26/06/2022
የኢትዮጵያ ባንኮችና የሐጅ ዶላር ጥያቄ ነገር
ክፍል ሁለት
❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗❗
በዚህ ጽሑፍ ክፍል 1 ቀደም ብለን እንደጠቀስነውም በአምናው ሪፖርት መሠረት ከዘጠና ሰባት ቢሊዮን በላይ ብር በወለድ አልባ ባንኮቹ ጋር አስቀምጠዋል። ጥያቄው ማስቀመጡ በራሱ ችግር ሆኖ አይደለም። በባንኮቹ ዘንድ ገንዘባቸውን ያስቀመጡት ምን ጥቅም እያገኙበት ነው? የሚለው ነው። ባንኮቹ በሀላል መንገድ ከሚያተርፉት ብዙም ድርሻ እንደሌላቸው ቀደም ባለው ክፍል ተመልክተናል፤
ለሐጅ ተግባርም በርካታ ባንኮች ዶላር ለመሸጥም እንደሚያግደረድሩም አይተናል፤ቀጥሎ የምንመለከተው ደግሞ በባንኮቹ ዘንድ በወለድ ነጻ አማካኝነት ከተቀመጠው ገንዘብስ ሙስሊም ነጋዴዎች በሃላል መንገድ እየተበደሩ (ፋይናንስ እያገኙ) ሥራቸውን ማስፋፋትና ማሳደግ ችለዋል ወይ? የሚለውን ነው።ምክንያቱም ይህም ነጠብ ባንኮቹ ለሙስሊሞች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ሊመዘንበት የሚገባው ሌላኛው ወሳኝ ነጥብ ነውና።
ከተቀማጭ ገንዘቡስ ምን ያክል ተጠቃሚ አደረጉ?
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢
የሙስሊም ነጋዴዎች ዋና ችግር ቢዝነሳቸውን ለማሳደግ ያለባቸው ማነቆ ወለድ ነጻ ሥርዓት የሚቀርብ የገንዘብ አቅርቦት ችግር ነው። አብዛኛዎቹ ባንኮች «በሸሪዓው መሠረት» እያሉ ሙስሊሞች ገንዘባቸውን እነርሱ ጋር እንዲያስቀምጡ ማስታወቂያ እየሠሩ ይወተውታሉ። እስካሁን ከአስራ አንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወለድ ነጻ ዘርፍ ገንዘባቸውን ባንኮቹ ዘንድ ማስቀመጥ ጀምረዋል።
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት ባንኮች ደንበኞቻቸው እነርሱ ጋር ተቀማጭ ካደረጓቸው ገንዘቦች መካከል 80% (ሰማንያ በመቶ ማለትም ከእያንዳንዱ መቶ ብር ላይ እስከ ሰማንያ ብር) ድረስ ለተበዳሪዎች ማበደር ይፈቅድላቸዋል።
በሀገራችን መደበኛ ባንኮች ዘንድ ከተቀመጠው አንድ ትሪሊዮን አራት መቶ ቢሊዮን(1,400,000,000,000) ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ ወለድን የሚጠነቀቁ ሙስሊሞች ወለድ ስለማይወስዱና ስለማይከፍሉ ከዚህ ገንዘብ መበደር አይችሉም።
በወለድ ነጻ ባንክ ዘርፍ የተቀመጠው ገንዘብ በሀገሪቱ በባንኮች አጠቃላይ ከተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ ሰባት በመቶ(7%) ድርሻ ሲኖረው ይህም በብሄራዊ ባንክ ይፋዊ ሪፖርት እስከ አምና ድረስ አጠቃላይ መጠኑ ዘጠና ሰባት ቢሊዮን ብር ደርሷል።ከዚህ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ እያንዳንዱ ባንክ እርሱ ዘንድ ካለው ምን ያክሉን በሸሪዓው መሠረት ፋይናንስ አደረጉ የሚለውን እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ምን ያክል ባንኮቹ ሙስሊም ነጋዴዎችንና ግለሰቦችን ለሥራቸው ማስፋፊያ፥ለቤት ግዢ፥ወዘተ እንዳበደሩ እንመለከታለን።
በብሄራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት በአጠቃላይ ባንኮች ካለው 97 ቢሊዮን በላይ ብር ዉስጥ ሰባ ስምንት ቢሊዮን(78) ድረስ ማበደር ይችላሉ። ሆኖም እስከ ጁን 30 ቀን 2021 ድረስ ሰባ ስምንት ቢሊዮን ዉስጥ በአጠቃላይ ያበደሩት መጠን ግን 25,876,177,940 (ሀያ አምስት ቢሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ ሰባት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ) ብር ያክል ብቻ ነው። ይህ ማለት እንዲያበድሩ ከተፈቀደላቸው ገንዘብ ዉስጥ ያበደሩት 33%(ሠላሳ ሦስት በመቶ) ብቻ ነው።ወይም ደግሞ ማበደር ከተፈቀደላቸው የተቀማጩ ገንዘብ 80%(ሰማንያ ከመቶ) ዉስጥ ያበደሩት የተቀማጩን ገንዘብ 26%(ሀያ ስድስት በመቶ) ብቻን ነው ማለት ነው። ቀጥሎ እያንዳንዱ ባንክ ካለው ተቀማጭ ላይ በብድር የሰጠውን ድርሻ በቅደም ተከተል እንመለከታለን።
1) እንደሀገር ከተቀማጭ ገንዘቡ ዉስጥ ለበርካታ ደንበኞች በማበደር የቀዳሚነቱን ሥፍራ የሚይዘው የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ነው።የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በሀገር ደረጃ በወለድ ነጻ ዘርፍ ከተሰጠው አጠቃላይ ፋይናንስ(ብድር) ዉስጥ 35.91%(ሠላሳ አምስት ነጥብ ዘጠኝ አንድ በመቶ) የሚሆነውን የርሱ ድርሻ ነው።
የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በአጠቃላይ ካለው 11,978,627,691(አሥራ አንድ ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰባ ስምንት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሀያ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና አንድ) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 9,582,902,152.8(ዘጠኝ ቢሊዮን አምስት መቶ ሰማኒያ ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ ሁለት ብር ከሰማኒያ ሳንቲም) ያክል ብቻ ነው።ከዚህ ዉስጥ የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በብድር የሰጠው 9,291,625,584.46(ዘጠኝ ቢሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሚሊዮን ስድስት መቶ ሀያ አምስት ሺህ አምስት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከአርባ ስምንት ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 96.96%(ዘጠና ስድስት ነጥብ ዘጠና ስድስት በመቶ) ያክሉን አበድሯል።
በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 78%(ሰባ ስምንት በመቶ) ያክሉን አበድሮ የቀረው 2%(ሁለት በመቶ) መጠን ነው ማለት ነው፤በዚህ ረገድም የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ ለበርካታ ቢዝነሶች በሸሪዓው መሠረት በሰጠው ፋይናንስ(ብድር) በእጅጉ ሊመሰገን ይገባል።
2) በቀጣይነት የሚገኘው ደግሞ በሀገሪቱ ደረጃ ካለው አጠቃላይ የወለድ አልባ ባንክ ዘርፍ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ ከግማሽ በላይ ማለትም 53.28 % (ሀምሳ ሦስት ነጥብ ሁለት ስምንት) ያክሉን ድርሻ የሚይዘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን ያበደረው ግን በተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ ከአራት እጥፍ ከሚያንሰው ከኦሮሚያ ሕብረት ባንክ መጠን በ11.71% (አስራ አንድ ነጥብ ሰባት አንድ በመቶ) ያነሰ ማለትም በሀገር ደረጃ ከተሰጠው አጠቃላይ ፋይናንስ ዉስጥ 24̀.2%(ሀያ አራት ነጥብ ሁለት) ያክል ብቻ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአጠቃላይ ካለው 52,039,110,704 (ሀምሳ ሁለት ቢሊዮን ሰላሳ ዘጠኝ ሚሊዮን አንድ መቶ አስር ሺህ ሰባት መቶ አራት)ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 41,631,288,563.2 (አርባ አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሠላሳ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰማንያ ስምነት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሦስት ብር ከሃያ ሳንቲም) ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር የሰጠው 6,261,216,099.20 (ስድስት ቢሊዮን ሁለት መቶ ስልሳ አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ አስራ ስድስት ሺህ ዘጠና ዘጠኝ ብር ከሃያ ሳንቲም) ያክሉን ነው፤
ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 15.04%(አስራ አምስት ነጥብ ዜሮ አራት በመቶ) ያክሉን አበድሯል።በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 12%% ያክሉን አበድሮ ሳያበድር የቀረው 68% መጠን ነው ማለት ነው፤
