Kichu-Ganamaa

Kichu-Ganamaa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Kichu-Ganamaa, Publisher, Bule Hora, Addis Ababa.

wancii
26/02/2021

wancii

Good Afternoon Oromia
17/02/2021

Good Afternoon Oromia

Good morning OROMIA
14/02/2021

Good morning OROMIA

Good Morning OROMIA!!
13/02/2021

Good Morning OROMIA!!

29/11/2020

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5552 የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5570 ደርሷል።...
27/06/2020

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5552 የላብራቶሪ ምርመራ 145 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5570 ደርሷል።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 8 (1 ከጤና ተቋም እና 7 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 2 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። ከዚህ ባለፈ 3 በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 94 ደርሷል፡፡ በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 327 ሰዎች (317 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ክልል፣ 1 ከትግራይ ክልል እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2015 ነው።

15/06/2020
Covid-19 info Ethiopia
13/06/2020

Covid-19 info Ethiopia

----- የሲ/ር አሰለፈች በኮሮና መያዝ፣ --------- ህልፈተ ህይወትና የቀብር ስነ ስርአት ---******************..........*****************'የሲ/ር አሰለፈች...
07/06/2020

----- የሲ/ር አሰለፈች በኮሮና መያዝ፣ ----
----- ህልፈተ ህይወትና የቀብር ስነ ስርአት ---
******************..........*****************
'የሲ/ር አሰለፈች ቀብር ከሃዘን ይልቅ ፍርሃት ነግሶበት አለፈ። እድርተኞች አልመጡም፤ ቤተዘመድ አልሸኛቸውም፤ ከሚወዷቸው የሥራ ባልደረቦቻቸው ግብዓተ መሬታቸው ሲፈጸም አንድም ሰው ዝር አላለም። ጸሎተ ፍትሐት የሚያደርግ ልዑክ ጠፍቶ መምህረ ንስሃቸውን አንድ ዲያቆን ከርቀት በለሆሳስ ነው ያደረሱት። . . . የሚያጽናና የለም። እዝን ያመጣም አልነበረም። . . . ከሞታቸው በላይ የእናታቸው ቀብር የልጆቻቸውን ልብ ሰብሯል።
'የታመመ ጠያቂ፣ የተጣላ አስታራቂ ነበሩ። ለቅሶ ቢሆን ሰርግ ወይዘሮ አሰለፈች ከሌሉ ጨው እንደሌለው ወጥ ነው። በአንዴ ከደጋሹ በላይ አዛዥ ናዛዥ ሆነው ይገኛሉ። በሰፈሩ በቤት ውስጥ ተወልዶ ሲ/ር አሰለፈች እትብቱን ያልቀበሩለት ማግኘት ይከብዳል። ለዚህም ይመስላል የሰፈሩ ጎረምሳ እሳቸውን እንደ እናት ከመቁጠር በላይ በስማቸው ሊምል የሚዳዳው። ታዲያ የእኚህ ደርባባ፣ አመለሸጋ የመንደሩ ሁሉ እናት ቀብር ለምን የአልፎ ሂያጅ ቀብር መሰለ?
'ሦስት ልጆቻቸውን ያለአባት አስተምረው ለዩኒቨርሲቲ ያደረሱት በአንድ የመንግስት ሆስፒታል በነርስነት እየሰሩ በሚያገኙት ደሞዝ ነበር። በባልደረቦቻቸው እንደተወደዱ፣ በታካሚዎች እንደተመሰገኑ 20 ዓመታት አገልግለዋል። . . .
'ታዲያ በአንድ ሰንካላ ቀን በሥራ ላይ እያሉ ሁለት ጸጉረ ልውጥ ሰዎች ከሜትረኗ ጋር አስጠርተዋቸው 'እዚህ ዋርድ ተኝቶ የነበረው ታካሚ 'ፖዘቲቭ' ስለሆነ መመርመር አለብሽ' አሏቸው።
ደነገጡ።
ምርመራ አድርገው ውጤት እስኪደርስ ለጤና ባለሞያዎች ወደተለየ ቦታ ተወሰዱ። ድፍን ሁለት ቀን ፍርሃት፣ ሃዘን፣ ጭንቀት፣ . . . መጥፎ ስሜቶች ሁሉ በከፍተኛ አቅማቸው በረቱባቸው። እንቅልፍ አይታሰብም፤ የመጀመሪያውን ቀን ስለልጆቻቸው ሲብሰከሰኩ ቁጭ ብለው ለደቂቃ በአይናቸው ሳይዞር ነበር የነጋው። . . . የፈሩቱ አልቀረም ኮሮና እንዳለባቸው ስለታወቀ ወደ ህክምና ማእከል ተወሰዱ።
'ካለባቸው የአስም ሕመም ጋር ተዳብሎ በሽታው ስለጸናባቸው ወደ ጽኑ ሕክምና ክፍል በገቡ በ3ተኛው ቀን የልጆቻቸውን ወግ ማእረግ ሳያዩ እንዲሁ እንደተንከራተቱ አረፉ።'
የሲ/ር አሰለፈች ታሪክ ምን አይነት ስሜት ፈጠረብን?
ሃዘን፣ ፍርሃት፣ ድንጋጤ፣ መሸበር፣ ጭንቀት . . .?
ስሜቶቹስ ምን ያህል ጠንካራ ናቸው? የምናውቃቸው እናት፣ ጎረቤት፣ ባልደረባ ወይስ ማንን አስታወሱን? ከእነዛ ሁሉ ቁጥሮች በተለየ እንድንጠነቀቅ፣ ወላጆቻችንን እንድናስብ፣ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን እንድንወጣ አነሳሱን?
እያንዳንዱ ብዙኃን መገናኛ ቢያንስ በሞት ያጣናቸውን ሰዎች (ማንነታቸው ሳይገለጽና ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ) ታሪክ በመተረክ ሕዝቡ ነፍስና ስጋ መንፈስም ያላቸው ወገኖቹ ምን እየደረሰባቸው እንዳለ እንዲገነዘብ ማድረግ ይቻላል።
እንዲያ ሲሆን ሰዎች ራሳቸውን በሞቱት ወገኖች ጫማ እንዲያስቀምጡ ያስችላቸዋል። ይህ መንገድ ሊፈጥር የሚችለውን የፍርሃት መጠን እያዩ ሚዛኑን መጠበቅ ይቻላል።
👉 ዶ/ር እንግዳ ግርማ
(የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር)

