Yeraber Media-የራበር

Yeraber Media-የራበር Yeraber media network is news and media page information about social-economic political historical

18/06/2023

#ዴይስቶቹ - Deists........................
ዴይዝም (Deism) በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው ግንኙነት "በመገለጥ" (Revelation) ላይ ሳይሆን "በአመክንዮ" (Reason) ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ብሎ የሚያምን በዘመነ "አብርሆት" (enlightenment) የምዕራቡን ዓለም አስተሳሰብ ቅርፅ ያስያዘ "ሃይማኖት ቅብ" ፍልስፍና ነው። የፍልስፍናው ተከታዮችም በስነ መለኮት ምሁራኑ ዘንድ "ዴይስቶች" ተብለው ይጠራሉ።

ታዲያ ዴይስቶቹ ትምህርታቸውን የሚጀምሩት "አፅናፈ ዓለሙን የፈጠረው ፈጣሪ አለ" ብለው ነው። ነገር ግን "ይህ ፈጣሪ መላ ዓለሙን ከፈጠረ በኋላ የፈጠረውን ፍጥረት በሙሉ "ለተፈጥሮ ህግጋት" አሳልፎ ሰጥቶታል። ስለዚህ ፈጣሪ በዕለት ተዕለትም ሆነ በአጠቃላዩ የሰው ህይወትና ኑሮ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የሰውን ህይወት አይመራም አይቆጣጠርም። ፍጥረተ ዓለም የሚተዳደረው በራሱ "የተፈጥሮ ህግጋት" ነውና ብለው ያስተምራሉ።

ዴይስቶቹ ይህንኑ አቋማቸውንም በምሳሌ ሲያስረዱ፤ "እግዚአብሔርን እንደ ሰዓት ሰሪ ቁጠሩት" ይላሉ። ሰዓት ሰሪ ሰዓቱን ይሰራና ይሸጥልናል እኛም ሰዓቱን ይዘን ወደ ቤታችን እንሄዳለን። ሰዓቱም በራሱ ጊዜ ይዞራል (ይቆጥራል) እንጂ ሰዓት ሰሪው ቤታችን እየተመላለሰ አያዞርልንም። "ፈጣሪም" እንዲሁ ነው፤ ተፈጥሮን ፈጠረና "ለተፈጥሮ ህግጋት" ሰጠው። "የተፈጥሮን ህግጋት አውቀህ መኖር ታዲያ የአንተ ድርሻ ነው። ህይወትህ በእጅህ ናት! ማለታቸው ነው። ዴይስቶቹ።

በነገራችን ላይ ዴይዝም "የቃል እምነት" ወይም "የብልፅግና ወንጌል" ስሁት አስተምህሮ "ቅድመ አያት" ነው። ለዚያ ነው ከቃል እምነት መምህራን መካከል እንደ ማይልስ ሞንሮይ ያሉት "እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚሰራው እኛ ስንፈቅድለት ነው" በማለት እግዚአብሔር በምድር ባለ ጉዳይ "አያገባውም" የሚል ዓይነት የድፍረት ቃል የሚጠቀሙት። እንዲሁም "በአንደበታችን ቃል" (word of faith) "የተፈጥሮ ህግጋቱን" አንቀሳቅሰን የምንፈልገውን ሁሉ ማግኘት እንችላለን የሚሉት ። (ትይይዙን በቀጣይ ልጥፍ እመለስበታለሁ)

ችግሩ ምንድነው?

