National tube

National tube Follow our media company

19/04/2022
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምዕራብ ኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ዘመቻንስፖንሰር ሲያደርግ!የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ዓላማ ያለው የእርቅ አካል ነ...
31/01/2022

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምዕራብ ኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ዘመቻን
ስፖንሰር ሲያደርግ!

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ዓላማ ያለው የእርቅ አካል ነኝ አለ፡፡

ነገር ግን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በህወሃትና ሼኔ ኦነግ የተከሰቱ የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች ዋና ስፖንሰር ሆኗል።

የተያያዘው ፎቶግራፍ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነኝ ብሎ የሚጠራው የሸኔ ኦነግ ታጣቂ ክንፍ በምዕራብ ኢትዮጵያ በUN መኪናዎች እየተጠቀመ ንፁሀን ወንዶችን ሴቶችን ህፃናትን በግፍ ሲጨፈጭፍ የሚያሳይ ነው።

ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ የፈፀመው ወረራ እና በአማራና አፋር ህዝብ ላይ የከፈተው የዘር ማጥፋት ጦርነት በWFP ስፖንሰርነት (ለWFP ለህወሓት ምግብ ሲያቀርብ እንደነበር) WHO, (ለWHO) ሳተላይት ሲያቀርብ እንደነበር በደንብ ይነገራል። ራዲዮዎች እና ከፍተኛ የመገናኛ መሳሪያዎች)፣ እና MSM (ለምዕራባውያን MSM የፕሮፓጋንዳ ፖርትሬይን እየመራ ነው ጨቋኙን እንደ
ተጠቂ አድርጎ። )

አቻምየለህ ታምሩ

22/01/2022

"የተከበራችሁ ውድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በአራዳ ክ/ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አጠገብ ፀብ አጫሪና አሳፋሪ ድርጊት እንዲሁም ከባህረ ጥምቀቱ ወደ ደብሯ በመመለስ ላይ በነበረችው በወይ ብላ ማርያም ታቦት በቡራዩ ከተማ አዋሳኝ አካባቢ የገጠማት መስተጓጎል እና ከዚሁ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው አለመግባባት ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የከተማ አስተዳደሩ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶታል፡፡

በዚህ ረገድ እንደ መንግስት የመንግስት አካላት ጥፋት የሆነውን ለይተን እርምጃ መውሰድ የጀመርን ሲሆን በቀረውም አጥፊዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ሃላፊነታችንን የምንወጣ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን፡፡"

አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር

22/01/2022

ሃይማኖትንና ሃይማኖታዊ በዓላትን መንግሥት የግጭት መነሻ ከማድረግ ይቆጠብ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ጭምር የምትታወቅበት በአብሮነት የመኖር፣ የመረዳዳት፣ የመተሳሰብ እና የመቻቻል ውብ የሆነው እሴታችን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመንግሥት መዋቅር ድጋፍ ጭምር ከፍተኛ አደጋ ውስጥ የወደቀ ሲሆን በዚሁ ከቀጠልን ደግፈው የያዙት ጠጠሮች ተበትነው እንደማኅበረሰብ አንድ አድርገው ያቆዩንን መልካም ወዳጅነት እንዳናጣ እንሰጋለን፡፡

የቀድሞው አገዛዝ በሕዝብ መራር ትግል እንዲያከትም ከተደረገ በኋላ በትረ ሥልጣኑን የያዙት አመራሮች ሀገራችንን ወደተሻለ ሰላም እና እድገት ያደርሷታል ተብሎ ቢጠበቅም እየተደረገ ያለው ግን ከሚጠበቀው በተቃራኒ እየሆነ በየቀኑ የምንሰማው በሙሉ አሳዛኝና አሸማቃቂ ከሆነ ከርሟል፡፡ ከጊዜ ጊዜ ይታረማሉ ተብለው የታሰቡ ጉዳዮችም ይልቅ ስር እየሰደዱ ለማኀበረሰባችን አብሮ መኖር እንቅፋት እየሆኑ የመጡ ሲሆን በፀጥታ እና የመንግስት መዋቅሮች የሚፈፀሙ ተግባራት ደግሞ ችግሩን የበለጠ እያወሳሰቡት ይገኛሉ፡፡

በትላንትናው ዕለት ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የቃና ዘገሊላ በዓል ሲከበር በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከሰንደቅ ዓላማ ጋር በተያያዘ ችግሮች ተፈጥረዋል፡፡ በተለይም የወይብላ ቅድስት ማርያም እና ታቦተ ቅዱስ ሚካኤል ወደ ቤተክርስቲያን በመመለስ ላይ ሳሉ የጸጥታ አካላት በፈጸሙት አላግባብ የሆነ ድርጊት ብዙ ሰዎች በመረጋገጥ፣ በድብደባ ጉዳት ሲደርስባቸው ቁጥራቸው በውል ያልተረጋገጠ የበዓሉ ታዳሚዎች ውድ ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ለማወቅ ችለናል፡፡

