Ethiopian Capital Media

Ethiopian Capital Media Just Truth Media

05/10/2026
ትክክለኛው የዶ/ር መሣይ ሀይሉ አካውንት ይህ ነው። አካውንቱም 1K ተከታዮች አሉት።ከዚህ ውጭ በዶ/ር መሣይ ሀይሉ ስም የሚገኙ አካውንቶች የተሳሳቱ መሆናቸውን ሚዲያችን ከቅርብ ሰዎቻቸው አረ...
30/09/2026

ትክክለኛው የዶ/ር መሣይ ሀይሉ አካውንት ይህ ነው። አካውንቱም 1K ተከታዮች አሉት።

ከዚህ ውጭ በዶ/ር መሣይ ሀይሉ ስም የሚገኙ አካውንቶች የተሳሳቱ መሆናቸውን ሚዲያችን ከቅርብ ሰዎቻቸው አረጋግጣለች።

‎የሲዳማ ክልል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሊጀምር ነው፦ ዶክተር መሳይ ኃይሉ ነገ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ-መሐላ በመፈጸም የክልሉን ፕሬዝዳንትነት መንበር ይረከባሉ!‎******************//...
30/09/2026

‎የሲዳማ ክልል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ሊጀምር ነው፦ ዶክተር መሳይ ኃይሉ ነገ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ-መሐላ በመፈጸም የክልሉን ፕሬዝዳንትነት መንበር ይረከባሉ!
‎******************//******************
‎
‎AFFINI መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም — ሐዋሳ
‎
‎የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ነገ መስከረም 21 ቀን 2019 ዓ.ም በሚያካኺደው የመንግሥት ምስረታ ጉባኤ፣ የክልሉን የመጀመሪያውን ፕሬዝዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞን በመተካት ዶክተር መሳይ ኃይሉን የክልሉ አዲስ ፕሬዝዳንት አድርጎ እንደሚሾም ተረጋገጠ።
‎ዶክተር መሳይ በነገው ዕለት በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ በመፈጸም የክልሉን ከፍተኛ የፖለቲካና የሥራ አስፈጻሚነት ሥልጣን ይረከባሉ።
‎
‎የአዲሱ ፕሬዝዳንት መሰየም መላው የሲዳማ ህዝብ በታላቅ ተስፋና ደስታ እየጠበቀው የሚገኝ ክስተት ሲሆን፣ አፊኒ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን በማህበራዊ ሚዲያዎችና በህዝብ ዘንድ ባደረገው የሐሳብ ዳሰሳ እንደተረጋገጠው፣ ህዝቡ የዶክተር መሳይን ወደ ሥልጣን መምጣት እንደ ታላቅ "ህዝባዊ ድል" እና የለውጥ መነሻ አድርጎ እየተመለከተው ይገኛል።
‎
‎ይህ የመሪዎች የሥልጣን ሽግግር የመጣው ክልሉ ባለፉት ስምንት ዓመታት፣ በተለይም ደግሞ ባለፉት አምስት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ከፍተኛ የኋላቀርነትና የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ በቆየበት ማዕቀፍ ውስጥ ነው።
‎
‎ባለፉት ዓመታት በክልሉ የቀደሙ ከፍተኛ አመራሮች የተዘረጋው የተደራጀ የጥቅም ትስስር (ኔትወርክ) እና ሰፊ የሀብት ዘረፋ የክልሉን መልካም አስተዳደር ያደቀቀ፣ የልማት እንቅስቃሴዎችን ያቆረፈደ እንዲሁም ህዝቡን ለአካባቢያዊና ማህበራዊ ምሬት የዳረገ ዋና ምክንያት ነበር። በመሆኑም የነገው የሥልጣን ሽግግር ተራ አስተዳደራዊ ለውጥ ሳይሆን፣ ህዝቡ ላለፉት ዓመታት ሲታገልለት የቆየው የፍትህ፣ የሙስና ትግልና የለውጥ ጥያቄ ያገኘው ምላሽ ተደርጎ ተወስዷል።
‎

