Buche Yogo

Buche Yogo Make better life for You !

29/09/2025

"የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።” ዘፍጥረት 4፥10

ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ቀናበት፤ ገደለውም :: በዚህም የተቆጣው ፈጣሪ “አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ” አለው።

ይህ ድርጊትና እርግማን ዛሬ በምድራችን ላይ እየተፈፀመ እናያለን።

28/09/2025

በጣም ከገረመኝ ነገሮች አንዱ የምን ልዑላዊነት ነው :- ሻቢያ ይግባ እንጅ: ወንድም ሕዝብ ነው: የህልውና ጉዳይ ነው: ሀገር እንዳትፈርስ ነው...ወዘተ ስሉ የቆዩ ሁሉ አሁን ዞሮ ደግሞ የችግራችን ምንጭ ሻብያ ነው እያሉን ናቸው🤔

28/09/2025

የታደሉ ሕዝቦች መርዎቻቸውን በምርጫ ኮሮጆ ይመርጣሉ:: ጥፋት ከሰሩ ወይም ግዜውን ከጨረሱ ሥልጣኑን ለሕዝብ አስረክቦ ይወርዳሉ:: እኛ ሀገር ግን በስሜ ድርጅት ሽፋን ንጉስ ይሾማል:- ይሻራልም:: የሚገርመው ይህ ብቻ አይደለም:: ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን ንጉሥና ሎሌው ከተቀያየሙ ሎሌው ሽምግልና ይልካል:: ሽማግሌዎቹም የሚያስፈልጋቸው ነገር ሁሉ ተሟልቶላቸው ወደ ንጉሱ ብሮ ይሄዳሉ:: ሽምግልናው ለእርቅና ለሕዝቦች ጉዳይ ብሆን: አዎ ክብር አለው:: ነገር ግን የሎሌውን ሥልጣን ዘመን ለማራዘም ብቻ ስሆን ግን ያስታዝባል:: በባህላችን ሽማግሌዎች ከፈጣሪ በታች የሚከበሩ ናቸው:- ምክንያቱም እውነቱን ስለሚናገሩና ስለምፈርዱ ነው:: አሁን ግን በተደጋጋሚ የሚንሰማው የሽማግሌዎቹ አካሄድ እንድንጠራጠራቸው እያደረገን ነው:: የዝህ ዓይነቶች ሽምግልና አካሄድ ባህልና እሴቱን ከመጣሱ ባሻገር ትልቁ አደጋው የሕዝብ ጥያቄዎች ወይም ችግሮች 'በንጉሳቸው'እንዳይሰማ ይጋርደዋል:: ሁሉም ነገር ያልፋል:: እውነት ግን ለዘላለም ትኖራለች:: እኔ ሽማግሌዎችን ለመምከር አልደፍርም:: ነገር ግን እንደ አንዱ ልጃቸው ለማስታወስ የሚፈልገው እውነቱን (Halaale) ይዞ በጥቅማጥቅም የሽምግልና መሠረቱን ሳያንዱ ችግሮችን በቀናነት እየፈቱ ማህበረሰብን ቢያገለግሉ ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ አሻራና ትምህርት ያስተላልፋሉ ብዬ በፅኑ አምናለሁ:: በመጨረሻም ፈጣሪ አሁንም እውነቱን (Halaale) ይግለጥልን! ምህረቱንና ሠላሙንም ያውርድልን!

ይህ የስዳማ ማህበረሰብ ለነፃነታቸዉ ከትጥቅ ትግል አንስቶ የነበረውንና ባህላዊ አኗኗራቸውን የሚያስተምር በዶክተር በዛብህ ባራሳ ጎሶማ የተፃፈ መፅሐፍ ነው:: ከ Amazon ገዝታችሁ አንብቡ:...
27/09/2025

ይህ የስዳማ ማህበረሰብ ለነፃነታቸዉ ከትጥቅ ትግል አንስቶ የነበረውንና ባህላዊ አኗኗራቸውን የሚያስተምር በዶክተር በዛብህ ባራሳ ጎሶማ የተፃፈ መፅሐፍ ነው:: ከ Amazon ገዝታችሁ አንብቡ:: እውነተኛ ታርክና ብዙ እውቀት ትቀስማላችሁ::

የሀገር ጠ/ር እንኳን ቀምታችሁ ለራሳችሁ ተደራጁ የሚሉበት ሀገር ለምሳሌ: የነዳጅ ቦትና ገንዘብ ወይም ብር ለውጥ የተደረገበት ግዜ እና ማርካችሁ ታጠቁና ተደራጁ የሚሉበት ሀገር ለምሳሌ በትግ...
27/09/2025

የሀገር ጠ/ር እንኳን ቀምታችሁ ለራሳችሁ ተደራጁ የሚሉበት ሀገር ለምሳሌ: የነዳጅ ቦትና ገንዘብ ወይም ብር ለውጥ የተደረገበት ግዜ እና ማርካችሁ ታጠቁና ተደራጁ የሚሉበት ሀገር ለምሳሌ በትግራይ ጦርነት ግዜ የፋኖ አርበኛ ምረ ወዳጆ መንግሥት የሚሸት መግለጫ ስሰጥ ስሰማ የብስለት ልዩነት ስፋት ምን ያህል እንደሆነ አሳየኝ::

...

26/09/2025

የወሎ ፋኖ ብቻውን ክ/ጦሮችን ከደመሰሰና ከማረክ ሁሉም ፋኖዎች አንድ ላይ ሆኖ ቢሆንስ ብላችሁ አስባችሁታል:? እንድሁም ሌሎችም ለምሳሌ: OLA, WBO, TDF…ወዘተ ተጣምሮ ቢሆን ለብልፅግና የዝንብ እድሜም አይኖረውም ማለት ነው::

26/09/2025

በነገራችን ላይ: አንድን ብር ከአንድ ዶላር ጋር እኩል እናረጋለን ወይም እኩል እንደሚሆን ገታ አሳይቶናል ስሉ የነበሩ የት ገቡ:?

ይህ አሁን ምን ይባላል🤔ግለሰቦች ከፈለጉ መጽሐፉን እራሳቸው ገዝተው ያነባሉ እንጅ በመሥሪያ ቤት በኩል ትዕዛዝ ተደርጎ እንዴት:??
24/09/2025

ይህ አሁን ምን ይባላል🤔ግለሰቦች ከፈለጉ መጽሐፉን እራሳቸው ገዝተው ያነባሉ እንጅ በመሥሪያ ቤት በኩል ትዕዛዝ ተደርጎ እንዴት:??

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Buche Yogo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Buche Yogo:

Share