ታዋቂው የስነ መለኮት ምሁር ኤን. ቲ. ራይት "ዴይዝም የኤቲዝም (እግዚአብሔር የለሽነት) ምንጭ ነው ብሎ ያምናል። ራይት ሲናገር "ዴይዝም በመጀመሪያ የመፅሐፍ ቅዱሱን እግዚአብሔር እንደ ባላባት (Landlord) እንድትቆጥረው ያደርግሃል። ቀጥሎ ይህ ባላባት (Landlord) የሆነ እግዚአብሔር በሰርክ ኑሮህ ውስጥ የለም ይልሃል። በመጨረሻ እግዚአብሔር ራሱ የለም ይልሃል" ብሏል። እውነቱን ነው። እግዚአብሔር በሰርክ ህይወታችን ላይ መሪ እና ተቆጣጣሪ ካልሆነ በጊዜ ሂደት "እግዚአብሔር የለም!" የማንልበት ምንም ምክንያት አይኖርም። ስለዚህ አንዱ እና ትልቁ ችግር ዴይዝም "ለእግዚአብሔር የለሽነት" አስተሳሰብ መንገድ ጠራጊ መሆኑ ነው።

ሌላው ችግር፤ ዴይስት (Deist) ስትሆን "ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን" ብለህ መፀለይ አለመቻልህ ነው። "እግዚአብሔር በሰማይና በምድር የወደደውን አደረገ" ብለህም አታመሰግንም። "እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ" እያልህ ለእግዚአብሔር ስልጣን እውቅና አትሰጥም። ዴይስት ስትሆን ተንበርክከህ "ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?" ብለህ እግዚአብሔርን አትለምንም። "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው" ብለህም አትዘምርም።

ዴይስት ስትሆን "እግዚአብሔር ምን ይፈልጋል" ሳይሆን "እኔ ምን እፈልጋለሁ" ብለህ ነው ህይወትህን የምትቃኛት። በአይምሮህ ብቻ ነው የምትመራው። ዴይዝም በተፈጥሮ ህግጋት ተጠቅመህ የመረጥኸውን ማምጣት የጠላኸ

በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ግጭት እየቀሰቀሰ ያለው የኦሮሚያ ባንዲራን ለመስቀል የሚደረገው ህገወጥ ተግባር  አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው ኢሰመጉ ጠየቀ            ታህሳስ 4/2015በአዲስ ...
13/12/2022

በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ግጭት እየቀሰቀሰ ያለው የኦሮሚያ ባንዲራን ለመስቀል የሚደረገው ህገወጥ ተግባር አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጠው ኢሰመጉ ጠየቀ
ታህሳስ 4/2015
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች የኦሮሚያን መዝሙር ለማዘመር እና የኦሮሚያን ባንዲራ ለመስቀል በሚደረገው ህገ ወጥ ሙከራ ለሚነሱ ሁከቶች መንግስት በቂ ትኩረት በመስጠት ጉዳዩ ከቁጥጥር ውጭ ከመውጣቱ በፊት አስቸኳይ እና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ ኢሰመጉ አሳስቧል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና ከመዝሙር ጋር ተያይዞ ሁከቶች መነሳታቸው ይታወቃል።
እነዚህን አለመግባባቶች ተከትሎ የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በትምህርት ቤቶች ሰላም ማጣት፣ የአካል ጉዳትና ንብረት ውድመት እንዲሁም ሌሎችም ተፈጽመዋል፡፡
ባሳለፍነው ዓመት 2014 ዓ.ም በለሚ ኩራ ፣ በየካ፣ በቂርቆስ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና መዝሙር ጋር ተያይዞ ሁከቶች ተነስተው እንደነበር እና ይህንንም ተከትሎ የሚመለከታቸው የክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች፣ ወላጆች እና የትምህርት ቤቶች አመራሮች ባደረጉት ስብሰባ እና ውይይት ጉዳዩ በጊዜያዊነት ተፈትቶ ቆይቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ይህ ጉዳይ በቂ ትኩረት ባለማግኘቱና በዘላቂነት ባለመፈታቱ በ2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አለመግባባቶች ሊቀጥሉ ችለዋል፡፡ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኙት የሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የአብዮት ቅርስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና የጠመንጃ ያዥ አንደኛ ደረጃና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና መዝሙር ጋር ተያይዞ አለመግባባቶች የተነሱ ሲሆን በዚህም ምክንያት የተለያዩ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል፡፡
እነዚህ ትምህርት ቤቶች የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት ከወላጆች ጋር በ13/02/2015 ዓ.ም ስብሰባዎችን ያደረጉ ሲሆን የቋንቋ ትምህርቱ ላይ አለመግባባት እንደሌለ ነገር ግን ዋነኛ አለመግባባቶችን እየፈጠረ ያለው የሰንደቅ አላማ እና የመዝሙር ጉዳይ መሆኑን እንዲሁም ልጆች የማያውቁትን መዝሙር እንዲዘምሩ መገደድ የለባቸወም የሚሉ ሃሳቦች በስብሰባዎቹ ላይ መነሳታቸውን ኢሰመጉ የክትትል ስራን ለመስራት በአካል በስብሰባዎቹ ላይ በመገኘት ለመረዳት ችሏል፡፡
ነገር ግን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስር በሚገኘው ጠመንጃ ያዥ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሁከቱ በድጋሚ አገርሽቶ በ29/03/2015 ዓ.ም እና በ30/03/2015 ዓ.ም ዳግም መነሳቱን እና በዚሁ ሁከት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸሙን፣ የትምህርት ቤቱ ንብረቶች መውደማቸውን፣ እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ተማሪዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች መታሰራቸው ታውቋል ኢሰመጉ ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል፡፡
ስለሆነም መንግስት በአዲስ አበባ ከተማ አስስዳደር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በተደጋጋሚ ከኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እና መዝሙር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ አለመግባባቶችና ግጭቶች ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጥ፣
በትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ትምህርት እና የሚከናወኑ ስርአቶች በማናቸውም ረገድ ከሀይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተጽእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መከወን እንዳለባቸው
ትምህርት ቤቶች የእውቀት ቤት እንደመሆናቸው በእዚያ አግባብ ብቻ ከማንኛውም ፖለቲካዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ተጽእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ ስራቸውን እንዲያከናውኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ
በመጨረሻም የኦሮሚያ መገለጫ የሆኑትን ባንዲራ እና መዝሙር በግዳጅ በተማራዎች ላይ ለመጫን የሚደረገው ጥረት እንዲቆም ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች የከተማ አስተዳደሩ ተጠያቂ ነው ሲል እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መሰቀል እና መዝሙር መዘመር ጋር በተያያዘ ...
13/12/2022

በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች የከተማ አስተዳደሩ ተጠያቂ ነው ሲል እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ
ከኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ አላማ መሰቀል እና መዝሙር መዘመር ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ለሚፈጠሩ ችግሮች ብቸኛው ተጠያቂ የከተማ አስተዳደሩ ነው ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አሳሰበ።
ተቋሙ ባወጣው መግለጫ ተማሪዎችን ለማስገደድ በሚፈፀሙ ድርጊቶች በተማሪዎች እና በትምህርት ቤት ንብረቶች ላይ ለሚደርሱ ጥፋቶች “ተጠያቂው የከተማ አስተዳደሩ እንጂ ሌላ ውጫዊ አካል” አይደለም ብሏል።
እንባ ጠባቂ ተቋሙ አክሎም የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ የሚያገኛቸው ልዩ ጥቅሞች እና የአፈፃፀም ስርዓት በልተቀመጠለት ሁኔታ የክልሉ ባንዲራ እና መዝሙር በከተማዋ እንዲፈፀም የሚያስገድዱ “ግለሰብ ባለስልጣናት” በመኖራቸው የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል።
የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባወጣው መግለጫ የአንድ አካባቢ ችግር በድርድር ከተፈታ ለሌላ አካባቢ የማይሰራበት እንዲሁም የአደረጃጀት ጥያቄ የአንዱ በህገ መንግስቱ ተፈቶ የሌላው የማይፈታበት ምክንያቶች አይኖሩም ብሏል።
የተቋሙ መግለጫ ከነዚህ በተጨማሪ በህግ የበላይነት፣ በዜጎች ደህንነት እንዲሁም በሙስናና ብልሹ አሰራር እና ሌሎችም ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጓል።