3) በ3ኛ ደረጃ ላይ የሀገሪቱን አጠቃላይ 13.69%(አስራ ሦስት ነጥብ ስድስት ዘጠኝ በመቶ) በመያዝ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ(አሁን ኦሮሚያ ባንክ በሚል ስያሜውን ቀይሯል) ይገኛል።ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በአጠቃላይ ካለው 4,879,909,490 (አራት ቢሊዮን ስምንት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ዘጠና) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 3,903,927,592(ሦስት ቢሊዮን ዘጠኝ መቶ ሦስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት) ብር ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በብድር የሰጠው 3,542,349,948.43(ሦስት ቢሊዮን አምስት መቶ አርባ ሁለት ሚሊዮን ሦስት መቶ አርባ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ብር ከአርባ ሦስት ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 90.74%(ዘጠና ነጥብ ሰባት አራት በመቶ) ያክሉን አበድሯል።በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 73%%% ያክሉን አበድሮ ሳያበድር የቀረው 7%(ሰባት በመቶ) መጠን ብቻ ነው ማለት ነው።
4) ከሀገሪቱ በወለድ ነጻ ዘርፍ ከተሰጠው ፋይናንስ ዉስጥ 8.46% ድርሻ በመያዝ በ4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ዳሸን ባንክ ነው። ዳሸን ባንክ በአጠቃላይ ካለው 4,608,841,903 (አራት ቢሊዮን ስድስት መቶ ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሦስት) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 3,687,073,522.4 (ሦስት ቢሊዮን ስድስት ሰማኒያ ሰባት መቶ ሦስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ዘጠና ሁለት) ብር ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ ዳሸን ባንክ በብድር የሰጠው 2,190,291,997.47 (ሁለት ቢሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሚሊዮን ሁለት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ብር ከአርባ ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 59.4%(ሀምሳ ዘጠኝ ነጥብ አራት አራት በመቶ) ያክሉን አበድሯል።በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 48% ያክሉን አበድሮ ሳያበድር የቀረው 32%(ሰላሳ ሁለት በመቶ) መጠን ነው ማለት ነው።
5) በሀገር ደረጃ 8.21% ድርሻ በመያዝ 5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዋሽ ባንክ ነው።አዋሽ ባንክ በአጠቃላይ ካለው 7,510,232,463 (ሰባት ቢሊዮን አምስት መቶ አስር ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ሦስት) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 6,008,185,970.4(ስድስት ቢሊዮን ስምንት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባቶ ብር ከአርባ ሳንቲም) ብር ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ አዋሽ ባንክ በብድር የሰጠው 2,123,779,822.54 (ሁለት ቢሊዮን አንድ መቶ ሃያ ሦስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ዘጠኝ ሺህ ሰምንት መቶ ሃያ ሁለት ብር ከሀምሳ አራት ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 35.35%(ሰላሳ አምስት ነጥብ ሰላሳ አምስት በመቶ) ያክሉን አበድሯል።በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 28% ያክሉን ሲሆን ሳያበድር የቀረው 52%(ሀምሳ ሁለት በመቶ) መጠን ያክል ነው ማለት ነው።
6) በ3.66% ሀገራዊ ድርሻ በ6ኛ ደረጃ ላይ አቢሲኒያ ባንክ ይገኛል።አቢሲኒያ ባንክ በአጠቃላይ ካለው 8,306,077,368 (ሰምንት ቢሊዮን ሦስት መቶ ስድስት ሚሊዮን ሰባ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ስልሳ ስምንት) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 6,644,861,894.4 (ስድስት ቢሊዮን ስድስት መቶ አርባ አራት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና አራት ብር ከአርባ ሳንቲ፥እ) ብር ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ አቢሲኒያ ባንክ በብድር የሰጠው 945,995,707.74 (ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ዘጠኛ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሰባት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 14.24%(አስራ አራት ነጥብ ሁለት አራት በመቶ) ያክሉን ብቻ አበድሯል።
