
11/04/2025
ህብረቱ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ኢዮቢልዩ በዓል መክፈቻ እና ዓመታዊ የመሪዎች ጉባዔ ከሚያዚያ 15-17 ያካሄዳል
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት ኢዮቢልዩ በዓል መክፈቻ እና ዓመታዊ የመሪዎች ጉባዔ ከሚያዚያ 15-17 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሄድ ህብረቱ በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ አስታውቋል
በዚህ 50ኛ ዓመት ኢዮቢልዩ በዓል የመሪዎችና የመጋቢዎች ኮንፍረንስ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ከመላው አገሪቱ ከአራት ሺህ በላይ መጋቢያን እና አገልጋዮች በዚህ ኮንፍራንስ ይታደማሉ ተብሏል
እንዲሁም የወንጌል እና የሰላም ጉዳይ ትልቅ ትኩረት የሚሰጥበት ፣ በመንፈሳዊ ፣ በማኅበራዊ ፣ በባህላዊና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ትምህርቶች የሚሰጡበትና ውይይቶች እንደሚካሄዱበት ተነግሯል
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት በአገር ውስጥ 182 ቤተ እምነቶችን በአባልነት፣ 75 ቤተክርስቲያን አጋዥ ክርስቲያናዊ ድርጅቶችን በተባባሪ አባልነት እንዲሁም ከ450 በላይ የሚሆኑ ቤተ-እምነቶችን በአጋር አባልነት የሚያስተባብር ኅብረት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባል እና የበላይ ጠባቂም ነው፡፡
የመጋቢዎችና የመሪዎች ኮንፈረንስ ላይ ለመመዝገብ ከታች ባለው ስልክ ቁጥሮች መጠቀም እንደሚቻል ማህበሩ አስታውቋል
0995 9 57 06/0995 9 57 07