11/12/2022

የደንቢደሎ ዩኒቨርስቲ የአማራ ተማሪዎች መታገታቸው ተነገረ።

በኦሮሚያ ክልል ስር በሚገኘው የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 9 የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች መታገታቸው ተነግሯል።

ተማሪዎቹ የታገቱት ባለፈው ሃሙስ ህዳር 29/2015 ከደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ አዲስ አበባ በኦዳ ባስ በሚጓዙበት ወቅት በምእራብ ወለጋዋ የጊምቢ ወረዳ ጉሊሶ ቀበሌ ውስጥ ነው ተብሏል።

ታጋች ተማሪዎችም:_

1) ቤዛ ተሾመ 5ኛ አመት የአርክቴክቸር ተማሪ ከአዲስአበባ ፣
2) ሰይዳ 5ኛ አመት የመካኒካል ተማሪ ከደባርቅ ፣
3) ማህሌት 4ኛ አመት የማኔጅመንት ተማሪ ከደብረ ማርቆስ ፣
4) ሲሳይ 4ኛ አመት ሳይኮሎጂ ከደብረ ማርቆስ ፣ 5) ደጀን 4ኛ አመት ኮምፒቱሽናል ሳይንስ ከ ደቡብ ጎንደር ፣
6) ኪሮስ 5ኛ አመት ሲቪል ኢንጂነር ከባህርዳር ፣ 7) ቀኑ መለስ 4ኛ አመት ባዮ ቴክኖሎጂ ከጎንደር ፣
😎 ቡዛዬሁ 4ኛ አመት ኮምፒቱሽናል ሳይንስ አከባቢው ያልታወቀ እና

9) ብርሀኑ 5ኛ አመት ሲቪል ኢንጂነሪንግ ከባህርዳር መሆናቸው ታውቋል።

በተጨማሪም ሌሎች የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉ ሮሃ የደረሳት መረጃ ያመለክታል።

በጉዳዩ ላይ የሚኖሩ ዝርዝር መረጃዎችንም ተከታትለን የምናደርስ ይሆናል።

ከሶስት ዓመት በፊት ህዳር 25/2012 ዓ. ም 17 የአማራ ብሄር ተወላጅ ተማሪዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን ታግተው ይኑሩ ይሙቱ ሳይለይ መረሳታቸው ይታወቃል።

እነዚህ መታገታቸው በመንግስት ትኩረት ያልተሰጠው ተማሪዎች፣ ቤተሰቦቻቸው በተደጋጋሚ" የመንግስት ያለህ የልጆቻችንን ነገር አንድ በሉን"ቢሉም ሰሚ አጥተው ዝም ብለዋል።

በነዚህ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ በአንድ ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞና ዘመቻ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም ከአንዳንድ ጉዳዩ ይመለከተናል ካሉ አካላት ውጪ አሁን ላይ ስለተማሪዎቹ የሚያነሳ የለም።

ታዲያ ከአመታት በኋላ የአጋች ታጋች ድራማ በማይጠፋበት የኦሮሚያ ክልል በተለይ ደግሞ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የታገቱበት የወለጋው ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዳግም መታገታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ዘገባው የሮሃ ሚዲያ ነው።

https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/3359799850929137/?app=fbl
05/12/2022

https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/3359799850929137/?app=fbl

በአዲስ አበባ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ግለሰብ የሞት ፍርድ ተወሰነባት

አዲስ አበባ (ኢዜአ) ህዳር 26/2015 በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሁለት ሕፃናትን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለችው ህይወት መኮንን የሞት ፍርድ ተወሰነባት።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ከባድ ግድያ እና የውንብድና ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ባዋለው ችሎቱ ነው የፍርድ ውሳኔውን ያሳለፈው።