ይህ ማለት ሳያበድር የያዘው 5,698,866,186.66(አምስት ቢሊዮን ስድስት መቶ ዘጠና ስምንት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰልሳ ስድስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ብር ከስልሳ ሳንቲም) አለው ማለት ነው።በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 11% ያክሉን ሲሆን ሳያበድር የቀረው 69%(ስልሳ ዘጠኝ በመቶ) መጠን ያክል ነው ማለት ነው።
7) በሀገር ዓቀፍ ወለድ አልባ ፋይናንስ በመስጠት ደረጃ በ3.18% ድርሻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በአጠቃላይ ካለው 3,056,420,485 (ሦስት ቢሊዮን ሀምሳ ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ ሃያ ሺህ አራት መቶ ሰማንያ አምስት) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 2,445,136,388 (ሁለት ቢሊዮን አራት መቶ አርባ አምስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ) ብር ያክል ብቻ ነው።ከዚህ ዉስጥ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በብድር የሰጠው 823,806,749.29 (ስምንት መቶ ሃያ ሦስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስድስት ሺህ ሰባት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከሃያ ዘጠኝ ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 33.69%(ሰላሳ ሦስት ነጥብ ስድስት ሰባት በመቶ) ያክሉን ብቻ አበድሯል።
በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 27% ያክሉን ሲሆን ሳያበድር የቀረው 53%(ሀምሳ ሦስት በመቶ) መጠን ያክል ነው ማለት ነው።
8) በ8ኛ ደረጃ ላይ በ3.10% ሀገራዊ የወለድ አልባ ፋይናንሲንግ ድርሻ ሕብረት ባንክ
ይገኛል።ሕብረት ባንክ በአጠቃላይ ካለው 1,847,561,771 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ አርባ ሰባት አምስት መቶ ስልሳ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አንድ) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 1,478,049,416.8 (አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰባ ስምንት ሚሊዮን አርባ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ አስራ ስድስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) ብር ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ ሕብረት ባንክ በብድር የሰጠው 803,191,681.33(ስምንት መቶ ሦስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ አንድ ብር ከሳላሳ ሦስት ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 54.34%(ሀምሳ አራት ነጥብ ሦስት አራት በመቶ) ያክሉን አበድሯል። በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 43% ያክሉን ሲሆን ሳያበድር የቀረው 37%(ሰላሳ ሰባት በመቶ) መጠን ያክል ነው ማለት ነው።
9) 9ኛ ደረጃ ላይ በ2.08% መጠን ሀገራዊ ድርሻ አባይ ባንክ ይገኛል።አባይ ባንክ በአጠቃላይ ካለው 1,277,435,441 (አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሰባት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሣ አምስት ሺህ አራት መቶ አርባ አንድ) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 1,021,948,352.8 (አንድ ቢሊዮን ሃያ አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሀምሳ ሁለት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) ብር ያክል ብቻ ነው።