————————————————
‎
በመሆኑም አዲሱ ፕረዝደንት ዶክተር መሳይ ኃይሉ ዳንግሶ ማን ናቸው?
‎
‎ወደ ክልሉ ከፍተኛ አመራርነት እየመጡ ያሉት ዶክተር መሳይ ኃይሉ ዳንግሶ፣ ሰፊ የሕዝብ ጤና ዘርፍ መሪነት፣ ኤፒዲሚዮሎጂስትነትና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ረጅም ዓመታት ያካበቱ የመልካም አስተዳደርና የአመራር ልምድ ያላቸው ባለሙያ ነበሩ።
‎
‎የትምህርት ዝግጅታቸው የመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) በሕዝብ ጤና (Public Health) ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪ (MPH) በሕዝብ ጤና (Master’s of Public Health) ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የዶክትሬት ዲግሪ (PhD) በኤፒዲሚዮሎጂ (Epidemiology) ከኖርዌዩ በርገን ዩኒቨርሲቲ (University of Bergen) ተከታትለዋል።
‎
‎ዶክተር መሳይ ኃይሉ የኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) ዋና ዳይሬክተር፣ የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ ጥናትና ምርምር፣ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች አስተዳደር፣ የላቦራቶሪና የጤና መረጃ ትንተና ፕሮጀክቶችን በበላይነት ሲመሩ ቆይተዋል። የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል (Africa CDC) የቴክኒክና አማካሪ ምክር ቤት አባል ሆነው በማገልገል ከአህጉራዊው ተቋም የላቀ የሥራ እውቅና አግኝተዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና የኢትዮጵያ አንቲ-ዶፒንግ ባለሥልጣን የቦርድ አባል ሆነው አገልግለዋል።
‎
‎የጤና ሚኒስቴር የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልም በመሆን በብሔራዊ የጤና ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን አገልግለዋል።

አቶ መምሩ ሞኬ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ  ሆነው ተሾሙ=======================አቶ መምሩ ሞኬ ዳዋቆ  የቀድሞው የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ...
30/09/2026

አቶ መምሩ ሞኬ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ
=======================
አቶ መምሩ ሞኬ ዳዋቆ የቀድሞው የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበረውን አቶ አብርሃም ማረሻሎውን በመተካት የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ
በመሆን ተሹመዋል።

አቶ መምሩ ከዚህ በፊት የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፓረሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እንዲሁም የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አሚኮ አዲስ ለተሾሙት መምሩ ሞኬ መልካም የሥራ ዘመን እንመኛለን !

📢 ማስታወቂያበ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚ...
25/09/2026

📢 ማስታወቂያ

በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡

1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡

የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።

2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦

👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement
3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።

ትምህርት ሚኒስቴር

ሰበር ዜናበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ500 ሚሊዮን ብር የICT ግዥ በአስቸኳይ እንዲቆም ተጠየቀየሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት የትምህርት ሚንስቴር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ፣ በግምት 5...
05/09/2026

ሰበር ዜና

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የ500 ሚሊዮን ብር የICT ግዥ በአስቸኳይ እንዲቆም ተጠየቀ

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት የትምህርት ሚንስቴር ያስተላለፈውን መመሪያ በመጣስ፣ በግምት 500 ሚሊዮን ብር የሚገመት የICT ግዥ ለማፅደቅ ጥረት እያደረገ መሆኑን ከውስጥ መረጃ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል።

በግዥው ሂደት ከ20–25 ሚሊዮን ብር የሚገመት የጉቦ ክፍያ ሊፈፀም እንደሚችል የሚያመለክቱ ክሶችም ቀርበዋል።

የትምህርት ሚንስቴር ራስ ገዝ የሚሆኑ ዩኒቨርሲቲዎች ከሐምሌ 1 ጀምሮ ትላልቅ ውሎችን እንዳይፈፅሙ በደብዳቤ መመሪያ መስጠቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህን መመሪያ በመጣስ የተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ በቀድሞ የግዥ ሂደት የተጭበረበረውን ውል ለመስጠት እንደገና ጥረት እያደረጉ መሆኑን የዘወትር የውስጥ መረጃ ምንጫችን ለኢካሚ አሳውቋል።

እንደ መረጃ ምንጩ ገለጻ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጨረታ ሂደት በተለያዩ ምክንያቶች መቋረጡን ተከትሎ፣ በአሁኑ ወቅት ግዥውን ለተወሰነ ኩባንያ ለማስተላለፍ የሚደረግ ጥረት እንዳለም ታውቋል።