በዚህም በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ቦሌ አራብሳ ኮንደሚኒየም በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረችው ህይወት መኮንን የፈጸመችውን የወንጀል ድርጊት በማጣራት ፍርድ ቤቱ የሞት ፍርድ ውሳኔ አሳልፏል።

03/12/2022

አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ!
ከሰሞኑ በኪረሞ፣ በሀሮ አዲስ ዓለም፣ በጃርዴጋ እና ሰቀላ አማራዎች ላይ ለቀናት የቆዬ ጦርነት በመክፈት በርካቶችን ሲገድል፣ ሲያቆስል እና ሲያፈናቅል ከሰነበተው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ፣ ሽምቅ ተዋጊ፣ ሚሊሻ እና የእነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ስርዓት ጋሻ/ጠባቂ ብዙ ሽህ ኃይል በተጨማሪ ህዳር 23/2015 ከ7 መኪና በላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልንና ኦነግ ሸኔን ያካተተ ጦር ከነቀምት ወደ ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ሻሾ በር ከተማ ገብቶ ማደሩ ይታወቃል።
ለጥቃት ያቀናው የኦሮሚያ ጥምር ኃይልም፦
1) ህዳር 24/2015 ከንጋቱ 12:30 ጀምሮ በጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ሻሾ በር/ጠጋጊጊ ከተማ ላይ በአማራው ላይ ጦርነት ከፍቷል።
2) ህዳር 24/2015 ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ ደግሞ በጊዳ አያና ወረዳ ከአንዶዴ ዲቾ 30 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ በአንገር ጉትን ከተማ በሚኖሩ አማራዎች ላይ በቡድን መሳሪያ በመታገዝ ይፋዊ ጦርነት የከፈተባቸው መሆኑን ከነዋሪዎች ለማረጋገጥ ተችሏል።
አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪም ተላልፏል።

የጫካ ፕሮጀክት የጫካ ፕሮጀክት ከእንግሊዝ ኤንባሲ ጀርባ ያለውን ተረራማ ጫካ ይዞ ፣ እንጦጦን አካሎ ፣ የሱሉልታን ግርጌ ይዞ ፣  ጣፎ ደርሶ ወዲህ የሚመለስ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው። የቦታው ስ...
18/11/2022