(ከፌስቡክ የተገኘ)

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ተቋም ስራተኛች ቁጥር 97 ደረሰ።በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ተቋም ስራተኛች ቁጥር 97 የደረሰ ሲሆን በአብዛኛዎቹ በሁለት ሳምንት ውስጥ የተያዙ ና...
07/06/2020

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ተቋም ስራተኛች ቁጥር 97 ደረሰ።

በኢትዮጲያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ የጤና ተቋም ስራተኛች ቁጥር 97 የደረሰ ሲሆን በአብዛኛዎቹ በሁለት ሳምንት ውስጥ የተያዙ ናቸው፡፡

በኢትዮጲያ የኮረና ቫይረስ ከገባበት መጋቢት ወር በኃላ ስርጭቱ ባለፉት ሁለት ሳምታት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑንና በቫይረሱ የሚያዙ የጤና ተቋም ሰራተኛች ቁጥርም እያሻቀበ እንደሆነ የጤን ሚንስትሯ ሊያ ታደሰ ከሚመለከታቸው ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ ተናግረዋል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 81 የሚሆኑ የጤና ተቋም ባለሙያዎች በቫይረሱ እንደተያዙ ይፋ ከተደረገው መረጃ ለመረዳት ችለናል፡፡

ቫይረሱ ከተገኘባቸው መካከል 91 የሚሆኑት በአዲስ አበባ የሚገኙ ናቸው፡፡ በቫይረሱ ከተያዙት የጤና ተቋም ሰራኞች መካከል 55 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡

አብዛኞቹ ሰራተኛች ምንም አይነት የበሽታው ምልክት ያልታየባቸው ሲሆኑ ነገር ግን ቫይረሱ እንደተገኘባቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

እስካሁን ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ንክኪ ነበራቸው ተብለው የተለዩ እና እራሳቸውን አግልለው የነበሩ የጤና ባለሙያውች ቁጥር 2340 ደርሷል ከነዚህ መካከል 1721 የሚሆኑት ተጋላጭ የነበሩት መጋቢት ወር ላይ ነው፡፡

የጤና ባለሙያዎቹ በዘውዲቱ ሆስፒታል ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ በሆንም አሁን ቁጥራቸው እየጨመረ ስለመጣ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ እየተዘዋወሩ ነው፡፡

ለህክምና ተቋማት የሚያስፈልጉ ራስን የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረት እንዳለ ሆኖ የአጠቃቀም እና የጥንቃቄ ጉድለቶች መስተዋላቸውንም ከተደረገው ሙያዊ ውይይት ለመገንዘብ ችለናል፡፡

ግንቦት 21 ቀን 2012 ከኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የወጣ ደብዳቤ ምን ያህል የጤና ለሙያዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ እንደሆኑ፤ በቫይረሱ እንደተጠቁ ወደ ለይቶ ማቆያ እንደገቡ አህዛዊ መረጃ ከመንግስት እንዲሰጠው ጠይቆ ነበር ፡፡

ይህ ጥያቄው የተነሳው በበሽታው የሚያዙ የጤና ባለሙያውች ቁጥር እየጨመረ ስለመጣ ክፍተቱ የቱ ጋር በግልፅ እንዳለ ለመረዳት እና የስራ ላይ አደጋን ለመቀነስ የሚቻልበትን መንገድ ለማፈላለግ ያለመ መሆኑን የኢትዮጲያ ሕክምና ማህበር ያብራራል።

ምንጭ ዋዜማ ራዲዮ/ ethio FM

COVID-19 INFO ETHIOPIA  #72
22/05/2020

COVID-19 INFO ETHIOPIA #72

Address

Bule Hora
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kichu-Ganamaa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category