Gohe Tv Broadcasting service

Gohe Tv Broadcasting service ጎህ የህዝብ ድምፅ🇪🇹

"Our Strategic Partnership challenges us in more than one way.If it is accepted, in terms of principles, that Africa mus...
14/02/2024

"Our Strategic Partnership challenges us in more than one way.
If it is accepted, in terms of principles, that Africa must, for its peace, its security
and its sustainable development, count first and foremost on its own strengths,
its own genius, its own chain of solidarity, no one can deny the relevance, at this
stage of our evolution, of the need for mutually beneficial Partnerships with
others."

"የእኛ ስልታዊ አጋርነት ከአንድ በላይ በሆነ መንገድ ይፈትነናል።
ተቀባይነት ካገኘ፣ ከመሠረታዊ መርሆች አንፃር፣ አፍሪካ ለሰላሟ፣ ለደህንነቷ መረጋገጥ አለባት"

H.E. MOUSSA FAKI MAHAMAT
CHAIRPERSON OF THE AFRICAN UNION COMMISSION
FORTY FOURTH ORDINARY SESSION OF
THE EXECUTIVE COUNCIL

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ አለም በሞት ተለየ። የስፖርት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን የሚያቀርብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅ...
23/01/2024

አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
የስፖርት ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ የሀገራችንን ስፖርታዊ ክንውኖችን የሚያቀርብ እንዲሁም ከስፖርታዊ ክንዋኔዎች በተጨማሪ በጠቅላላ እውቀቱ እና መረጃ አያያዙ በርካታ እውቀቶችን ያስጨበጠ ጋዜጠኛ ነበር።
በተለያዩ የራዲዮና ቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ላይ ታሪኮችንና ወጎችን በማቅረብም በሚዲያው ላይ ከአርባ አመታት በላይ አገልግሏል።
አንጋፋው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ “ ሊብሮ “ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ንጋት ላይ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።
ጎህ ቴሌቪዠን ለመላው ቤተሰቦቹ ፣ ጓደኞቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት ሊድ የዕድገት ...
23/01/2024

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የሦስት ዓመት ሊድ የዕድገት ስትራቴጂ ቀርፆ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረ አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ አስቆጥሯል ብለዋል።

በዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ የሚችል አቅም እየገነባ መሆኑንም ገልፀዋል።

በግማሽ ዓመቱ አዳዲስ 232 የሞባይል ጣቢያዎች መገንባታቸውን ጠቁመው የ3ጂ፣ 4ጂ እና 5ጂ ማስፋፊያዎች መስራታቸውን ተናግረዋል።

በዚህም እስካሁን 463 ከተሞች የ4ጂ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 40 አዳዲስ ከተሞች ላይ ተደራሽ መደረጉን አብራርተዋል።

በርካታ የገጠር ቀበሌዎችም ላይ የኔትወርክ ማስፋፊያ እና አዳዲስ ግንባታ መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በዓለም ካሉ 774 የቴሌ ኦፕሬተሮች መካከል 19ኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን ጠቁመው፤ በአፍሪካ ከሚገኙ 195 ኦፕሬተሮች መካከል ደግሞ 2ኛ ደረጃ ላይ መሆኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልፀዋል።

በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 42 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ጠቁመው፤ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ አገልግሎቶችም 84 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ አግኝቷል ብለዋል።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 26 በመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 11 ነጥብ 5 ቢሊየን የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ጠቁመው ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል።

ከጋዜጠኞች ለተነሳላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በተለየዩ የሀገሪቱዋት ክፍል ያጋጠመው የፀጥታ ችግር የአገልግሎት መቋረጥ፣የቴሌኮም ማጭበርበርና የግንባታ ስራ ግበዓቶች እጥረት እንዲሁም የገበያ አለመረጋጋት በግማሽ አመቱ እንደ ተግዳሮት ተጠቅሰዋል።

Interms of enhancing quality of service,networks coverage & capacity, various projects are underway while 5G mobile tech...
23/01/2024

Interms of enhancing quality of service,networks coverage & capacity, various projects are underway while 5G mobile technology service is already commercialized in certain cities,during half year, vast mobile network expansions and capacity enhancements have been done to serve additional 678.2 k customers over a 3G network, 1.1 million customers over a 4G network, 148.2k over 5G network .as a result a total capacity of serving additional 1.9 million customers where created, which brought the total mobile network capacity to 81 million.

ኢትዮቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት መንፈቅ 43 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት 42.9 ቢሊዮን ብር ...
23/01/2024

ኢትዮቴሌኮም በ2016 በጀት ዓመት መንፈቅ 43 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ገለፀ።

መንግስታዊው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት 42.9 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ኢትዮ ቴሌኮም በዚሁ ጊዜ ውስጥ የደንበኞቹን ቁጥር 74.6 ሚሊዮን መድረሱንም ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የገለጸው የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። ተቋሙ በዚህ ጊዜ ውስጥ ያስገባው ገቢ፤ ከእቅዱ 98 በመቶውን ያሳካ መሆኑን የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬሕይወት ታምሩ ተናግረዋል።።

ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 26 በመቶ ዕድገት ያሳየ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል። ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ያገኘው ገቢ 33.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን በወቅቱ ያስመዘገበው ትርፍ ደግሞ 8.18 ቢሊዮን ብር ነበር። ተቋሙ ዘንድሮ በግማሽ ዓመት ብቻ 11 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱም ይፋ ተደርጉዋል።

 የ19ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ጨዋታ ነገ በሚደረጉ መርሃ ግብሮቾ ይጀምራል፡፡ አስቶንቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት መርሃ ግብር ከተጠባቂ ጨዋታወች መካከል የመጀመሪያዉ ነ...
25/12/2023


የ19ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜየርሊግ ጨዋታ ነገ በሚደረጉ መርሃ ግብሮቾ ይጀምራል፡፡ አስቶንቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት መርሃ ግብር ከተጠባቂ ጨዋታወች መካከል የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡

 የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለማቅረብ የሚስችል የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ አገልግሎት ተጀመረ*******************,(ኢ ፕ ድ) ኢትዮ ቴሌኮም የፋይናንስ ተቋማት አገ...
22/12/2023


የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለማቅረብ የሚስችል የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ አገልግሎት ተጀመረ
*******************,
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮ ቴሌኮም የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን በቴሌብር ለደንበኞቻቸው ለማቅረብ የሚስችል የዲጂታል ፋይናንስ ገበያ እና የዲጂታል አክሲዮን ግዢና ሽያጭ አገልግሎቶችን በይፋ አስጀመረ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ስለ አገልግሎቶቹ ማብራሪያ በሰጡበት በወቅት እንደገለፁት፤ አገልግሎቶቹ ሁሉም ባንኮች ኢንሹራንሶች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎታቸውን በቴሌ ብር መተግበሪያ በማስቀመጥ ለበርካታ ዜጎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያስችላል።

ይህም ብሔራዊ ባንክ በ2025 በአገር ደረጃ የፋይናን አግልግሎትን 70 በመቶ ለማድረስ ያስቀመጠዉን ግብ ለማሳት እና ዲጅታል ፋይናንሲንግን ለማሳደግ ይረዳል ብለዋል።

በተጨማሪም ሁለተኛው የአክሲዮን አገልግሎቶችን ለመግዛትና ለመሸጥ የሚያስችል ሲሆን፤ በዚህም ህጋዊ የሆኑ ባለአክሲዮኖች አገልግሎታቸውን በማቅረብ ብስልክ ቢቻ ለበርካታ ዜጎች ተደራሽ ይሆናሉ ሲሉ ገልፀዋል።

 የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ትላንት ሲደረግ  ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡  ዛሬም አንድ መርሃ ግብር አምስት ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡ት...
22/12/2023


የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ ትላንት ሲደረግ ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡ ዛሬም አንድ መርሃ ግብር አምስት ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡

ትላንት ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ እና ብራይተን ያደረጉት የ18ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሜርሊግ ጨዋታ በአቻ ዉጤት ተጠናቋል፡፡
ክሪስታል ፓላስ ባሳለፍነዉ የዉድድር አመት ወደ ወራጅ ቀጠናዉ ላለመዉረድ ሲታገሉ መቆየተቻዉ ይታወሳል፡፡ በዘንድሮዉ የዉድድር አመትም የ76 አመቱን ሮይ ሀዲሰንን በዋና አሰልጣኝነት በድጋሜ ወደ ክለቡ በማምጣት ጥሩ የዉድድር አመትን ለማሳለፍ ቢሞክሩም እያሳለፉት ያለዉ፡የዉድድር አመት ግን እንዳሰቡት እየሆነላቸዉ አይደለም፡፡
በፕሪሜርሊጉ አስራ ስምንት ጨዋታቸዉን አድርገዉ አስራስምንት ነጥቦችን በመያዝ አስራአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
ትላንት ያደረጉትን ጨዋታም በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል፡፡ በተቃራኒዉ ያማረ እግር ኳስን የሚጫወቱት ብራይተኖች በምሽቱ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እና የጎል ማግባት ሙከራወችን ቢያደርጉም ክሪስታል ፓላስ ላይ ሙሉ ሶስት ነጠብ ይዘዉ መዉጣት አልቻሉም፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይም ጆርዳን አዩ ለክሪስታል ፓላስ በመጀመሪያዉ የጭታ አጋማሽ ጎል ማስቆጠር ሲችል ደኒ ዉየሊቤክ ለብራይተን ከረፍት መልስ የአቻነት ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

