
07/09/2025
የኅብር ቀን
ኢትዮጵያ በብሔር፣ በሃይማኖት እና ባህል ኅብር ያጌጠች ውብ ሀገር ነች፡፡
ኅበሯ የጥንካሬዋ እና የውበቷ መገለጫ ነው፡፡
በዚህ ኅብሯም ዓለም የሚደነቅባቸውን ጀብዱዎች ፈጽማለች፡፡
ጳጉሜን ሁለት "ብዝኃነት የኢትዮጵያ ጌጥ!" በሚል መሪ ቃል የኅብር ቀን ሆኖ ይውላል፡፡ በዕለቱ ኢትዮጵያውያን በኅበረት ያሳኳቸው ታላላቅ ድሎች ይታሰባሉ፡፡
ኢትየጵያውያ በዘመናት ሂደት በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነቡ የመጡ የነባር የአብሮነት እሴቶች፣ የወል ታሪኮች እና ባህሎችበላቤት ነች፡፡
ይህን እሴቷን ተጠቅማም የትንሣኤዋ ማብሰሪያ የሆነውን የማንሰራራት ዘመን ጀምራለች፡፡
ትላንት በኅብረት ዓድዋ ላይ ታሪኳን በወርቅ ቀለም እንደጸፈችው ዛሬም በልጆቿ ኅብር እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ያሉ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን አሳክታለች፡፡
#ኢትዮጵያ #ኅብር #ጳጉሜን