የጫካ ፕሮጀክት
የጫካ ፕሮጀክት ከእንግሊዝ ኤንባሲ ጀርባ ያለውን ተረራማ ጫካ ይዞ ፣ እንጦጦን አካሎ ፣ የሱሉልታን ግርጌ ይዞ ፣ ጣፎ ደርሶ ወዲህ የሚመለስ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።
የቦታው ስፋት በጠቅላላ 3,700 ሄክታር ሲሆን ይህም ማለት ደግሞ የልደታ ክፍለ ከተማን አራት ያህል እጥፍ ማለት ነው - ልደታ ክፍለ ከተማ 800 ሄክታር ገደማ እንደሆነ ልብ ይሏል።
በዚህ የጫካ ሳተላይት ከተማ ውስጥ ቤተመንግስት ፣ መኖሪያ ቤቶች ፣ የንግድ ማዕከላት ፣ ግድብ ፣ትላልቅ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፣ የኬብል ትራንስፖርት፣ ከተማን ከተማ የሚያሰኙ መዝናኛና አገልግሎት መስጫ ግንባታዎችን ያካተተ ነው።
ከአመት በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባወጣው የግንባታ ተሳትፎ ፍላጎት ጥሪ 11 ኩባንያዎች ቀርበው ነበር። ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት እያንዳንዳቸው ከአስር ሄክታር ያላነሰ ቦታ ተረክበው በሚሰጣቸው ዲዛይን መኖሪያ አፓርትመንቶችን ለመገንባት ተንቀሳቅሰዋል።
የቤተመንግስቱም ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የቤተመንግስት ግንባታው ብቻ የየወቅቱን የኮንስትራክሽን ዋጋ ጨምሮ እስከ 80 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ፤ አጠቃላይ ሳተላይት ከተማውን ለማጠናቀቅ ደግሞ አንድ ትሪሊዮን ብር ድረስ ሊፈጅ እንደሚችል ለፕሮጀክቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ ።
አዲሱ-አዲስ አበባ ውብ እና በየቀኑ ብዙ ገንዘብ ማመንጨት የሚችል እንደሆነ በባለሙያዎች ታምኖበታል ። ባለሙያዎች እንደሚሉት የጫካው ከተማ ሌሎች ከተሞች ሲገነቡ የተሠሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ እድል ይሰጣል። ሰው እና ተፈጥሮም የሚገናኙበት ውብ ስፍራም ይሆናል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (phd) ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፕሮጀክቱን ‘’የአፍሪካ ኩራት’’ ብለውታል ።
ፕሮጀክቱ በርካታ ኮንትራክተሮችን የሚያሳትፍ ፣ ብዙ የስራ ዕድል የሚፈጥር - አዳዲስ እና ዘመናዊ የአገነባብ ስልቶችን የሚያቀዳጅ በመሆኑ ለኢንዱስትሪው ተዋንያን መልካም ዜናም ጭምር ነው።
አዲሱ እየሩሳሌም -አሮጌው እየሩሳሌም ፤ አዲሱ ፓሪስ አሮጌው ፓሪስ እንደሚባለው ሁሉ አሮጌው አዲስ አበባ ፣ አዲሱ አዲስ አበባ - ይባል ዘንድ ጊዜው ፈቅዷል።
ምንጭ WZ news / ውድነህ ዘነበ
📸 ፋይል

15 ኪ.ሜ ስኩዌር የቆዳ ስፋት ያለው ገዳም በሰሜን አሜሪካ ሊገዛ ነው   | በሰሜን አሜሪካ በመካከለኛው የካልፎርንያ ግዛት  በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ስም  ገዳም ለ...
08/11/2022

15 ኪ.ሜ ስኩዌር የቆዳ ስፋት ያለው ገዳም በሰሜን አሜሪካ ሊገዛ ነው
| በሰሜን አሜሪካ በመካከለኛው የካልፎርንያ ግዛት በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ስም ገዳም ለማነጽ 15 ኪ.ሜ ስኩዌር የቆዳ ስፋት ያለው ቦታ ሊገዛ መሆኑ ተገለጸ።
በዚሁ ጉዳይ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ በሰሜን አሜሪካ የካልፎርንያ እና ኔቫዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መግለጫ ሰጥተዋል።
ብፁዕነታቸው በሰሜን አሜሪካ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በፍጥነት በማደግ እና በመስፋፋት ላይ ያለች መሆኗን አንስተው በውጪ ለሚኖሩ ምእመናን ሃይማኖታቸውንና ባሕሉን እንዲያውቅ የበኩሏን አስተዋጽኦ እያበረከተች እንዳለች ገልጸዋል።
ይህንን ተልእኮዋን በሥፋት ለመወጣትና የተሟላ አገልግሎት ለመሥጠት የሚያስችል አራት ዘመናዊ ቤቶች ከነ ሙሉ ዕቃቸው፣ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች፣ ልዩ ልዩ የጭነትና የእርሻና የቤት መኪናዎች እንዲሁም እንዲሁም በርካታ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች ያለውንና 3700 ኤከርስ (acers) ወይም አስራ አምስት ኪ.ሜ ስኩዌር ስፋት ያለውን ቦታ ለመግዛት ጥረት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ሀገረ ስብከቱ በገዳሙ ይዞታ ወጣቶች ሀገራቸውንና ቤተ ክርስቲያንን እንዲያውቁ ቋሚ የትምህርት አሰጣጥ መርሐ ግብር መዘርጋት ፣ ዘመናዊ ዩኒቨርስቲ፣ የካህናት ማሰልጠኛ ኮሌጅ፣ ቤተ መጻሕፍትና ሙዝየምን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን በአጭርና በረጅም ጊዜ ለማከናወን ዕቅድ ይዟል።
ለዚህ ዓላማ መሳካትም ምእመናን በገንዘብ ፣ በቁሳቁስ ፣ በዕውቀትና በጸሎት አስፈላጊውን ዕርዳታ በማድረግ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።
#ኢኦተቤ
share

የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች አስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ  | በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሁሉም ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ሚኒስትሮች የክልል ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የተወካዮችና ...
04/11/2022

የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች አስቸኳይ ስብሰባ ተጠሩ
| በዛሬው እለት በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ሁሉም ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና
ሚኒስትሮች የክልል ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት ኃላፊዎች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የሚሳተፉበት አስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል።
አስቸኳይ ስብሰባው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መክሮ የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

 #ለጥንቃቄ በተለይ  ለ ሴት እህቶቻችን ሴት እህቶቻችን በ ታክሲ ዉስጥ  ሿሿ በሚባል የ ሌብነት አይነት  በየቀኑ ማለት በሚቻል  ደረጃ እየተዘፉ  ስለሆነ  ሁሌም ጥንቃቄ አይለያችሁ1, እረ...
03/11/2022

#ለጥንቃቄ በተለይ ለ ሴት እህቶቻችን
ሴት እህቶቻችን በ ታክሲ ዉስጥ ሿሿ በሚባል የ ሌብነት አይነት በየቀኑ ማለት በሚቻል ደረጃ እየተዘፉ ስለሆነ ሁሌም ጥንቃቄ አይለያችሁ
1, እረዳቱ የትነሸ / ናቹ ሲል የሚሄዱበትን ቦታ ቀድሞ አለመናገር
2, ጋቢና አሰገብተው የበሩ ጎሚኒ ለቀቀ አሰተካክይው ሲሉ አለመተባበር
3, አጠገብሸ ያሰቀመጡት ሰው ሴትም ብትሆን የነሱ ተባባሪ ሰለምትሆን ሰልክ ቁጥር በስልክሸ ያዥልኝ ሲልሽ/ስትልሽ የስልክሽን አይነት አይቶ ለመስረቅ ስለሆነ በተቻለ አቅም ፈቃደኛ አለመሆን
4. ሶስት ወይም አራት ሆነው ተነጣጥለው የተቀመጡ ተሳፋሪዎች ሲያጋጥሙ ጥንቃቄ ማድረግ
5. የታክሲዉ ታፔላ እንዲሁም ታርጋው የተሸፈነ የተቆለመመ ከሆነ መጠራጠር
6. ከጎንሽ የተቀመጠው ተሳፋሪ ኮቱን በእጁ ይዞ እጁን ሸፍኖ ሚቁነጠነጥ ከሆነ ጥንቃቄ ማድረግ
7. ታክሲው እየሄደ ጋቢና ከሌላ ሰው ጋር ተቀምጠሽ የጋቢናው መስታወት ክፍት ሆኖ ረዳቱ በደጅ በኩል ሲያዋራሽ ጥንቃቄ ማድረግ ምክንያቱም አንቺ ዞረሽ በየዋህነት እሱን ስታዋሪው ከጎንሽ ያለው ሰው ከቦርሳሽ ውስጥ ሊሰርቅ ስለሚችል
8, አልኮል ሳኒታይዘር ልቀባሽ ሲሉ እንቢ ማለት ምክንያቱም የመርጫውን ጫፍ አዙረው በቀጥታ ወደ አይንሽ በመርጨት አንቺ አይንሽን ስታሺ ቦርሳሽን ወስደው ከታክሲ ውስጥ ሊወረዉሩሽ ስለሚችሉ...

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yeraber Media-የራበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Yeraber Media-የራበር:

Share