
14/09/2025
የሎንኪንግ የከባድ ማሽነሪዎች በኢትዮጽያ
ዩኒክ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. ከቻይናው የሎንኪንግ የግንባታ ማሽኖች አምራች ጋር ብቸኛ ወኪል ሆኖ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ፈረመ።
በትናንት እለት በተደረገው ስምምነት መሠረት እንደ ሎደር እና ኤክስካቫተር ያሉ የግንባታ ማሽኖችን በኢትዮጵያ ገበያ የማስተዋወቅና የማቅረብ እድልን እንደሚፈጥር በመርሐግብሩ ላይ ተገልጸዋል።
የዩኒክ ትሬዲንግ መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ ኢንድሪስ እንደገለፁት የንግድ ስራውን የጀመሩት ከአባታቸው በመነጨ የንግድ ልምድ ሲሆን፣ ስራውንም የጀመሩት ከ12 አመታት በፊት ቄራ አካባቢ በሚገኘው ሶፍያ ሞል ውስጥ በሚገኝ አንድ ትንሽዬ ሱቅ ውስጥ እንደነበር ገልጸዋል።
ዩኒክ ትሬዲንግ ሁለተኛ ቅርንጫፉን ሃና ማርያም አካባቢ መክፈት እንደቻለ እና የተለያዩ ተጎድተው የነበሩ ማሽነሪዎችን በመግዛት እና በመጠገን ወደ ገበያ በማቅረብ ስራውን ማስፋት እንደቻለ ተናግረዋል።
ይህ የስራ መስፋፋት ተጨማሪ ቦታን ስለሚያስፈልግ፣ ድርጅቱ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ 3000 ካሬ ሜትር ላይ የጥገና አገልግሎት የሚሰጥበት ማዕከል እና መጋዘን በመክፈት ስራውን ይበልጥ ማሳደግ ችሏል። ድርጅቱ የመለዋወጫ እቃዎችንም ከቻይና፣ ከኮሪያ እና ከዱባይ በማስመጣት ስራውን ይበልጥ እንዳጠናከረ አቶ መሀመድ አብራርተዋል።
አቶ መሀመድ ለውጭ ምንዛሪ እጥረት መፍትሄ ለመስጠት ድርጅቱ ከሁለት አመት በፊት ወደ ቡና ኤክስፖርት ስራ መግባቱን ገልጸዋል።
አሁን ደግሞ በቡልቡላ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ 13,000 ካሬ ሜትር ቦታ በመውሰድ የቡና ፕሮሰሲንግ እና የኩኪስ ብስኩት ፋብሪካ ግንባታ ማጠናቀቁን ገልጸው በመጪው ጥቅምት ወር ምርት ለመጀመር ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል። በአሁኑ ጊዜ ዩኒክ ትሬዲንግ 53 ቋሚ እና 25 ጊዜያዊ ሰራተኞች አሉት።
ዩቱብ
https://youtube.com/?si=c6Wc8RignrUhSQp_
ቴሌግራም https://t.me/Habsha_Taem
ፌስቡክ https://www.facebook.com/habeshatae?mibextid=ZbWKwL
ሊንክ ዲን https://www.linkedin.com/in/dj-fortin-k-ሐበሻ-ጣዕም-555600202