Wollo Media Network WMN

  • Home
  • Wollo Media Network WMN

Wollo Media Network WMN This page will be the page of voicelesses of wollega peoples

በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት አንድ የረድዔት ሰራተኛው መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የነፍስ አድን ቡድን (ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ) ገለጸ።ተቋሙ በዚህ የአየር ጥቃት...
17/10/2022

በትግራይ ክልል ሽረ ከተማ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት አንድ የረድዔት ሰራተኛው መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የነፍስ አድን ቡድን (ኢንተርናሽናል ሬስኪው ኮሚቴ) ገለጸ።
ተቋሙ በዚህ የአየር ጥቃት የረድዔትሰራተኛውን ጨምሮ ሶስት ሰዎች መገደላቸውንም ቅዳሜ ጥቅምት 5፣ 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የጤናና የስነ ምግብ ቡድን አባል የሆኑት የረድዔት ሰራተኛው ለሴቶች እና ህጻናት እርዳታ እያቀረቡ ባለበት ወቅት በተፈጸመ ጥቃት ከቆሰሉ በኋላ ህይወታቸው አርብ ጥቅምት 4፣ 2015 ዓ.ም እለት ማለፉን መግለጫው አትቷል።
በዚህ ጥቃት ሌላ የአይአርሲ የረድዔት ሰራተኛ የቆሰሉ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ሰላማዊ ሰዎች እንደተገደሉና እንደቆሰሉ መግለጫው አክሏል።
ተቋሙ “የእርዳታ ሰራተኞች እና ሰላማዊ ዜጎች በፍፁም ኢላማ መሆን የለባቸውም” ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሽረ ከተማ ላይ ተፈጸመ በተባለው የአየር ጥቃት ላይ ምንም አይነት አስተያየት ባይሰጥም ከዚህ ቀደም ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ እንደማያደርግ መግለጹ ይታወሳል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ባሉባት ሽረና አካባቢው ባሉ በርካታ ግንባሮች ጦርነቱ እየተጠናከረ መምጣቱንም ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት ጦርነቱ እንዲቆም ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የትግራይ ኃይሎች ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ጦርና የኤርትራ ጦር በከተማዋ እና አካባቢው የከባድ መሳሪያ ድብደባና የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ነው ሲሉ ከሰዋል።
ይህንንም ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት ሰላማዊ ዜጎች ኢላማ መደረጋቸውን አውግዟል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፍ ቦረል “በሽረ የቀጠለው ጦርነት እንዲሁም ሰላማዊ ነዋሪዎች ኢላማ የመደረጋቸው ሪፖርት አስደንጋጭ ነው” ብለዋል ።
"እውነተኛ የሰላም ጥረቶች ወታደራዊ ጥቃቶች ወይም ትንኮሳዎቸ እንዳልሆኑ" በገለጹበት የትዊተር መልዕክታቸው "አለም አቀፉን ህግ ማክበር የሁሉም ግዴታ ነው" ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጦርነቱ መባባሱን በማስመልከት የተፈጠረባቸው "ከባድ ስጋት" ከገለጹ በኋላ ጦርነቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
"በሽረ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የፈጸሙት ሰላማዊ ሰዎችን ያልለየ ጥቃት አሳሳቢ ነው" በማለት የአሜሪካ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) ኃላፊ ሰማንታ ፓወር ተናግረዋል።
ሙሉውን ለማንብበ፦https://bbc.in/3eyNrfv

  - ሕወሃት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በትግራይ እየተካሄደ ላለው ጦርነት ባስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብየዋለሁ ሲል ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ...
17/10/2022

- ሕወሃት የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በትግራይ እየተካሄደ ላለው ጦርነት ባስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብየዋለሁ ሲል ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ዛሬ ባሰራጩት አዲስ መግለጫ፣ ሁሉም ወገኖች ባስቸኳይ እና ያለ ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንደገና እንዲጀምር እንዲያደርጉ እና በደቡብ አፍሪካ በሚካሄድ አፍሪካ ኅብረት-መራሽ የሰላም ንግግር ላይ ለመሳተፍ ቀደም ሲል የገለጹበትን ስምምነታቸውን በድጋሚ እንዲያረጋግጡ ጠይቀው ነበር። ፋኪ ከሳምንት በፊት "በሎጅስቲክ ምክንያት" ለሌላ ጊዜ ተላለፈ የተባለው ደቡብ አፍሪካ ላይ ሊካሄድ የነበረው የሰላም ንግግር ቀጠሮ፣ ወደፊት የሚካሄድበት ቀን ይወሰን አይወሰን ግን አልገለጡም።

