Eyob Media Agency

Eyob Media Agency Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Eyob Media Agency, Media/News Company, Addis Ababa.
(1)

13/09/2023

2016 አዲስ አመት የሠላም፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንልዎ እንመኛለል!
መልካም 🌼🌼🌼 አዲስ 🌼🌼🌼 አመት 🌼🌼🌼 2016 "አዲስ ዓመት አዲስ ህይወት"

28/08/2023

ቁምነገሩ የማንም ዜጋ ሀገሩን የሚወደውና የሚጠብቃት ብሎም ለእድገቷ የተቻለውን ማድረግ ያለበት ለመሪዎቿ አልያም ሌላውን ለማስደሰት ሳይሆን የዜግነት ግዴታውን ለመወጣት እደሆነ ማመንና ኃላፊነት ሊሰማው ይገባል ፤ "ፈጣሪ ሆይ ሀገራችንን ጠብቅልኝ፤
Eyob Media Agency
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 22_2015 ዓ.ም

09/12/2022

ትኩረት
ሸኔ ማነው ? ምንስ ይፈልጋል ?
ቀደም ሲል ህወኃት በስልጣን ዘመኑ ከነበረው የረዥም ጊዜ እቅዱ ዋነኛው ኢትዮጵያን በዘርና በሐይማኖት በመከፋፈል ብሄር ተኮር ግጭችን፤ የድንበር ወሰን ግጭቶችንና ሐይማኖታዊ አለመግባባቶን በመቀስ በዚህ ሽፋን በሀገሪቱ ሀብት ታላቋ ትግራይን የመመስረት ሀገር ሆኖ የመተዳደርና የማስተዳደር ህልም እንደነበረው በተግባምርም ያየነውና በወጡ መረጃዎችም የተረዳነው እውነት
ነው ። በዋናነት ደግሞ አማራና ኦሮሞ በማንኛውም አቅጣጫ እንዳይስማሙና እንደጠላት ተያይተው እንዲኖሩ ማድረግ የስኬታቸው መንገድ እንደሆነ ተልመው ሲሰሩበት ቆይተዋል
አሁንም እየሰሩበት ይገኛሉ ።
ለዚህ ደግሞ ዋነኛው መሳሪያ እሾህን በሾህ እንዲሉ
ህወኃቶች በአገዛዝ ዘመናቸው ብዙ የትግራይ ወጣቶችን ኦሮሚያ ባሉ ቋንቋና የንግግር ዘይቤ ወግና ባህልን ያካተተ ትምህርት በሺዎች ለሚቆጠሩ ትውልደ ትግራይ ወጣቶችን አስተምረው እንደተዘጋጁበትና ከውጊያው ጎን ለጎን በትግራይ ሰላም ሰፍኖ በሀገሪቱ አጠቃላይ ከተሞች ግን መልኩን የቀያየረ ብጥብጥና እልቂት ብሎም የንብረት ውድመቶች በዚሁ ቡድን መሪነት በተፈፀሙ አስከፊ ተግባሮች ስንተራመስ ቆይተናል ።
ዛሬ በኦሮሚያ ትርምስና ብሄር ተኮር ግጭቶችን፤ ግድያና ማፈናቀልን ስራዬ ብለው የተያያዙት እነዚሁ ቡድኖች በመሆናቸው የተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ቀጥተኛው ሲሆን ዋነኛው ግን በሸኔ ስያሜ በእጅ አዙር ስራውን እየሰራ እንደሆነ ጥርጣሬ የሚያጭር ብቻ ሳይሆን ትክክለኛነቱንም የሚያሳይ የሽብር ተግባርም ስለሆነ ለይተን ልንገታው የምንችለው ከባድ የሚመስል ነገር ግን ቀላል ጉዳይ እንደሆነ ያመላክታል ።
ምናልባት ከመግስት አቅጫጫ ያለውን መገመት ባይቻልም አብዘኃኛው ማህበረሰባችን ያለው ግንዛቤ ጭፍጨፋ እገታና ዘረፋው በኦሮምኛ ተናጋሪዎች እየተከወነ ከመሆኑ ጋር በማነፃፀር የኦሮሞ ኦነግ ሸኔ እንደሆነ በማሰብ የተሳሳተ ግንዛቤ ላይ ተደርሷል ።
በገሀድ እንደምንሰማውና ችግር ፈጣሪው ኦነግ ሸኔ እንደሆነ ቢያመላክትም እውነቱ ግን የኦሮሞ ተወካይ ኦነግ ሸኔ ብቻ እንዳልሆነ እየጠቆምን ልንገነዘበው የሚገባን ይህ ቡድን የኦሮሞን ህዝብ የማይወክልና ኦሮሞ በባህሉ ሰው ወዳድ እንግዳ ተቀባይ ከብሔርና ብሔረሰቦች ጋር ተጋምዶ ተዋልዶ የኖረና እየኖረ ያለ ኩሩ ብሔር ከመሆኑም በላይ በኢትዮጵያ ከኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነትና በመተሳሰብ የመኖርን ሀገራዊ እሳቤ የተጎናፀፈ ህዝብ ለመሆኑ በቃለ መሀላ እንዲረጋገጥለት የሚፈልግ አካል ያለ አይመስለንም ።