በተለይም የግዥ ክፍሉን በመጫንና የጨረታ ሂደቱን በማስተካከል የተጠቀሰውን ኩባንያ ለመጥቀም እየተደረገ ነው የተባለው ጥረት ሌብነቱ የደረሰበትን ጥግ ያሳያል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ፣ የICT ክፍል ኃላፊ አቶ እንዳልካቸው በቴክኒክ ኮሚቴው ሂደት ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ግዥው እንዲፈፀም እያደረገ ነው።

ስለሆነም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት፣ በተለይም ትምህርት ሚንስቴር፣ የግዥውን ሂደት በአስቸኳይ እንዲመረምሩና ሕገወጥ ድርጊቱን እንዲያስቆሙ ጥሪ ቀርቧል።

ግልባጭ፦ ለክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የኢኮኖሚ ለውጥ ሞተር መሆን አለባቸውበThe Reporter Ethiopia ነሐሴ 1 ቀን 2026 የታተመ አንድ የአስተያየት ጽሑፍ፣ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ...
03/09/2026

የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የኢኮኖሚ ለውጥ ሞተር መሆን አለባቸው

በThe Reporter Ethiopia ነሐሴ 1 ቀን 2026 የታተመ አንድ የአስተያየት ጽሑፍ፣ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ወረቀትና ተመራቂ ብቻ ከማፍራት ባለፈ የኢኖቬሽን፣ የምርታማነትና የኢኮኖሚ ለውጥ ሞተሮች መሆን እንዳለባቸው አበክሮ ያቀርባል።

ጽሑፉ በዶ/ር ታደሰ ዘርፉ የቀረበ ሲሆን፣ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ከግብርና፣ ከኢንዱስትሪ፣ ከጤና፣ ከአየር ንብረት፣ ከዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ ከኃይልና ከአስተዳደር ጋር ተያይዘው ለሀገሪቱ ዋና ችግር መፍትሔ ማበጀት እንዳለባቸው ይጠቁማል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በህትመት ብዛት ብቻ ከመመዘን ይልቅ፣ በፓተንት፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ አዳዲስ የንግድ ሥራዎች፣ የፖሊሲ ተፅዕኖ፣ የሥራ ፈጠራና የማህበረሰብ ተፅዕኖ መመዘን እንዳለባቸው ያስረዳል።

ጽሑፉ የቅርብ ጊዜውን የዩኒቨርሲቲዎች ምደባ አንድ ጠቃሚ እርምጃ ቢሆንም፣ ምደባ ብቻ የምርምር ብቃትን አይፈጥርም ይላል። ግልጽ ተልዕኮ፣ ተገቢ ሀብት፣ ጠንካራ አመራር፣ ተጠያቂነትና ከመንግሥትና ከኢንዱስትሪ ጋር የተጠናከረ ትስስር ያስፈልጋል።

ዋናው ጥያቄ፦ኢትዮጵያ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች አሏት? የሚለው ሳይሆን፣ እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የኢኖቬሽን፣ የምርታማነትና የኢኮኖሚ ለውጥ ሞተሮች ለመሆን ዝግጁ ናቸውን? የሚለው ነው።

ደግሰው ደርቤ እንደዘገበው

ልዩ ዘገባ፦ የሲዳማ ተወላጅ ምሁራንን ከሥራ ለማሰናበት የታቀደ ፕሮጀክት ተቀርጾ መጠናቀቁ ተገለፀ። ኢትዮጵያ ካፒታል ሚዲያ — ከአስተማማኝ ምንጮች ባገኘችው መረጃ መሠረት፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ...
30/08/2026