ሕወሃት በዛሬው መግለጫው በመስከረም ወር መግቢያ ላይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ያቀረብኩትን ጥሪ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ ቢደግፉትም፣ ተጨባጭ ርምጃ ግን ሳይወስዱ ቀርተዋል በማለት ወቅሷል። "የሕወሃት ተቀዳሚ ዓላማ በትግራይ የሚካሄደውን ጭፍጨፋ እና የኤርትራ ሠራዊት ከሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች የትግራይ ሕዝብን መፈናቀል ማስቆም" እንደሆነ በሕወሃት መግለጫ ተጠቅሷል።

"ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ አሁን ያለው አማራጭ፣ ተኩስ እንዲቆም ማድረግ ወይም የትግራይ ሕዝብ ራሱን ከጥቃት እንዲከላከል መርዳት ነው" ያለው ሕወሃት፣ "ይህ ካልሆነ ግን የትግራይ ሕዝብ ሕልውናውን ለማስጠበቅ ውጊያውን ይቀጥላል" በማለት አስጠንቅቋል። ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ "የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ እንዲወጣ እንዲያስገድድ፣ ለተኩስ አቁም ተጨባጭ ርምጃዎችን እንዲወስድ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ድርድር ጠረጼዛ እንዲመጣ ግፊት እንዲያደርግ" ሕወሃት ጠይቋል[ዋዜማ]

16/10/2022

“ማረጋገጫ ከተሰጠን ጦርነቱን አቁመን ሀገር ለቀን ለመውጣት ዝግጁ ነው” የህወሃት አመራሮች

ጦርነቱ ወደ መገባደዱ መድረሱን ተከትሎ የህወሃት ቁንጮዎች አነጋጋሪ ውሳኔ ላይ እንደ ደረሱ ከውስጥ አዋቂ የሚመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከቀን ወደ ቀን፣ ከሰዓት ወደ ሰዓት የከበባው ቀለበት በሁሉም አቅጣጫ እየጠበበ መምጣቱን የተረዱት የህወሃት ሰዎች አለም አቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት መውጫ ካመቻቸልን ጦርነቱን ወዲያው አቁመን ከሀገር ለመውጣት ተዘጋጅተናል የሚል አቋም ላይ እንደደረሱና ይሄንንም አቋማቸውን በቴድሮስ አድሃኖም አማካኝነት ለአሜሪካና የአውሮፓ ህብረት ተደራሽ እንዳደረጉ ታውቋል። ዛሬ የአፍሪካ ህብረት ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ የህወሃት ሚዲያዎች በሙሉ ተኩስ አቁሙን እንደተቀበሉ ተደርጎ እንዲሰራጭ ከማዕከል ትዕዛዝ ተሰጥቷል።

ዛሬ ቴድሮስ አድሃኖም በርሊን ላይ ይህንኑ የህወሃት አመራሮችን ማስመለጫ መንገድ በተመለከተ ከተለያዩ ሰዎች ጋር እንደተነጋገረና በቀጣይ ቀናትም ወደ ብራሰልስ እንደሚጓዝ ይጠበቃል። ዛሬ በርሊን ላይ ካነጋገራቸው አካላት መካከል የአሜሪካ ሰዎችም እንደሚገኙበት ነው ጀርመን ካሉ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች የተረዳነው።

ጦርነቱ መቀልበስ የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ጠላትም ወዳጅም ተረድቷል። አሁን መፍትሄው፣ ውሳኔውም ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያ እጅ ነው። መከላከያ ሰራዊት ግዳጁን በሚገርም ኦፕሬሽን አፈፃፀም እየተወጣ ነው። ህወሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መወገዱ የማይቀር ብቻ ሳይሆን በጣም በፍጥነት የሚሆን ነገር መሆኑ ተረጋግጧል። ከአሁን በኋላ ከህወሃት በኋላ የሚኖረው የትግራይ ክልል አስተዳደርና የሰሜኑን የሀገራችን ክፍልን መልሶ ማቋቋም ላይ ትኩረት መደረግ አለበት!

( ሱሌማን አብዴላ )

16/10/2022

ፈተና ጥሎ የወጠው ተማሪ ቤት እንዳይገባ ተከለከለ
********************************
👉 ይህ የገጠር ቤተሰብ በድህነት ቤቱ፣ የቀን ስራ ሰርቶ ፣ አራጣ ተበድሮ ፣ እራፊ ልብስ ለብሶ፣ አንጀቱን አስሮ ያስተማረውን ልጁን '' በበሬ ወለደ '' ወሬ ተላላፊ በሽታ ፈተናውን ትቶ ወደ ቤተሰብ ትናንት ከምሽቱ 1:20 ይገባል

