Ethiopian illuminati

Ethiopian illuminati Reporting Daily ongoing Ethiopian News

06/05/2025
13/05/2024
ሰበር መረጃየጃውሳ ታጣቂዎች የታጠቁትን መሳሪያ እየሸጡ መሸሽ መጀመራቸው ታውቋል!በዘመነ እና ማስረሻ ሰጤ መካከል የሚደረገው ጦርነት ተስፋ ያስቆረጣቸው የቡድኑ አስተባባሪዎች ከሚመሯቸው ታጣቂ...
09/05/2024

ሰበር መረጃ

የጃውሳ ታጣቂዎች የታጠቁትን መሳሪያ እየሸጡ መሸሽ መጀመራቸው ታውቋል!

በዘመነ እና ማስረሻ ሰጤ መካከል የሚደረገው ጦርነት ተስፋ ያስቆረጣቸው የቡድኑ አስተባባሪዎች ከሚመሯቸው ታጣቂዎች መሳሪያ እየቀሙ በመሸጥ ላይ እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በዚህም ዘመነ ሆነ አስረስ ለግል ፍላጎታቸው ነው የሚንቀሳቀሱት የሚሉት እነዚህ ታጣቂዎች የያዙትን እና ከስራቸው ያሉ ታጣቂዎች የታጠቁትን መሳሪያ ጭምር በመሸጥ ቡዱኑን መክዳት መጀመራቸው ታውቋል።

የሚገርመው የአባትህ ንብረት ሲዘረፍ አብረህ ዘርፍ ነው አባባሉ ሲሉ የተደመጡትም መኖራቸው ጃውሳ ምን ያህል በእንቅስቃሴው ተስፋ እንደቆረጠ የሚያመላክት ከመሆኑ በላይ ቡድኑ ለሌብነት ዓላማ የተደራጀ የሰፈር ሽፍታ መሆኑንም ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ጃውሳ “ያልታወቁ ሃይሎች” በሚል የሚፈፅመው ግድያ ህዝቡን እያገዳደለው ይገኛል!  ጃውሳ ለህዝብ የአይን ብሌን የሆኑ መምህራንን፣ የጤና ሰራተኞችን እንዲሁም ለህዝብ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የ...
07/05/2024

ጃውሳ “ያልታወቁ ሃይሎች” በሚል የሚፈፅመው ግድያ ህዝቡን እያገዳደለው ይገኛል!

ጃውሳ ለህዝብ የአይን ብሌን የሆኑ መምህራንን፣ የጤና ሰራተኞችን እንዲሁም ለህዝብ ማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ዜጎችን አሳድዶ በመግደል እና ከነርሱ ጋር የስጋ ዝምድና ያላቸው ሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ ማህበረሰብን የሚያሳዝን ተግባር ከመፈፀሙም ባሻገር ህዝብ እርስ በእርስ በጥርጣሬ አይን እንዲተያይ እያደረገ ነው። ይህ የፀረ ሰላም ሃይል በወሎ ደላንታ አከባቢ ከመንግስት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል የሚፈፅመው የሽብር ጥቃት የአካባቢውን ህዝብ እርስ በርስ እያባላ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም በደጋ ዳሞት አካባቢ አንድን ግለሰብ የመንግስት ሰራተኛ ነው በሚል መግደሉ የአካባቢው ማህበረሰብ “ደም የመመለስ” የሚል ዘመቻ አድርጎ እርስ በርስ እንዲገዳደል ማድረጉ ይታወሳል። ይህ ነገር ገደብ ካልተበጀለት እና በዚህ ከቀጠለ ህዝቡ ማብቂያ የሌለው ጦርነት ውስጥ እንደሚገባ የጃውሳ ሚዲያዎች ጭምር ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛል።

ህዝብን ያስካደው የጃውሳ የገንዘብ ፍቅር!  እንደሌላው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ ጃውሳው በላስታም ተመሳሳይ የሽብር ድርጊቱን በማን አለብኝነት እየፈፀመ ይገኛል።  ወንድሙ ማሩ የተባለ በ...
28/04/2024

ህዝብን ያስካደው የጃውሳ የገንዘብ ፍቅር!