ልዩ ዘገባ፦ የሲዳማ ተወላጅ ምሁራንን ከሥራ ለማሰናበት የታቀደ ፕሮጀክት ተቀርጾ መጠናቀቁ ተገለፀ።

ኢትዮጵያ ካፒታል ሚዲያ — ከአስተማማኝ ምንጮች ባገኘችው መረጃ መሠረት፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቋም እና አሠራር ላይ ቅሬታ ያቀረቡና የተቃወሙ በርካታ የሲዳማ ተወላጅ ምሁራንን ከሥራ ለማሰናበት የተዘጋጀ ፕሮጀክት መጠናቀቁንና ጉዳዩ ለትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት መደረጉን ለማወቅ ተችሏል።
በተቋሙ ውስጥ የተከሰቱ አሠራር ነክ ችግሮችን በአደባባይ አጋልጠዋል የተባሉትን እነዚህን ምሁራን ከሥራ ለማሰናበት የተጀመረው እንቅስቃሴ “የመጨረሻ የበቀል እርምጃ” ሲሉ ምንጮች ገልጸውታል። እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ከሥራ እንዲሰናበቱ በዝርዝር የተካተቱት ባለሙያዎችና መምህራን የሚከተሉት ናቸው፦
* ዶ/ር ፍረው ካሳ — ከዳዬ ካምፓስ
* አቶ ዮሴፍ — ከዳዬ ካምፓስ
* ዶ/ር ክብሩ — ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ
* ዶ/ር ባዩ ቡንኩራ — ከግብርና ኮሌጅ
* ዶ/ር አለሙ ጣሚሶ — ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ
* አቶ አየለ አዳቶ — ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት
* አቶ ተመስገን — ከቴክኖሎጂ ካምፓስ
* ወ/ሮ ምህረት ገነነ — ከሥርዓተ ፆታ ክፍል
* አቶ ምትኩ — ከግንባታ ክፍል
* አቶ ባልጉዳ በላይ — ከወንዶ ገነት ኮሌጅ
* ዶ/ር ሳሙኤል — ከወንዶ ገነት ኮሌጅ
* አቶ አጥናፉ — ከዋናው ግቢ
* ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ — የምክትል ፕሬዚዳንት (እንደ ምንጮቹ ገለጻ የመጨረሻው ተሰናባች እንዲሆኑ የተመደቡ)
ይህ የታቀደው እርምጃ በዶ/ር ችሮታ ተዋናይነት፣ በዶ/ር ፍስሃ አስፈጻሚነት እንዲሁም በሁለቱ የሲዳማ ተወላጅ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ደጋፊነት እስከ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ተፈጻሚ ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ የሌላ ብሔር ተወላጅ ምሁር እንደገለጹት፤ በስም ዝርዝሩ የተካተቱት ምሁራን ላይ ሊወሰድ የታሰበው እርምጃ በሙያዊ ብቃት ወይም በሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን፣ የሲዳማ ተወላጅ ምሁራን በተቋሙ ውስጥ ዳግም እንዳያንሰራሩ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።
ቀደም ሲል ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ “እነዚህን ኃላፊዎችና ምሁራን ከሥራ ካሰናበትኩ በኋላ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ እመደባለሁ፤ ወይም ደግሞ እዚሁ እቀጥላለሁ” የሚል አቅጣጫ ከበላይ አካል እንደተሰጣቸው ለወዳጆቻቸው መናገራቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
ይህ መሰሉ አሠራር በአካባቢው የፀጥታና የስጋት ሁኔታዎችን ሊፈጥር ስለሚችል የሚመለከተው የመንግሥት አካል በተቋሙ ላይ የከፋ ጉዳት ሳይደርስ አስቸኳይ ውሳኔና ጣልቃ ገብነት እንዲያደርግ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በመማጸን ላይ ይገኛሉ።

ኢካሚ

1.15 ቢሊዮን ብር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመዘበረና በኦዲት የተረጋገጠ ገንዘብ በርካታ ኃላፊዎችን ለእስር ሊዳርግ እንደሚችል የፍትህ ሚኒስቴር ምንጮች ገለጹከ12 በላይ ሠራተኞች በእስር ላይ እ...
29/08/2026

1.15 ቢሊዮን ብር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመዘበረና በኦዲት የተረጋገጠ ገንዘብ በርካታ ኃላፊዎችን ለእስር ሊዳርግ እንደሚችል የፍትህ ሚኒስቴር ምንጮች ገለጹ

ከ12 በላይ ሠራተኞች በእስር ላይ እንዳሉ የሚገለጸው የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሙስና ጉዳይ፣ ሌሎች በርካታ አመራሮችንም በተጨማሪነት ለእስር ሊዳርግ እንደሚችል በውስጥ መስመር በተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ሙሰኞችን በተመለከተ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ተከትሎ፣ በከፍተኛ ደረጃ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው የፍትህ ሚኒስቴር በርካታ የዩኒቨርሲቲ አመራሮችን ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል ምርመራ ማጠናቀቁንና ቀጣይ እርምጃ እየተጠበቀ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል የዲላ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ በአጠቃላይ የተመዘበረው ገንዘብ መጠን ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎ፣ ሁለት የቀድሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችን ጨምሮ በርካታ ኃላፊዎች በሕግ ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ዝርዝር መረጃውን በተከታታይ የምናቀርብ ይሆናል!