➢ የተፈታኝ ተማሪና የቤተሰብ ሀገር በደ/ጎ/ዞን ፎገራ ወረዳ ነው

---- ቃለ ምልልስ ---
➢ተማሪ - ሰላም ዋላቹህ ብሎ ከቤቱ በር ላይ ከወንድሙ ጋ በፍቅር ተሳስመው ውጭ ላይ አውርተው ወደ ቤት ይገባሉ
➢ ወንድም - አንተየ እንዴት ነው ረብሸው ኧረ እንኳን ፈጣሪ አወጣህ የእነ ታድሎ፣የእነ አሰፋ ልጆች ሁሉ መጥተዋል
➢ ተማሪ - አወ በጣም አስቸጋሪ ነበር በጣም ብዙ ተማሪ ሙቷል፣ ብዙ ሴት ተማሪ ተደፍሯል ፣ በጣም ብዙ ቁስለኛ ሞልቷል
➢ አባት - የክንዱ ልጅ ታዲያ አልወጣሁም ሰላም ነኝ እንዳታስቡ ብሎ ያስደወለ ያልወጣ አለ እንዴ
➢ ተፈታኝ ተማሪ - አወ የተወሰኑ ያልወጡ አሉ ዝም ብለው መሔጃ አጥተው ዛሬ ምሽትና አዳር እንዴት እንደሚሆኑ ፈጣሪ ይርዳቸው ግን ሁሉንም ገለዋቸው ነው የሚያድሩ
➢ እናት - ኧረ እንኳን በሰላም ወጣቹህ እነርሱንም እመቤቴ በሰላም ትጠብቃቸው

===== ከነጋ በኃላ ዛሬ ጧት ====

➢ አባት - ለስራ ወደ አጎቱ ልጅ ቤት ሒዶ ለሰኞ ያልኩህ ስራ እንደተጠበቀ ነው እያለ ሲያወራ ልጅህ በሰላም መጣ ይለዋል

➢ የአጎት ልጅ - ኧረ የእኔውኮ አልመጣም እየተፈተነ ነው ትናንት ማታ ደህና ነኝ ብሎ ደውሏል

➢ አባት - አንተ የእኛ ልጅማ ሁሉም ወጥቷል, የሞተ ፣የቆሰለ፣የተደፈረ ሁሉ አለ ብሎ ትናንት ከመሸ መጥቶ አይደል

➢ የአጎት ልጅ - ኧረ ሰነፉ ተማሪ ካልሰረቅን እኮ ብሎ ረብሻ አንስቶ ነው የመጣ እንጅ ጎበዙማ ቀርቷል

== በል ሰላም ዋል ተባብለው ከተለዩ በኃላ==

➢ አባት - ወደ ቤቱ ተመልሶ መጥቶ አዱኛ ብሎ ልጁን ጠረው

➢ ተፈታኝ ልጅ - አቤት ብሎ ወደ አባት ቀረበ

➢ አባት - ትናንት ፈታኝ ነው ያስረበሸን, የሞተ ፣የቆሰለ ፣ የተደፈረ አለ ሁሉም ወጥቷል የቀረ የለም ብለህ ነበር አይደል የእነ ክንዱ ልጆች እየተፈተኑ አይደል

➢ ተፈታኝ ተማሪ - እነርሱማ ዝም ብለው ነው ብሎ ተኮላተፈ

➢ አባት - ከዚህ በኃላ ድግም ከዝች ቤት አትገባትም ስንት መከረየን አይቸ አስተምሬ፣ አረም እንኳን ብቻየን ስማቅቅ ከርሜ አንተ በቀር ተማርኩ እያልክ መጫወቻ ታደርገኛለህ ብሎ ወደ ስረው

➢ ተፈታኝ ተማሪ - ጧት ተናዶ ከቤተሰብ ወጥቶ ሒዷል

2/2/2015 አ.ም
Derbew Ameshe
እየሆነ ያለው እንግዲህ ይህ ነው, ከባድ ነው!!
የድሃን ልጅ በቆሻሻ ፖለቲካ ከአላማ ውጭ ማድረግ የወደፊት እጣ ፋንታቸውን ጫኝ አውራጅ ያደረጋቸው የፌስታል ብሄርተኛው ነው ‼️

16/10/2022

ሰበር መረጃ አለማጣ
***************
ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ከአማራ ልዩ ሀይል እና ፋኖው ጋር በመሆን የራያዋን ኮከብ ከተማ አለማጣ ከደቂቃወች ቡሃላ ይረከባል። ከሌሊት ጀምሮ በከተማዋ ዙሪያ ከባድ ተኩስ የነበረ ሲሆን አሁን 5፡00 ላይ የከተማዋን ዙሪያ ይዞ እየጠዘጠዛት ይገኛል።

ከአበርገሌ የተነሳው ሀይላችን ኮረምን ቆርጦ የያዘ ሲሆን በእብሪት እምበር ተጋዳላይ ሲዘል የነበረው አንbeጣ ከመሀል ገብቶ እየተፈጨ ነው።

ይብላኝ የበሬ ቆለ... ይወድቃል ለመሰለው ለፌስታል ብሄርተኛው ኬንያ እና ዑጋንዳ ሲመላለስ ለከረመው።

ራያየ ከዘማሚት እና ቁጫጭ ነፃ የወጣች ሲሆን አሁን ደግሞ ትግራይን ከአንbeጣ ነፃ እናወጣለን። ኢትዮጵያም ከያዛት ጋንግሪን ትፈወሳለች !!!