ከዚህ አንፃር ምሁራንና የኢትዮጵያና ዜጎቿ ጉዳይ ይመለከተናል የምንል በተለይ የፖለቲካ ፖርቲዎች ሁላችንም የችግሩን ፈጣሪና ባለቤቶች በጥሞና በመመርመርና በስልታዊ ጥናት እውነቱን እስከምናገኘው ድረስ በየምንሰጠውን አስተያየት ትችትና ትንታኔ ሚዛን በሚደፋና ጥንቃቄ በተሞላበት እይታ ዘግበን ማስተላለፍ ስንችል የእርስ ግጥጭት በአለበት እንዲገታና ማህበረሰቡ ነቅቶና ተሳትፎበት ሽብርተኛውና ሽብር ፈጣሪው በቀላሉ ተለይቶ ሰላማችን ሊረጋገጥ እንደሚችል ለመጠቆም እንወዳለን ።
በተለይ የፖለቲካ ፓርቲ ማለት በአመለካከት የተለየ ግን ኢትዮጵያዊ የሆነና ነገ ለሀገሩና ዜጎች የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የሚታገል እንጂ ጎራ የሚለይ በብሄርተኝነት ልክፍት የታወከ ችግሮችን እየነቀሰና እያውለበለበ መታወቂያ ማግኘት የሚፈልግ ከሆነ እንኳን ለሀገር ለራሱም መጥፊያው ከመሆን የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም ።
ይልቁንስ ችግሮችን አነፍንፎ ከማጋለጥ ባሻገር የመፍትሄ አቅጣጫ በመስጠትና የሰላም አስከባሪነቱን ዘመቻ ተቀላቅሎ ከሚዲያ ፍጆታ ባሻገር በተግባር ተሳትፎ ህዝባዊ አለኝታነትን ማረጋገጡ ቅስቀሳ የማያስፈልገው ቅቡልነትን የሚያረጋግጥልንና ተስፋ የሚጣልበት ታጋይ ለመሆን የሚያበቃን ከመሆኑም በላይ ታማኝነትና ህዝባዊ ውክልና ሊያሰጠን የሚያስችል ቀናና አቋሯጭ መንገድ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ሀቅ ይሆናል ።
የክልሉ መንግስትና የፌደራሉን መንግስት
ከዚህ ችግር ጋር ለማያያዝ የሚደረገው ርብርብ ከስልጣን ጥም የመነጨና አጉል ብሔር ተኮር ጥላቻ ከመሆን አልፎ ለዜጎች ሰላምና ደህንነት ከመቆርቆር የመነጨ አስተሳሰብ እንዳልሆነ ግልፅ ነው ።
ምክንያቱም መንግስት በራሱ አገዛዝ ላይ እሳት ጭሮ ዜጎቹን እርስ በርስ ያፋጃል ማለት ከእብደት የሚመነጭ ሐሳብ እንጂ የጤናማ አስተሳሰብ ውጤት ነው ማለት በራሱ እብደት ስለሚሆን ነው ።
ይህ ማለት ግን ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በዘረፋና ሌብነት የተሰማሩ የሉም ማለት እንዳልሆነና ሌባና ዘራፊ ደግሞ ብሔር እንደማይለይ ሊሰመርበት የሚገባና በመንግስ መስሪያ ቤቶችም ጭምር ባንዳና የባንዳው ተላላኪ ሆዳሞች በት/ርት ቤቶችም ጭምር በባንዲራና መዝሙር ሰበብ እሳቱን በየከተማው እሳት ለማቀጣጠል የነደፉት ስልትና የመንግስት እጅ እንዳለበት የሚያስመስል ምስል እንዲይዝና ህዝባዊ አመፅ ማስነሳት እንዲያስችል ተቀምሮ የተሰራ እኩይ ተግባር እንጂ ህጋዊ አካል አቅዶ እያስፈፀመው ነው ብለን ካሰብን ተሳስተን በማሳሳት አልያም ሆን ብለን የአጥፊዎቹ መሳሪያ ሆነናል ማለት ነው ። ምናልባት ቀደም ሲል ሲነሳና መነጋገሪያ ሆኖ መጨረሻው እየተጠበቀ ያለው የአ/አበባ /ፊንፊኔ/ከተማን በኦሮሚያ የማካተት እቅድ አለ ተብሎ ሲናፈስ ከነበረው ወሬ ጋር አገናኝተነው ቢሆን እንኳን የዚህ ጥያቄ አጫሪዎች በራሳቸው የሽብርተኛው ቡድን ፖለቲከኞች ሀሳብ እንጂ የመንግትና የህዝብ ተወካዮች እውቅና የሌለው ከመሆኑም በላይ የሀገር ርዕሰ መዲናን በዚህ ደረዳ አውርዶ ማየት በራሱ በወሬ የምንነዳ ተላላዎች መብዛታችንን የሚሳይ እይታ ብቻ ነው የሚሆነው ።
በጥቅሉ መንግስት በየመስሪያ ቤቱ የተሰገሰጉ ባንዳዎችን መንጥሮ ለማውጣት የሚያስችል ስልት በመቀየስ ዜጎች በተሳሳተ መረጃ እንዳይሸበሩ በሚዲያም ጭምር በትኩረት እንዲሰራበት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን እየጠቆምን በአጭር ጊዜና በቀላሉ ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ የሚቻለው የኛ የዜጎች ተሳትፎና አጋርነት የአንበሳውን ድርሻ አንደያዘ አውቀን ችግር ፈጣሪዎችን በመጠቆምና በማጋለጥ በቀጥታ የዘመቻው ተሳታፊ ስንሆን ችግሩን ከምንጩ በማድረቅ ሰላማችንን ለማረጋገጥ ያስችለናል የሚል እምነት አለን ።
Eyob Media Agency
"ሰላምና ብልፅግና ለኢትዮጵያ"
ህዳር 29-2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

