
17/09/2022
ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተነሱ 1,897 ዜጎች በፍላጎታቸው ወደየመጡበት አካባቢ ተሸኙ
የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎችን ከጎዳና ላይ በማንሳት የህይወት ክህሎት ስልጠና በመስጠት 1,615 ወንዶች እና 282ሴቶችን በአጠቃላይ 1,897 ዜጎችን በፍላጎታቸው መሰረት ወደመጡበት በሰሜን፣ ደቡብ፣ ምስራቅና ምዕራብ አቅጣጫዎች በዛሬው ዕለት ሽኝት አድርጓል።
ቢሮው በ2015 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር 3,273 ዜጎችን ከጎዳና ላይ ያነሳ ሲሆን ዛሬ 1,897 በፍላጎታቸው መሰረት ወደ በቤተሰባቸው ተሸኝቷል።
ቀሪዎቹ 1,376 ከጎዳና የተነሱ ሰዎች ወደስራ ለማሰማራትና ተደራራቢ የአካልጉዳት ያለባቸውንና ዕድሜያቸው የገፉ አረጋውያንን ዘላቂ የተቋም አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
Ethio Color Media