16/10/2022

ከቆቦ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ‼️

የከተማችንን አሁናዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ የሰዓት እላፊ ገደብ በማውጣት የተለያዩ ክልከላዎችን ማስቀመጥ በማስፈለጉ የከተማ አስተዳደሩ የጸጥታ ምክር ቤት የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል።

1) በከተማችን ከምሽቱ 2:00 እስከ ጧቱ 12:00 ድረስ ማንኛውም የሰውና የተሽከርካሪ ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

2) ለግዳጅ የሚፈለጉ ተሽከርካሪዎችን አለመተባበር እና የተለያዩ ምክኒያቶችን በመደርደር ፍላጎት አለማሳደር በፍፁም የተከለከለ ነው::

3) ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም መጠጥ ቤቶች ምግብ ቤቶች የሻሂ ቤቶችና፣ ሆቴሎች ፣ ከተፈቀደለት ስአት ውጭ ቤት ከፍቶ ማስተናገድ የተከለከለ ነው::

4) ፀጉረ ልውጥ ሰዎችን ማሳደር ወይንም ለሚመለከተው ህግ አስከባሪ አካል ጥቆማ ሰጥቶ አለማሰያዝ የተከለከለ ነው ::

5) ማንኛውም የከተማችን ወጣቶች ለወገን ጦር እውነተኛ የኋላ ደጀን የመሆን ሎጀስቲክ እና ተተኳሺ የማቅረብ ግዴታ ዛሬ ስለአለበት ፣ ቆቦ ከተማ የሚገኝ ወጣት በሙሉ ቆቦ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ጽ/ቤት እየተገኛቹሁ ተመዝገቡ ፣

6) በማንኛውም የከተማችን ቤትና የንግድ ቤት ቁማር / ቢንጎ ; ካርታ ; / መጫወት ማጫወት ; የመጫወቻ ቦታ ማከራየት ; በፍጹም የተከለከለ ነው ::

7) በከተማችን ሁሉም የሚገኙ የመንግስት ተቋማት የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች እና የቀበሌ መዋቅር ከመቸውም ግዜ በበለጠ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ተደራሺ የሆነ ሙያዊና መንግስታዊ ሃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ አለበት::

😎 00 ባጃጂና ወደ ባጃጂ ማህበር አባል ያልገባ
ባጃጂ መንቀሳቀስ አይቻልም ::

9) ሆርን ኦፍ አፍሪካ ኤፍ ኤም 88.0 አሁን ላይ ስርጭት ስለጀመረ ከጧቱ 1:00-3:00 ቀን ከ6:00-80:00 ማታ ከ10:00- 12:00 በአማርኛ ; በትግርኛ ; ስለሚተላለፍ ትከታተሉ ዘንድ እናሳውቃለን ::

10) የሸቀጥ እቃወችን / ክብሪት ; ዳቦ እርሾ ; መድሀኒት ; ዘይት ; ስኳር; አረቂ ወዘተ/ ቦታ ማንቀሳቀስ ; ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ; ህገ-ወጥ ንግድ የተሳተፈ አካል በህግ ይጠየቃል ::

11)በከተማ አስተዳደሩ ጥይት የተኮሰ ያስተኮስ በተቀመጠው ውሳኔ መሰረት በህግ ይጠየቃል

12) በህዝብ መዝናኛ ቦታወች ; በገበያ ማእከል ; በሀይማኖት ተቋማት ; በሆቴልና ካፌ በመሳሰሉት ቦታወች ላይ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

ይህ ክልከላ አሸባረውን የትግራይ ወራሪ ሃይልን ቀብረን አማራን ከውርደት ኢትዬጲያንም ከብተና ለመታደግ የሚደረገው ትግል እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል:: ይህንን ውሳኔ የማያከበር ግለሰብም ሆነ ድርጅት ላይ የፀጥታ መዋቅሩ አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ጭምር በአጽእኖት እያሳወቀን ለክልከላው ተግባራዊነት ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ እናሳስባለን፡፡ ::