18/11/2022

የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር
በወኔ ቢስ ትውልድ ሲዘመር

በቀደመው ታሪክ ለስልጣኔ በር
የኢትዮጵያ አንድነት ጽኑ ግምብ ነበር
ዜጎች በክብራችን የማንደራደር
ለጠላት ፍም እሳት የዳር ድንበር አጥር
በብዝሀ አንድነት የቀለማት ህብር
ደምቆ ህዝባዊነት እናበራ ነበር

በሰላም በፍትህ በአንድነት ጉዞአችንን
ሆ ብለን ዘምተን ነው ዛሬን ማየታችን
ለነፃነት ወድቀን ለእናት ሀገራችን
የድል ችቦ በርቶ በዓም መግነናችን
አድዋ ምስክር ህያው ታሪካችን

ድንቅ የባህል ውበት የአኩሪ ድል ባለቤት
የተፈጥሮ ፀጋ የጀግኖች ህዝብ እናት

ከአበው ተረክበን ሰጥተውን አደራ
ለምድና ጋሻ ጦር ተሰቅሎ ከጣራ
ትውልድሽ ተኝተን በሸረሪት ደራ
ሀሞተ ቢስ ወጣት ልበቢስ ወጣራ
መንደር ውሎ አዳሪ ዱሩን የምንፈራ
እንዴት በኛ ኮርተሽ እኛስ በአንቺ እንኩራ

ዛሬ.......
በአንድነት በፍቅር መኖር ትተንልሽ
ስለ ሰፈር ሆኗል እሳቤው ትውልድሽ
ይሄ ነው እማማ ታሪኩን ስነግርሽ
ሳንቃው ዝቅዝቅ ብሎ ከላይ ከጉበንሽ
ግድግዳው ዘመመ ጣራው ወድቆ ቤትሽ
ክረምትና በጋው ቢፈራረቁብሽ
ሀገሬ ቁርና ቸነፈር ገረፈሽ
ሀገሬ ከጂና ሆዳሙ ከበበሽ

አሁን ከምነግሽ እጅግ የሚገርመው
አቤልን ቃኤልን ትውልድሽ ደገመው
የሰው ደም እንደ ጎርፍ ምድርሽን በከለው
አኩሪ ታሪክሽን ቂም ጥላሸት ቀባው
ደም በደመ ተቃብተን እሳት ነው ጠባሳው