Office of the Prime Minister-Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia
Prosperity Party - ብልፅግና ✪
Abiy Ahmed Ali

ልዩ ዘገባ፦ የምክትል ፕሬዚዳንቱ ከ400 ሺህ ብር በላይ ለዩኒቨርሲቲው መመለስና የአሠራር ጥያቄዎችኢትዮጵያ ካፒታል ሚዲያ — ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባገኘችው መረጃ መሠረት፣ የዩኒቨርሲቲው የምርም...
29/08/2026

ልዩ ዘገባ፦ የምክትል ፕሬዚዳንቱ ከ400 ሺህ ብር በላይ ለዩኒቨርሲቲው መመለስና የአሠራር ጥያቄዎች
ኢትዮጵያ ካፒታል ሚዲያ — ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ባገኘችው መረጃ መሠረት፣ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ ከ400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር በላይ ወደ ዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ መመለሳቸው ታውቋል።
ኢትዮጵያ ካፒታል ሚዲያ ቀደም ሲል ባስነበበው ዘገባ፤ ዶ/ር ታፈሰ ማቴዎስ እና የአስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ በሥልጣን ዘመናቸው ከሁለት የፋይናንስ ምንጮች ተደራራቢ የሥራ ኃላፊነትና ጥቅማጥቅሞችን ሲቀበሉ ነበር በሚል የቀረበውን ጥያቄ መዘገቡ ይታወሳል።
ሚዲያው ባደረገው ተጨማሪ ማጣራት፣ ዶ/ር ታፈሰ ከ400,000 ብር በላይ በያዝነው ወር ወደ ዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ተመላሽ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። ከዩኒቨርሲቲው የተገኙ ምንጮች እንደገለጹት፣ ክፍያው ተመላሽ ከተደረገ በኋላ ጉዳዩ ለብዙኃን መገናኛዎችና ለሕዝብ እንዳይወጣ ለፋይናንስ ሠራተኞች ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
በሌላ በኩል፣ የአስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ ተመሳሳይ ተመላሽ መደረግ ያለበትን ገንዘብ እስካሁን አለመመለሳቸውን የዩኒቨርሲቲው የውስጥ ኦዲት ማረጋገጡንና ተመላሽ እንዲያደርጉ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንደጻፈላቸው ምንጮች ጠቁመዋል። በተጨማሪም ዶ/ር ሳሙኤል ገንዘቡን ለመመለስ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቃቸው ታውቋል።
ይህ አጋጣሚ በዩኒቨርሲቲው የፋይናንስ አሠራር፣ በኃላፊዎች ጥቅማጥቅም አከፋፈል እና በውስጥ ቁጥጥር ሥርዓት ላይ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል። በተለይም ተመሳሳይ የኦዲት ግኝት ባለበት ሁኔታ፣ አንደኛው ኃላፊ ገንዘብ ሲመልስ ሌላኛው ሳያመለስ መቅረቱ ለምን የተለያየ አካሄድ እንደተከተለ ጥያቄ ፈጥሯል። ይህንንም ተከትሎ ዶ/ር ሳሙኤል ጂሎ የኦዲት ግኝት ያለባቸው በመሆኑ በቀጣይ እርምጃ ከሚወሰድባቸው ኃላፊዎች ተርታ እንዲሰለፉ መደረጉን ምንጮች አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ካፒታል ሚዲያ ጉዳዩን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንትና ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብታደርግም፣ እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።
ሌሎች፣ ተያያዥ ሰነዶችና ኦፊሴላዊ ምላሾች ሲደርሱን ለአንባቢዎች እናደርሳለን።

Office of the Prime Minister-Ethiopia
Ministry of Education Ethiopia
Federal Ethics and Anti-Corruption Commission

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Capital Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share