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ም/ቤት
05/02/2015
በቆቦ ከተማ

15/10/2022

ቻይና የተከተለችው “የዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ” ውጤታማ መሆኑን ገለጸች
October 15, 2022
በቤጂንግ ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ ምክንያት የሀገሪቱ የጋብቻና የወሊድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ይገለጻል
ቻይና በሰዎች ህይወት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ማንኛውንም ወረርሽኞችን በፍጥነት ለማስወገድ በሚል ተግባራዊ ያደረገችው የ“ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ” ውጤታማ መሆኑን ገለጸች፡፡
የገዥው ኮሚኒስት ፓርቲ ቃል አቀባይ ሱን ዬሊ በቤጂንግ እየተካሄደ ባለው የፓርቲውን 20ኛ ጉባኤ ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፤ “የቻይና የኮቪድ-19 እርምጃዎች ምርጡ፣ ወጪ ቆጣቢ ነው ስለዚህም በተሻለ መልኩ ይቀጥላል” ብለዋል።
“ብርሃን ከወዲፋታችን አለ እንዲሁም ጽናት ድል እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን” ሲሉም ነው ሱን በፈተናዎች የታጀበውን የቻይና ወቅታዊ ጉዞ የገለጹት፡፡
ሱን ዬሊ ይህን ይበሉ እንጅ ቻይና በጀመረችው የዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲዋ ከቀጠለች ከተቀረው ዓለም የተገለለች እንዳያደርጋትና ሌላ ችግር እንዳያስከትከል በርካቶች የሚያነሱት ስጋት ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የ“ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ” የጋብቻ እና የወሊድ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ አስተዋጽኦ እንዳደረገ የቻይና ብሄራዊ ጤና ኮሚሽን በቅርቡ አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ “ኮሮና ቫይረስ በአንዳንድ ሰዎች ጋብቻ እና ልጅ መውለድ ላይ ግልጽ ተጽዕኖ አሳድሯል” ብሏል።
ብዙ ሴቶች ለማግባት ወይም ልጅ የመውለድ እቅዳቸውን ማዘግየታቸውን ቀጥለዋል ያለው ኮሚሽኑ፤ በሀገሪቱ አየተስተዋሉ ያሉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገቶች ወደ "ጥልቅ ለውጦች" እያመሩ ነው ማለቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተጨማሪም የ“ዜሮ-ኮቪድ ፖሊሲ” የሀገሪቱ ዜጎች ልጅ የመውለድ ፍላጎት ላይ ከፍተኛና ዘላቂ ጉዳት ማድረሱን የስነ-ህዝብ ባለሙያዎች ሲናገሩ ይደመጣል።
ባለው ሁኔታ በቻይና ውስጥ አዲስ የሚወለዱ ህጻናት በዚህ ዓመት ወደ ዝቅተኛ ደረጃ ይወርዳልም ነው ያሉት ባለሙያዎቹ፡፡
ባለሙያዎቹ፤ “ ካለፈው ዓመት 10 ነጥብ 6 ሚሊዮን ህጻናት ጋር ሲነጸጸር ከ10 ሚሊዮን በታች ቅናሽ ያሳየ ሲሆን፤ ይህ ደረጃ በ2020 ከነበረው በ11 ነጥብ 5 በመቶ ያነሰ ነው” ብለዋል።
ቤጂንግ እንደፈረንጆቹ ከ1980 እስከ 2015 የአንድ ልጅ ፖሊሲን ተግባራዊ ባደረገችበት ወቀት የሀገሪ ህዝብ ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን ማመኗ የሚታወቅ ነው፡፡
ይህም ታዲያ ሀገሪቱ አረጋውያንን የመክፈል እና የመንከባከብ አቅሟን የሚፈትንና ቀውስ ሊስከትል የሚችል እንዳይሆን ተሰግቷል፡፡
ሁኔታው ያሰጋት ቻይናም ችግሩን ለመቋቋም በሚል በማዕከላዊና የተለያዩ ግዛቶች ባለስልጣናት አማካኝነት ከባለፈው ባለፈው አንድ አመት ጀምሮ እንደ የግብር እፎይታ፣ ረዘም ያለ የወሊድ ፈቃድ፣ የተሻሻለ የህክምና መድን፣ የመኖሪያ ቤት ድጎማ እና ለሶስተኛ ልጅ ተጨማሪ ገንዘብ የመሳሰሉ እርምጃዎችን ማስተዋወቅ ጀምራለች፡፡

ተመድ ሩሲያ የዩክሬንን ግዛቶች መጠቅለሏን ባወገዘበት ጉባኤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድምጸ ተዓቅቦ አደረጉየተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን በኃይል መያዟን በከፍተኛ ድምጽ ባወገዘበ...
15/10/2022

ተመድ ሩሲያ የዩክሬንን ግዛቶች መጠቅለሏን ባወገዘበት ጉባኤ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድምጸ ተዓቅቦ አደረጉ
የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን በኃይል መያዟን በከፍተኛ ድምጽ ባወገዘበት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካ አገራት የተከፋፈለ ድምፅ አሰምተዋል።

ሃያ ስድስት የአፍሪካ አገራት ሩሲያ በዩክሬን አራት ግዛቶች ላይ ያደረገችውን አወዛጋቢ ሕዝበ ውሳኔ እና ግዛቶቹን መጠቅለሏን በማውገዝ ድምፃቸውን አሰምተዋል።

ከዚህ ቀደም ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችውን ወረራ የሚያወግዘውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውሳኔ ውድቅ ያደረገችውን ኤርትራን ጨምሮ 19 አገራት ደግሞ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል።