የስጋ ልባች ደንድኖ አንደ ዋዛ
እውነትና እምነት ረገፈ እንደጤዛ
አምላክን በክህደት ሰይጥነን ልንገዛ
ሐይማኖት ቅጥ አጣ ምድርቱን ገዛ
ጭካኔአችን ቢብስ አሳራችን በዛ

እንሰማው ናፈቀን የሚጥመን ወሬ
ረሃብ ማስታገሻ ለጉርስ እፍኝ ጥሬ
ኑሮ መሮ ኮሶ ለብላቢ በርበሬ
ጉዞአችን ወዴት ነው ንገሪኝ ሀገሬ

ተነስ የሀገሬ ሰው ትውልድ ሆይ ንቃ
ዘር ጥራጥሬ እንጂ ሰው መሆኑ ይብቃ
በምነትህ ጠጅ ጥና በፀሎት በሲቃ
ከአንድ አምላክ ታረቅ ለንስሃ ብቃ
አንድነት እምነት ነው ለድል የሚያበቃ
ያበረ ክንድ ነው ጠላት የሚደቃ

አዘጋጅና ገጣሚ ኢዮብ...
Eyob Media Agency
ህዳር 09/2015
አዲስ አበባ

በመላው ዓለም የሚገኙ 17 የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጥምረት አባላት በድርድሩ ውጤት ላይ ያልተገባ ጫና ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን ተግባር እየተቃወሙ እንደሆነ እየሰማን ነው ። የበኩላቸውን የ...
30/10/2022

በመላው ዓለም የሚገኙ 17 የዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጥምረት አባላት በድርድሩ ውጤት ላይ ያልተገባ ጫና ለመፍጠር የሚሞክሩ አካላትን ተግባር እየተቃወሙ እንደሆነ እየሰማን ነው ። የበኩላቸውን የዜግነት ድርሻና ሀገራዊ ግዴታቸውን እየተወጡ ከመሆናቸውም በላይ ኢትዮጵያዊ ማለትን በሉዓላዊነቱ የማይደራደር ርቀትና አሰፋፈር የማይገታው ሀገር ወዳድ ጀግኖች መሆናችንን ለዓለም ጠላቶቻችን ያሳወቁበትና ያስጠነቀቁበትም ጭምር ነው ። አዚህ ሀገር ቤት ያለነው ኢትዮጵያንም ቀጣይነት ባለው ትግል እስከማጠቃለያው ድረስ ህዝባዊ የሰላም ማስከበር ሂደት ላይ መሆናችንን የሚያስረዳና አይበገሬነታችንን አውቀው ከሀገራችን ላይ እዳቸውን እንዲያነሱና ዳግም በኛ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ መደምደሚያ ላይ የሚያደርሳቸውን ትግል ልናቋርጥ አይገባምና ከታች በምስሉ እንደምናየው ጀግኖች ልጆቻችን አየተዋደቁ ነውና እኛም ባለፈው ንቅናቄአችን ሳንወሰን የተጀመረውን ንቅናቄ ማስቀጠል ይኖርብናል እንላለን ።
Eyob Media Agency
ጥቅምት 20-2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

27/10/2022

ኢትዮጵያን መረኳት

ሀገሬ ሀገሬ እምዬ ኢትዮጵያ
የስልጣኔ በር የጀግኖች መፍለቂያ
ፈለገ ጊዮኔ ጥበብ መታወቂያ

ዘመኑ ይዋጅሽ ሀገሬ ግፊበት
ጉዞሽንም ቀኝ ይሁን ድል ተላበሽበት
ሰንደቅ ሆነሽ ታይ ሰልፍሽ ይሁን ከፊት
የዘራሽ ያፍራ ምርት ይታፈስበት
ጓዳሽ ሙሉ ይሁን በረከት ይግባበት
ሠላምሽን ያብዛው ምድርሽ ይሁን ገነት

ገዜው ይታዘዝሽ ግዛትሽ ይስፋፋ
በክፉ የሚያይሽ ጠላትሽ ይደፋ
ህዝብሽ አንድ ይሁን ተንኮለኛሽ የጥፋ

መከራ ችግር እንዳልነበር ይሁን
ንፋስ የሚያርቀው አመድ ይሁን ይብነን
ድምፅሽ በታኝ መብረቅ ከንፋስም ይፍጠን
ወዳጅሽን ጠብቆ ጠላትሽን ያዳፍን
ይጥፈ ያልሽ ይጥፋ ይሁን የልሽው ይሁን
"አሜን"
Eyob Media Agency
ጥቅምት 17/2015
አዲስ አበባ