ዛሬም ምሽት አምስት ሰዓት ላይም አስቶን ቢላ ከሸፊልድ ዩናይትድ ጭታቸዉን በቪላ ፓርክ ያደርጋሉ፡፡
አስቶን ቪላወች በኡና ኤምሬ ስር ከወትሮዉ በተለየ ጥሩ የዉድድር አመትን እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በሜዳቸዉ የሚቀመሱ አይደለም፡፡ አርሰናል እና ማንችስተርሲቲ እንኳን በቪላ ፓርክ ሽንፈትን ቀምሰዉ ተመልሰዋል፡፡
አስቶን ቪላም ዛሬ ምሽት በፕሪሜርሊጉ መጨረሻ ደረጃ ላይ የተቀመጠዉን ሺፊልድ ዩናይትድን በሜደዉ የሚያስተናግድ ይሆናል፡፡ እናም የሚያሸንፍ ከሆነ ለጊዜዉም ቢሆን ፕሪሜርሊጉን በአንደኝነት የሚመሩ ይሆናል፡፡
በተቃራኒዉ ሸፊልድ ዩናይትዶች ከሜዳቸዉ ዉጭ እስካሁን ምንም ጨዋታ ማሸነፍ አልቻሉም ፡፡ እስካሁን ድረስ 17 ጨዋታወችን አድርገዉ ማሸነፍ የቻሉት ሁለት ጨዋታወችን ብቻ ነዉ፡፡
ታዲያ እነዚህ ሁለት ክለቦች ዛሬ ምሽት በቪላ ፓርክ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡

 በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት መካከል የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታ ላይ በጋራ መስራ...
21/12/2023


በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት መካከል የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱ የ24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን እንደሚያካትትም ተመላክቷል።

በስምምነቱ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት ኢመደአ የኢንፎርሜሽንና የኢንፎርሜሽን መሠረተ-ልማት ደህንነት መጠበቅ ኃላፊነቱና ተልእኮው መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ለመንግስት ቁልፍ ተቋማትን የ24/7 የደህንነት ጥበቃ ከማድረግ ባሻገር ክልከላ ያለባቸውን ሶፍትዌሮችና ሀርድዌሮችን አበልጽጎ የማስታጠቅ ሥራን እየሠራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡

አቶ ሰለሞን አያይዘውም ዛሬ የተደረገው ሥምምነት የኢ-ፓስፖርት ሥርዓትን ከዲዛይን ጀምሮ ደህንነትን መሰረት ያደረገ የሲስተም ግንባታና የ24/7 የሳይበር ደህንነት ጥበቃ አገልግሎትን መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የሳይበር ደህንነት ኦዲት፣ አገልግሎቱ ያሉበትን የሳይበር ደህንነት ሥጋትና የተጋለጭነት ክፍተቶችን የመለየትና የመድፈን ስራዎችን በመስራት ተቋሙ የጀመረዉን በቴክኖሎጂ የመዘመን እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ለኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

የኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው ከኢመደአ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታቸው እንዳስደሰታቸዉ ገልጸዋል።

ተቋማቸው የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመን የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እና ተቋሙ በባህሪው የሚይዛቸው መረጃዎች ሚስጥራዊነት እና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከኢመደአ ጋር መሥራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ወደፊትም በርካታ ሥራዎችን በጋራና በትብብር እንደሚሰሩ ዋና ዳይሬክተሯ መግለጻቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

 ሊቨርፑል በካራባዉ ካፕ ጨዋታ  ውየስትሃምን በማሸነፍ  ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ማለፍ ችሏል፡፡ሊቨርፑል  በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በአንፊልድ ዉየስታሃምን ጋብዞ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡ በጨዋታ...
21/12/2023