ከእነዚህም መካከል የሩሲያ አጋሮች የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ ማሊ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ዚምባብዌን ጨምሮ ሌሎች አገራት ይገኙበታል።

ድምጸ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ሦስቱ የሩስያ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሰርጌ ላቭሮቭ ባለፈው ዓመት ሐምሌ ወር አገራቸው ከአፍሪካ አገራት ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር በሚል የጎበኟቸው ናቸው።

ላቭሮቭ ኢትዮጵያን ጨምሮ በግብፅ፣ በዲሞክራቲክ ኮንጎ እና በኡጋንዳ ጉብኝት አድርገው ነበር።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ በነበራቸው ጉብኝት ለዓለም አቀፍ የምግብ ዋጋ መናር እና ለነዳጅ ቀውስ ተጠያቂዎቹ ምዕራባውያን አገራት ናቸው ሲሉ ወቅሰዋል።
ላቭሮቭ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት አድርገዋል።

በያዝነው ወር የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሜትሮ ኩሌባ አህጉሪቷ በሩሲያ ላይ ያላትን ድጋፍ ለመሸርሸር እና መሪዎቹ ዩክሬንን እንዲደግፉ ለማሳመን በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ጉብኝት አድርገዋል።

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታደርገው የቦምብ ጥቃቶች መጠናከሩን ተከትሎ ጉብኝታቸውን ለማሳጠር ተገደዋል።

ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን እና ኢኳቶሪያል ጊኒ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጠቅላላ ጉባኤ ላይ አልተገኙም።

ውሳኔው በ143 አገራት ድጋፍ ሲያገኝ ቻይና እና ሕንድ ግን ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል።

ሩሲያን ጨምሮ አራት አገራት ደግሞ ውሳኔውን ባለመቀበል የተቃውሞ ድምጽ ሰጥተዋል። ከሩሲያ ጋር አብረው የቆሙት ቤላሩስ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሶሪያ እና ኒካራጉዋ ናቸው።

ሩሲያ የዩክሬንን ከወረረች ወዲህ በዚህን ያህል ድምጽ ተቃውሞ ሲገጥማት የመጀመሪያው ነው።

ባለፈው ሳምንት እጅግ በደመቀ ሥነ ሥርዓት ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን ሉሃንስክ፣ ዶኔስክ፣ ዛፖሪዥያ እና ኬርሶን የሩሲያ አንድ አካል እንዲሆኑ ፊርማቸውን ማኖራቸው ይታወሳል።

ሉሃንስክ፣ ዶኔስክ፣ ዛፖሪዥያንና ኬርሶን የምሥራቅ ዩክሬን ግዛቶች ነበሩ።

የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን በኃይል መያዟን በከፍተኛ ድምጽ ባወገዘበት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካ ሃገራት የተከፋፈለ ድምፅ አሰምተዋል። ሃያ ስድስት የአፍሪካ ሃገራ....