ከዚህ ዉስጥ አባይ ባንክ በብድር የሰጠው 537,573,724.00(አምስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሃያ አራት በመቶ) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 52.60%(ሀምሳ ሁለት ነጥብ ስድስት በመቶ) ያክሉን አበድሯል። በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው 42% ያክሉን ሲሆን ሳያበድር የቀረው 38%(ሰላሳ ስምንት በመቶ) መጠን ያክል ነው ማለት ነው።
10) 1.38% ሐገራዊ የወለድ አልባ ብድር መስጠት ድርሻ በመያዝ ወጋገን ባንክ በ10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።ወጋገን ባንክ በአጠቃላይ ካለው 1,536,191,534 (አንድ ቢሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ ስድስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አንድ ሺህ አምስት መቶ ሰላሳ አራት) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 1,228,953,227.2(አንድ ቢሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ስምንት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ሦስት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ሰባት ብር ከሃያ ሳንቲም)ብር ያክል ብቻ ነው።ከዚህ ዉስጥ ወጋገን ባንክ በብድር የሰጠው 356,346,626.03 (ሦስት መቶ ሀምሳ ስድስት ሚሊዮን ሦስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ስድስት ብር ከሦስት ሳንቲም) ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ 29%(ሃያ ዘጠኝ በመቶ) ያክሉን አበድሯል። በሌላ አነጋገር ከአጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ 80% ማበደር ሲፈቀድለት እርሱ ግን ያበደረው የተቀማጩን 23% ያክሉን ሲሆን ሳያበድር የቀረው 57%(ሰላሳ ስምንት በመቶ) መጠን ያክል ነው ማለት ነው።
11) ብድር ባለመጀመር ወይም በ0% መጠን ቡና ባንክ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛል።ቡና ባንክ በአጠቃላይ ካለው 624,000,000 (ስድስት መቶ ሃያ አራት ሚሊዮን ብር) ብር ዉስጥ እንዲያበድር በሕግ የሚፈቀድለት 499,200,000 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር ያክል ብቻ ነው።ከዚህ ዉስጥ ቡና ባንክ እስከ ጁን 30 ቀን 2021 ድረስ የሰጠው ብድር የለም ወይም ዜሮ ነው ማለት ነው።ስለዚህ ሳይሰጥ የያዘው ሙሉውን 499,200,000 (አራት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር ያክሉን ነው፤ይህ ማለት ፋይናንስ ማድረግ ከሚፈቀድለት ገንዘብ ዉስጥ ምንም አላበደረም ማለት ነው።
በአምናው የብሄራዊ ባንክ ሪፖርት መሠረት ከሀገራችን ባንኮች መካከል ወለድ አልባ ዘርፍን ከተቀላቀሉት መካከል ከሰበሰቡት የተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ የተቀማጫቸውን ስንት በመቶ በወለድ አልባ ዘርፍ ገንዘቡን መልሰው ለደንበኞች አበደሩ የሚለው ደረጃቸው ከላይ ያየነውን ይመስላል፤ ካላቸው ተቀማጭ ገንዘብ ዉስጥ በማበደር ደንበኞች ቢዝነሳቸውን እንዲያሳድጉ የፋይናንስ በማድረግ ባንኮቹ ያላቸው ደረጃ ቅደም ተከተል ሲጠቃለል የሚከተለው ነው።
1ኛ-የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ፥
2ኛ፡-ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፥
3ኛ-ዳሸን ባንክ፥
4ኛ-ሕብረት ባንክ
፥5ኛ-አባይ ባንክ፥
6ኛ-አዋሽ ባንክ፥
7ኛ-ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
፥8ኛ-ወጋገን ባንክ፥
9ኛ-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
፥10ኛ-አቢሲኒያ ባንክ፥
11ኛ-ቡና ባንክ ላይ ይገኛሉ።
ይቀጥላል…