቀማጮች እና ሌሎች አበዳሪዎች ጥቅም ለከፍተኛ አደጋ ሳይጋለጥ የተለያዩ አማራጮች እና ስልቶችን በመጠቀም ባንኩ ከገበያ እንዲወጣ የሚደረግበትን ማዕቀፍ መዘርጋት ይገኙበታል፡፡

በመጨረሻም፣ ይህ አዋጅ የባንክ ዘርፍን የቀጣይ ዓመታት አሠራር የበለጠ ጤናማ እና የተረጋጋ እንዲሆን በማስቻል ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት መረጋገጥ የበኩሉን ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

Congratulations 🎆🎉The 47 president of USA 🇺🇸 Congratulated Donald J. Trump
06/11/2024

Congratulations 🎆🎉
The 47 president of USA 🇺🇸
Congratulated Donald J. Trump

Address

Kasanchis
Addis Ababa

Telephone

+251972183031

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DAF news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to DAF news:

Share