15/10/2022

የመጀመሪያዎቹ የሩሲያ ወታደሮች ለጋራ ወታደራዊ ኃይል ቤላሩስ ገቡ
October 15, 2022
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ “ሩሲያ ቤላሩስን በቀጥታ ወደዚህ ጦርነት ለመሳብ እየሞከረች ነው” ብለዋል
ከቤላሩስ ወታደሮች ጋር አዲስ የተቀናጀ ጦር ኃይል ይፈጥራሉ የተባሉት የመጀመሪያዎቹ የሩሲያ ወታደሮች ቤላሩስ መግባታቸውን የሚንስክ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጋራ ወታደራዊ ኃይል ተልዕኮ "የድንበርን ለማጠናከር ብቻ ነው" እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡
ወታደሮቹ ቤላሩስ ሲደርሱ ባህላዊ አልባሳት ለብሰው ዳቦና ጨው የሚያቀርቡ ሴቶች አቀባበል ሲያደርጉላቸውም ነው በሚኒስቴሩ በኩል የተለቀቁ ምስሎች የሚያሳዩት፡፡
የፑቲን የቅርብ ወዳጅ የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ “ዩክሬን በእኛ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እየተዘጋጀች ነው” ሲሉ ከቃናት በፊት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
በተጨማሪም ሉካሼንኮ ፖላንድን፣ ሊትዌኒያን እና ዩክሬንን የቤላሩስ አክራሪዎችን “የሽብር ጥቃቶችን ለመፈጸም እና በሀገሪቱ ውስጥ ወታደራዊ ጥቃትን ለማደራጀት” የሚያስችል ስልጠና እየሰጡ ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
ሉካሼንኮ ከሀገሪቱ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ስብሰባ "ዛሬ ዩክሬን እየተወያየች ብቻ ሳይሆን በቤላሩስ ግዛት ላይ ጥቃት ለማድረስ እቅድ እንዳላት አስቀድሜ ተናግሬያለሁ" ማለታቸውም ነው ቤልታ የተሰኘው የመንግስት የዜና ወኪል የዘገበው።
የሩሲያ ፌዴሬሽን እና የቤላሩስ ሪፐብሊክ ጥምር ጦር ለማሰማራት ከስምምነት መድረሳቸውም ተናግረው ነበር፡፡
እናም የአሁኑ የቤላሩስና የሩሲያ የጋራ ወታደራዊ ኃይል በዩክሬን ያለው ሁኔታ ይበልጥ እንዳያባብሰው ተሰግቷል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በቡድን-7 ጉባኤ ላይ ባሰሙት ንግግር “ሩሲያ ቤላሩስን በቀጥታ ወደዚህ ጦርነት ለመሳብ እየሞከረች ነው” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
በዩክሬን-ቤላሩስ ድንበር ላይ የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች ተልዕኮ እንዲደረግም ጠይቀዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
የቀድሞዋ የሶቪየት ህብረት አባል ሀገር የነበረችው ቤላሩስ ከዩክሬን ጋር ባለው ጦርነት ከሩሲያ ጎን ከቆሙ ሀገራት መካከል ብቸኛዋ ናት፡፡
ከቤላሩስ ውጪ ሁሉም የቀድሞዎቹ የሶቪየት ህብረት አባል ሀገራት ከሩሲያ በተቃራኒ ወይም ከምዕራባዊያን ጎን ተሰልፈው የተለያዩ እርምጃዎችን የወሰዱ ሲሆን የምዕራባዊያንን ማዕቀብ በማስፈጸም ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ ሞስኮ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ከመጀመሯ በፊት በነበሩት ወራት ውስጥ በወታደራዊ ልምምድ ሰበብ የሩሲያ ወታደሮችን ወደ ቤላሩስ እንዲገቡ የፈቀዱ መሪ ናቸው፡፡
ከጦርነቱ በኋላም ቢሆን በሩሲያ ላይ የሚቃጣ የትኛውንም ጥቃት ቤለሩስ እንደምትመክትና እንደምትከላከል በአደባባይ በመናገር ለፑቲን ያላቸው አጋርነት ያረጋገጡባቸው በርካታ አጋጠሚዎች ይታወሳሉ፡፡

15/10/2022

የመጨረሻውን መጀመሪያ የሚያበስሩ የተረጋግጡ የግንባር መረጃዎች

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና ጥምር ጦሩ በአሸባሪ ህወሓት ታጣቂ ላይ እየወሰዱት ባሉት ፀረ ማጥቃት እርምጃዎች የመጨረሻውን መጀመሪያ የሚያበስሩ የድል ዜናዎች እየተሰሙ ነው፡፡

✔ በደቡብ ግንባር በሰሜን ወሎ ግዳን ወረዳ ወትወት፣ ሲሞንዛ፣ ማሆጎ፣ጀመዶ፣ ግራኝ አገው እና ዶጊያት የነበረው የጠላት ጦር የተደመሰሰ ሲሆን፤ አሸባሪው ቡድኑ ቀሪ ኃይሉን ወደ አላማጣ አየር ማረፊያ እንዲሸሽ አድርጓል።

✔ በራያ አላማጣ ግንባርም ተሰልፎ የነበረው የጁንታው ታጣቂ ክፉኛ ተመትቶ ዋጃን እየለቀቀ እና ከአላማጣ ከተማ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ተበታትኖ ምሱን እያገኘ ነው፡፡

✔በሰቆጣ ግንባር ጥራሬ ወንዝ ማዶ ላይ በነበረው የጠላት ኃይል ላይ በተወሰደ የማጥቃት እርምጃ የአሸባሪው ታጣቂዎች ደቆል፣ ቆዝባ፣ መረዋ እና ዛታ ከተማዎችን ለወገን ጦር ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡

✔በምዕራብ ግንባር አዲአርቃይ ከተማን አልፎ መጥቶ በነበረው የጠላት ኃይል በደረሰበት ጠንካራ ምት ጠጣ፣ ሲምንዛ፣ አዲአርቃይ ከተማ፣ ጃማ ወንዝ፣ ማይለሃም፣ ማይቃጫን፣ ኮሎፊያን አባማር፣ አዲጉባይ እና ቡያን እንእንዲለቅና ወደ አቄስብሎ፣ ማይፀብሪ እና ዜሮ ዜሮ እንዲሻገር ተገዷል።

✔በሰሜን ምዕራብ የነበረው የአሸባሪው ኃይል ከአዲዳሮ ተገፍቶ ወጥቷል። በዛላምበሳ በኩልም ዛላምበሳን ለቆ ፋዒ የምትባል ትንሽ ከተማ ላይ ሰፍሯል። በመሆኑም በዚህ አቅጣጫ የወገን ጦር የአዲግራት ከተማን በቅርብ ርቀት እያየ ግስጋሴውን ቀጥሏል።