ሊቨርፑል በካራባዉ ካፕ ጨዋታ ውየስትሃምን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ማለፍ ችሏል፡፡
ሊቨርፑል በሩብ ፍፃሜ ጨዋታ በአንፊልድ ዉየስታሃምን ጋብዞ በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፏል፡፡ በጨዋታዉ ሁሉም ነገር ተቆጣጥረዉ ማምሸት የቻሉት ሊቨርፑሎች መዶሻወቹ ላይ አምስት ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡
ባሳለፍነዉ እሁድ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ጨዋታቸዉን አድርገዉ 13 የጎል ሙከራወችን አድርገዉ ወደ ጎል መቀየር ግን ተስኗቸዉ ያመሹት ሊቨርፑሎች በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ግን ሁሉን ነገር አርመዉ የገቡ ይመስላል፡፡
ሊቨርፑሎች ከተደጋጋሚ ጠንካራ ሙከራወች በኅላ ዶሚኒክ ሶቦዝላይ ከ25 ያርድ አካባቢ አክርሮ የመታት ኳስ ወደ ጎልነት ስትቀየር ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ መግባታቸዉ ገና ጨዋታዉ ሳይጠናቀቅ ያስታዉቅ ነበር፡፡
ለሊቨርፑልም ኮርትስ ጆንስ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ማህመድ ሳላህ እና ኮዲ ጋክፖ ሌሎች ጎሎችን አስቆጥራዋል፡፡
ኮርትስ ጆንስ በዉድድር አመቱ የመጀመሪያዉን ሁለት ጎሎች በምሽቱ ጨዋታ ማስቆጠር ችሏል፡፡
በዚህ ጨዋታ ላይም እንግሊዚያዉዩ ባለተስፍ ወጣት ተጫወች ኢሌይት ጨዋታዉን በቋሚነት ጀምሮ ድንቅነቱን ይበልጥ በትላንትናዉ ጨዋታ አሳይቷል፡፡ ለየረገን ክሎፕም ተጨማሪ ማስረጃወችን ይበልጣ ማሳየት ችሏል፡፡
ሊቨርፑል በሜዳዉ ዉየስትሃም ላይ አምስት ጎሎችን አስቆጥሮ ለ10ኛ ጊዜ ከፍ አድርጎ ለማንሳት ትልቅ መነሳሳት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ዋንጫ ለ9ኛ ጊዜ በማንሳተም የመጀመሪያዉ ክለብ ነዉ፡፡

የዲቭድ ሞይሱ ቡድን ውየስትሃም አሳዛኝ ምሽትን አሳልፈዋል፡፡ በዚህ ጨዋታ ላይም አምስት
ጎሎችን አስተናግደዉ አንድ ጎል በጆርዳን ጎል አማካኝነት አስቆጥረዉ ከዉድድሩ ተሳንብተዋል፡፡
በወልቭስ ላይ ባደረጉት አስገራሚ ድል ለሊቨርፑልም ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆኑ የተገመተ ቢሆንም ተከታታይ ኳሶችን በማግኘት ለተቃራኒ ቡድን ስጋት የሚሆኑበትን እድል ግን መፍጠር አልቻሉም፡፡
አሰልጣኝ ዲቪድ ሞይስ ከጭዋታዉ መጠናቀቅ በኅላ በሰጡት አስተያይትም አፈፃፅማችን በጣም ጥሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያ ደቂቃ ጀምሮ የመተንፈስ ዕድል አላገኘንም፡፡ የተጫወትነዉ በጣም ፍጥነት የተሞላበት ጨዋታ ነበር በማለት አስተያይታቸዉን ሰጠዋል፡፡
ሊቨርፑል ፣ፉልሃም ፣ቼልሲ እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ ክለቦች ሲሆኑ ሊቨርፑል በግማሽ ፍፃሜዉ ጨዋታም በመለያ ምት ኤቨርተንን አሸንፎ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍ የቻለዉን ፍልሃምን የሚያገኝ ይሆናል፡፡ ጨዋታዉም ጥር ስምንት የሚደረግ ይሆናል፡፡ ከሁለት ሳምንት በኅላም የፍፃሜዉ ጨዋታ ይደረጋል፡፡

 የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን ምክክር መድረክ በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል****(ኢ ፕ ድ) በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የአፍሪካ ሀገራት ቴክኖሎጂ...
20/12/2023


የአፍሪካ ሀገራት የኤሌክትሮኒክ አስተዳደርና የዲጂታላይዜሽን ምክክር መድረክ በሩሲያ እየተካሄደ ይገኛል
****
(ኢ ፕ ድ)

በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው መድረክ የአፍሪካ ሀገራት ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሀገራቸው የሚካሄደውን የኢኮኖሚ ስርዓት ለማዘመን የሄዱበትን የስኬት ጉዞና ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ለሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ተሞክሮ ይቀርብበታል።

ኢትዮጵያን ወክለው በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ውባየሁ ማሞ (ኢ/ር) የኢትዮጵያን የዲጂታል መታወቂያ አሰጣጥ፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይቶችንና ኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት በተሞክሮነት አቅርበዋል።