እንደሌላው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ ጃውሳው በላስታም ተመሳሳይ የሽብር ድርጊቱን በማን አለብኝነት እየፈፀመ ይገኛል።

ወንድሙ ማሩ የተባለ በላስታ ላሊበላ አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን ፀረ ሰላም ሀይል የሚመራ ግለሰብ በህዝብ ስም ገንዘብ እየሰበሰበ ለግል ጥቅሙ እንደሚያውለው ታውቋል።

ይህ የሽብር ቡድኑ ክንፍ ከዳያስፖራው ምንም አይነት ድጋፍ እየተደረገልኝ አይደለም በሚል ተቃውሞ እያሰማ ሲሆን ተቃውሞውንም እየመራ ያለው ወንድሙ ማሩ የተባለው ግለሰብ ነው።

የወሎ እዝ በሚል የሚንቀሳቀሰው የጃውሳ ክንፍ አባል የነበረው ወንድሙ ከዚህኛው አደረጃጀት እንዳሰበው መጠቀም ባለመቻሉ ፋንታሁን ሙሃቤን በመክዳት የተቀናቃኙን ምሬ ቡድን ተቀላቅሏል። ቢሆንም ግን ከምሬ ወዳጆም ተቀባይነት በማጣት አተርፍ ባይ አጉዳይ የሆነው ግለሰቡ አሁን ደግሞ የላስታ ላሊበላ ህዝብ ለርሀብ ተጋልጧል በሚል አዲስ ዲስኩር ከፅንፈኛው ዳያስፖራው ጋር በመመሳጠር ገንዘብ የመሰብሰብ እንቅስቃሴ መጀመሩ ታውቋል።

ወንድሙ ይሄን ሁሉ ሴራ ሲጎነጉን ከኮሎኔል ፋንታሁንም ሆነ ምሬ እውቅና ውጪ ሲሆን እንዳይሰሙም ሚስጥር አድርጎ የያዘ ቢሆንም አንድ የምሬ ሰው መረጃውን አጋልጦበታል። በዚህም ምሬ እና ኮሎኔል ፋንታሁን በየፊናቸው ወንድሙን በእግር በፈረስ ማሳደድ ጀምረዋል።

ወንድሙ ከተሳካለትና ያሰበውን ያህል ገንዘብ መሰብሰብ ከቻለ ቡድኑን በመክዳት በገንዘቡ የራሱን ህይወት የማደላደል ድብቅ ፍላጎት እንዳለው እየወጡ ያሉ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በሸዋ ግሸር አቤ አርሶ አደር ላይ ጽንፈኛው ቡድን ጥቃት ፈጸመ!በፋኖ ስም የአማራ ህዝብን እየዘረፈ የሚገኘው ጽንፈኛው ጃውሳ ከዝርፊያ ባለፈ በምስኪኑ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል እና ሲቃ ...
25/04/2024

በሸዋ ግሸር አቤ አርሶ አደር ላይ ጽንፈኛው ቡድን ጥቃት ፈጸመ!

በፋኖ ስም የአማራ ህዝብን እየዘረፈ የሚገኘው ጽንፈኛው ጃውሳ ከዝርፊያ ባለፈ በምስኪኑ ህዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል እና ሲቃ ይሄ ነው የሚባል አይደለም። ከሰሞኑን በሸዋ ግሸር አቤ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው በመከታው ማሞ የሚመራው ታጣቂ ሃይል በምስኪኑ አርሶ አደር ላይ አስነዋሪ ተግባር ፈጽሟል።

ጃውሳው በሸዋ ግሸር አቤ ከሚኖሩ አርሷ አደሮች ወደ 60 የሚጠጉ በሬዎችን በመዝረፍ ከህዝቡ ባህል እና እምነት ባፈነገጠ መንገድ በአብይ ጾም ወቅት ማረዱን የመከታው ተቀናቃኝ የሆነው አሰግድ ከታጣቂዎቹ ጋር ባደረገው ስብሰባ ላይ ሲናገር ተሰምቷል።

በመከታው ማሞ እና በአሰግድ የእርስ በርስ ጸብ አንዱ የአንዱን ጉድ ማጋለጥ ከጀመሩ የሰነባበቱ ሲሆን አሰግድ በዚህ መልኩ መከታው ማሞ ያደረገውን አስነዋሪ ተግባር በአንደበቱ በየአደባባዩ እየተናገረ ይገኛል።

በእነዚህ ጽንፈኞች ምስኪኑ አርሶ አደር አንዴ የደረሰ ሰብል በክምር እንዳለ ሲቃጠልበት ባስ ሲል ደግሞ ጥማድ በሬው ሲዘረፍበት ስናይ ጃውሳ
የሚያደርገው ግፍ አሸባሪ የሚል ስም የሚያሰጥ አረመኔያዊ ተግባር ነው እንላለን።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian illuminati posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share