የኦሮሚያ የፀጥታ ዘርፍ አካላት ታቦታቱ እየተመለሱ ባለበት ወቅት ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ማለፊያውን መንገድ አጥረው በመያዝ ታቦታቱን ያጀቡ ምዕመናን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያለባቸውን ማንኛውንም ቁሶች (ግንባር ላይ የሚታሰር፣ እጅ ላይ የሚደረግ፣ የሴቶች የሀገር ባህል ቀሚስ ጥለት፣ ቲሸርት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን መገልገያ የሆኑ ከበሮዎችን) ይዘው እንዳይገቡ በመከልከላቸው ከፍተኛ የሆነ ችግር ተፈጥሯል፡፡ በዚህም ግጭት ሃይማኖታዊ በዓሉ በጸጥታ አካሎች ምክንያትነት ከመረበሹም በላይ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ሊደርስ ችሏል፡፡ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ጥፋት ያጠፉ አካላት ድርጊታቸው በአግባቡ ተጣርቶ እርምጃ ሳይወሰድባቸው በመቅረቱ ተመሳሳይ ጥፋቶች እንዲበራከቱ በር ከፍቷል፡፡ የፀጥታ ሀይሎች የሕዝብን ደሕንነት ከማስጠበቅ ይልቅ እራሳቸው ስጋት ከመሆን መታረም አለባቸው፡፡

ሀገራችንን ወደ ሃይማኖት ግጭት ለማስገባት ቀን ከሌት የሚጥሩ ኃይሎች በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ጭምር ተሰግስገው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አካላትን የሚቆጣጠር አቅም እና ፍላጎት ያለው ተጠያቂ የሆነ አመራር ባለመኖሩ ልንወጣው ወደማንችለው ችግሮች ውስጥ እየገባን እንገኛለን፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ይህን የመሸከም ጫንቃ የሌላት በመሆኗ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ለጠፋውም ጥፋት ይቅርታ ሊጠይቅ እንዲሁም ከቤተክርስቲያኗ ሀላፊዎች ጋርም በመምከር ችግሮች ዳግም እንዳይፈጠሩ ሊሰራ ይገባል፡፡ ይህም ጉዳይ እንደ ከዚህ ቀደም ኩነቶች እናጣራለን ተብሎ ብቻ የሚተው እንዳይሆን በፅኑ እናሳስባለን፡፡

ኢዜማ ይህን መሰል ችግር ድጋሚ እንዳይፈጠር በጋራ መሠራት እንዳለበት የሚያምን ሲሆን በዚህ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተፈጠረውን ችግር በጽኑ ያወግዛል፡፡ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ( #ኢዜማ)
ጥር 14 ቀን፣ 2014 ዓ.ም

21/01/2022
19/01/2022
04/01/2022
04/01/2022

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ነገ ኢትዮጵያ ትገባለች

ታኅሣሥ 26/2014 (ዋልታ) የሽብር ቡድኑን ትሕነግና የአጋሮቹን ወንጀል ለዓለም በማጋለጥና በመሟገት የምትታወቀው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ነገ ኢትዮጵያ እንደምትገባ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለ1 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጅ ዲያስፖራዎች ያቀረበውን የወደ አገር ቤት ግቡ ጥሪ ተከትሎ ነው ነገ ማለዳ አዲስ አበባ የምትገባው።

የሲቢኤስ ጋዜጠኛና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄርሜላ ከኢትዮጵያ አጀንዳነት ተሻግሮ ዓለም ዐቀፍ ንቅናቄ የሆነውን እምቢ ለባርነት ወይም የበቃ እንቅስቃሴን በማስጀመርም ትታወቃለች። #""

04/01/2022
03/01/2022

ሱዳን ያለ ውጪ ጣልቃ ገብነት የራሷን ችግር በራሷ መፍታት ይኖርባታል - የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ያለ ማንም የውጭ ጣልቃ ገብነት የራሷን ችግር በራሷ መፍታት እንዳለባት የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ በመግባት ሠላምና መረጋጋት ተስኗት በቀጠለችው ሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ስልጣናቸውን ለቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር አጋማሽ ከሌሎች ከፍተኛ ሹማምንትጋር በወታደራዊ ኃይሉ በቁም እስር ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ ኢትዮጵያ በጎረቤት ሀገር ሱዳን ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለች መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ሱዳናውያን ያሉባቸውን ልዩነቶች ያለማንም የውጪ ጣልቃ ገብነት በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ትሻለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሁልጊዜም የምትፈልገውና ማየት የምትሻው የሱዳንን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ነው ሲሉም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የሁለቱ ሀገራት የድንበር ጉዳይም በውይይት ብቻ እንደሚፈታ ከዚህ ቀደም ስትገልጽ መቋየቷን አስታውሰው አሁንም ይህንኑ አቋም ይዛ ትቀጥላለች ብለዋል።

ኢትዮጵያና ሱዳን አንድ ሕዝብ ነን፤ የፖለቲካ ድንበሩ ሰው ሰራሽ ነው፤ እኛ ለሚሰነዘሩብን ማንኛውም አይነት ጥቃቶችና ድርጊቶች አሉታዊ የአጸፋ ምላሽ መስጠት አንፈልግም ብለዋል።

ለዚህም አሁን በሱዳን ካለው አስተዳደር በተለይም በሽግግር መንግስቱ የወታደራዊ ክንፍ በኩል እኛን ለግጭት ለማነሳሳት ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ምላሽ ከመስጠት የተቆጠብነው ከዚህ ጉዳይ ጀርባ ሆኖ ግፊት የሚያደርገውን አካል ስለምናውቅ ነው ነበር ያሉት አምባሳደር ሬድዋን።

እ.አ.አ በ2019 የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሐሰን አል-በሽር ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ የፈጠረውን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህምድ አማካኝነት የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ወሳኝ ሚና ተጫውታለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when National tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share