ጠላት አሁን ላይ በተለያዩ ግንባሮች በደረሱበት ጥቃቶች ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራም አስተናግዷል። ሙትና ቁስለኛውን ይዞ ለመሸሽም ተቸግሯል። በዚህም ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫና ውስጥ ገብቷል። የደረሰበትን ከፍተኛ ኪሳራ በሐሰትና በበሬ ወለደ ፕሮፓጋንዳው ለመሸፈን ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ለአብነትም በወገን ጦር እጅ ባለችው ሽራሮ ከተማ ኅብረተሰቡን በሐሰት ፖሮፓጋንዳ በማወናበድ እንዲለቅ ቢያደርግም ሕዝቡ ወደ ቀየው ተመልሶ መኖር ጀምሯል። በዋጃ ከተማም ተመሳሳይ ውጅንበር ለመፍጠር እየሞከረ ይገኛል።

ሕዝቤ ሆይ ንቃ ቀዬህን ለቀማኛ ለቀህ አትሂድ፤ ትግራዋይም በቃኝ በል ! ለከፋ ሰቆቃ የዳረገህና ወደማይቀረው መቃብሩ እየተሸኘ ያለውን ኃይል ለይተህ ምታ፤ ጨክነህ ቁረጥ .

ሱሌማን አብደላ

=============================

በሕይወት የሌሉ እና በውጪ ሀገር የሚገኙ ደንበኞችን ሒሳብ ለግል ጥቅም በማዋል የተጠረጠሩ 7 የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች ላይ ክስ ተመሠረተ ************************ በሕይወት የሌሉ...
13/10/2022

በሕይወት የሌሉ እና በውጪ ሀገር የሚገኙ ደንበኞችን ሒሳብ ለግል ጥቅም በማዋል የተጠረጠሩ 7 የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
************************

በሕይወት የሌሉ እና በውጪ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በባንክ ያላቸውን ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀስ የቆየ ሒሳብ ደንበኞቹ እንዳሉ እና እንደቀረቡ አስመስለው በማንቀሳቀስ ገንዘቡን ለሌሎች ሰዎች በማስተላለፍ በድምሩ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል የተባሉ 7 የአዋሽ ባንክ ሠራተኞች ላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መሠረተ።

ተከሳሾቹ፦

1ኛ) አቶ ሐብታሙ ደረሰ ጅማ - (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ)
2ኛ) አቶ ወርቁ ኃይሉ ጫሊ - (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ የነበረ)
3ኛ) አቶ ፈጠነ ገ/እግዚአብሔር ነጋ - (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች ግንኙነት መኮንን የነበረ)
4ኛ) አቶ ደበላ ንጉሴ ወርቅነህ - (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ)
5ኛ) አቶ ምስጋናው ያረጋል አንለይ - (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ)
6ኛ አቶ ሮባ ታደለ ዲንቃ - (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ ሒሳብ ሹም የነበረ) እና
7ኛ) ተከሳሽ ጉግሳ (በአዋሽ ባንክ የዋናው መ/ቤት ቅርንጫፍ የደንበኞች አገልግሎት መኮንን የነበረ) ናቸው።

12/10/2022

ከ12 ሺህ 700 በላይ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን እንዳልወሰዱ ተገለጸ
October 12, 2022
ፈተናውን አንፈተንም በሚል ላቋረጡ ተማሪዎች ሁለተኛ እድል እንደማይሰጥም ትምህርት ሚንስቴር ገልጿል
ከ12 ሺህ 700 በላይ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን እንዳልወሰዱ ተገለጸ።
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ባሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ መሰጠት የጀመረ ሲሆን ዛሬ ተጠናቋል ተብሏል።
የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ስለ ፈተናው በሰጡት መግለጫ 595 ሺህ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ፈተናን መውሰድ ያለባቸው ቢሆንም 585 ሺህ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።
በአማራ ክልል በመቅደላ አምባ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ባህርዳር እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች 12 ሺህ 787 ተማሪዎች ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውንም ሚንስትሩ በመግለጫው ላይ ተናግረዋል።
ፈተናውን አቋርጠው ለወጡ ተማሪዎች ሚኒስቴሩ ምንም አይነት እድል እንደማይሰጥም አሳውቋል።
በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ህይወቱ አልፏል።
የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና መጠናቀቁን ሚንስትሩ አክለዋል።
በፈተናው ወቅት ከሌሎቹ በተለየ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ በደረሰ ግርግር የአንድ (ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በፀጥታ አካላት ላይ ጉዳት እንደደረሰም ተገልጿል።
በሑዋሳ ዩንቩርሲቲም በመሸጋገሪያ ድልድይ ላይ በተፈጠረ የመደርመስ አደጋ የአንድ ተማሪ ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የአካል መጉደል አደጋም ደርሷል።
የሁለተኛው ዙር የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና የፊታችን ሰኞ እንደሚጀመር ይጠበቃል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Media Network WMN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wollo Media Network WMN:

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share