በጉባዔው የአፍሪካ ሀገራት ከሩሲያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ተሞክሮዎችን በመውሰድ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን ተግባራዊ ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ 37 የአፍሪካ ሀገራት ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።

 ትላንት በተደረገ የካራባዉ ካፕ ጨዋታ ቼልሴ ፤ፉልሃም እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍቸዉን አረጋግጠዋል፡፡በካራባዉ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ትላንት  ሶስት መርሃ ግብሮች የተካሂዱ ሲሆ...
20/12/2023


ትላንት በተደረገ የካራባዉ ካፕ ጨዋታ ቼልሴ ፤ፉልሃም እና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ማለፍቸዉን አረጋግጠዋል፡፡
በካራባዉ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ትላንት ሶስት መርሃ ግብሮች የተካሂዱ ሲሆን ቼልሲ ፣ ፉልሃምና ሚድልስቦሮዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉ ክለቦች መሆን ችለዋል፡፡
ከተጠባቂ መርሃ ግብሮች መካከል የነበረዉ የቼልሲ እና የኒዉካስትል ዩናይትድ ጨዋታም በመለያ ምት ቼልሲወች አሸንፈዉ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችለዋል፡፡
ኒዉካስትል ዩናይትድች በዚህ ጨዋታ ላይ ዊልሰን ቀድሞ ባስቆጠራት ጎል ቀድመዉ መሪ የሆኑበትን እድል ቢያገኙም ቼልሲወች ደቂቃወች ሊጠናቀቁ በሰከንዶች ልዩነት ጎል አስቆጥረዉ ወደ ጭማሪ ደቂቃ ያለፈበትን እድል ማስተካከል ችለዋል፡፡ ሙሉ የጭዋታዉ ጊዜ በአንድ አቻ የተጠናቀቀዉ ይህ ጨዋታም በመጨረሻም ቼልሲወች በመለያ ምት አሸንፈዉ ግማሽ ፍፃሜዉን ተቀላቅለዋል፡፡
ሌላኛዉ መርሃግብር የኢቨርተን እና የፉልሃም ጨዋታ በተመሳሳይ በመለያ ምት የተጠናቀቀ መርሃ ግብር ነበር፡፡
ኤቨርተኖች የፍይናሻል ፊር ፕላይ ህግን በመጣሳቸዉ አስር ነጥብ ከተቀነሰባቸዉ በኅላ ይበልጥ ጠንካራ ሆነዉ ለመቅረብ እየታገሉ ይገኛሉ ፡፡ በምሽቱ ጨዋታም ማይክል ኪን በራሱ መረብ ላይ ከረፍት በፊት ጎል አስቆጥሮ ፍልሃሞችን መሪ ያደረገ ቢሆንም ቤቶ በመጨረሻም ለኢቨርተን ጎል አስቆጥሮ ወደ ጭማሪ ደቂቃ ማምራት ችለዉ ነበር ፡፡ ጭማሪ ደቂቃወች ጨርሰዉ ወደ ፔናሊቲ ያመሩት ሁለቱ ክለቦች ኦናና እና ጎዩ የኢቨርተንን ሁለት ፔናሊቲወችን አምክነዉ ፍልሃሞች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ሲያልፉ በተቃራኒዉ ኢቨርተኖች ወደ ግማሽ ፍፃሜዉ ሳያልፉ ቀርተዋል፡፡
ሜድልስቦሮዉ እና ፓርት ቫሊ ያደረጉት ጨዋታ በሚድልስቦሮዉ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ዛሬም በካራባዉ ካፕ ሩብ ፋፃሜ ጨዋታ አንድ ቀሪ መርሃ ግብር ይደረጋል፡፡ በዚህ ጨዋታም ሊቨርፑል ዊስትሃምን በአንፊልድ ይጋብዛል፡፡ ሊቨርፑል በዘንድሮዉ የዉድድር አመት ወደ ሻንፒወን ሽፑ የተወረወረዉን ሊስተርሲቲን አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜዉ ማለፉ ይታወሳል፡፡ የሊግ ዋንጫዉን ያነሳል ተብሎ ከሚገመቱ ክለቦች መካከል የየርገን ክሎፕ ቡድን የመጀመሪያዉ ነዉ፡፡ በተቃራኒዉ ውስትሃም ዩናይትድ የሊቨር ፑል ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆን ይጠበቃል ፡፡ ጠንካራዉን አርሰናልን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፎ ወደ ሩብ ፍፃሜዉ ማለፉ ይታወሳል፡፡ ታዲያ ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ በአንፊልድ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የሚፍለሙ ይሆናል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

http://tiktok.com/@gohetv0

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gohe Tv Broadcasting service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gohe Tv Broadcasting service:

Share

Category