25/10/2022

አዋሽ ባንክ የመጀመሪያው ፈር ቀዳጅ ህዝባዊ ባንክ,
ቴክኖሎጂውን እግር በእግር እየተከተለ አሰራሩን እያዘመነ በቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት ሰጪነቱ የተመረጠ የዘመኑ ተደራሽ ባንክ ነው ። በየትኛው የባንኩ ቅርንጫፎች የሚሰጡ አገልግሎቶች የሰራተኞቹን አቀባበልና ትህትህና ብሎም ፈጣን መስተንግዶ ጋር ተዳምሮ የባንኩን ተመራጭነት ከፍታ ላይ እንዲታይ አድርጎታል ።
በዚህ አጋጣሚ ለማመስገንና ለማድነቅ የምፈልገው የወላጆችን ለህፃናት የቁጠባ ባህል ለማዳበርና ነገን ዛሬ እንዲገነቡ ለማበረታታት ለህፃናት ቡክ ሲከፍቱ አዋሽ ደግሞ 400 ብር ከኔ ብሎ ቤተሰባዊነቱን ያረጋገጠበትን አሰራር ሳናደንቅ አናልፍ ።
ከባንክ ሁሉ ምርጫ
አዋሽ አለው ብልጫ

ኢትዮጵያ በጥቂት ዓመታት የለውጡ ሂደት ያሳለፈቻቸው የመከራ ጊዜያቶች ቀላል የሚባሉ አይደሉም። በሰላምም ሆነ በኢኮኖሚው ከፍተኛ ቀውስ ተፈጥሯል ። ነገር ግን የተበተነ ዘር ከመሰብሰብና ያልተ...
25/10/2022

ኢትዮጵያ በጥቂት ዓመታት የለውጡ ሂደት ያሳለፈቻቸው የመከራ ጊዜያቶች ቀላል የሚባሉ አይደሉም። በሰላምም ሆነ በኢኮኖሚው ከፍተኛ ቀውስ ተፈጥሯል ።
ነገር ግን የተበተነ ዘር ከመሰብሰብና ያልተጣራ ውስብስብ ጉዳዮችን ከመፍታት ጀምሮ በጥቂት ሀገር ወዳድ ጀግና መሪዎች ከመፈራረስና ከእርስ በዕርስ ጭፍጨፋ ተርፈናል።
በልማትና ኢኮኖሚው ዘርፍ በሳይንስ ቴክኖሎጂው መስክ ደግሞ በዘመናት ያልታዩ ለውጦች ተመዝግበዋል። ከዚህ አስከፊ የሀገር ውስጥና የውጪው ጫና ጎን ለጎን ስንመለከተው የስልጣን ሽግግሩ ሂደት ሰላማዊነቱን ጠብቆ በአንድ ልብ ወደ ልማትና ኢኮኖሚ ግንባታ ፊታችንን አዙረን ቢሆን ኖሮ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከ 27% ያላነሰ እድገት ይመዘገብ እንደነበር ይገመታል ። በቀላሉ ለሰላም ማስከበርና ከተፈናቃዮች መሰረታዊ አቅርቦት ጀምሮ እስከ መልሶ ማቋቋም ድረስ የነበረውን ወጪ የህዝብና ተቋማትን ድጋፍ ሳንጨምር የመንግስ ወጪ ብቻውን ቀላል የሚባል አይደለም ። በጦርነቱ የወደመውንና መልሶ ለመገንባት እየወጣ ያለው ስናካትተው የሀገሪቱን እድገት ሁለት አስተ ዓመታት ያህል ወደኃላ እንደጎተተን ይገመታል ። ብዙ ችግሮች እንዳሳለፍነው ብዙ ለውጥና እድገቶችም ተመዝግበዋል። አሁን የሚፈለገውና ዋናው ጉዳይ የሀገሪቱ የዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ዘመቻ 85 % በላይ ተከናውኖ የማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ከተደረሰበት እውነታ በመነሳት ለመገመት የሚከብድ ጉዳይ አይደለም ። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን የጀመርነውን እስከምንቋጭ ከመንግስትና ሰላም አስከባሪው ኃይላችን ጎን በመቆም እያደረግን ያለውን ድጋፍና አብሮነት አጠናክረን ልንቀጥልበት ይገባል እንላለን ።
Eyob Media Agency
ጥቅምት 15/2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Eyob Media Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share