Lewi Christian Media

Lewi Christian Media ለከበረ ህይወት ተጠርተናል!

🔥 የተሀድሶ revival part1“ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ  #አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም  #አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና  #እጸልይ ነበር፥”  — ነሀምያ 1፥4🔥ብዙ ክር...
04/07/2023

🔥 የተሀድሶ revival part1

“ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ #አለቀስሁ፥ አያሌ ቀንም #አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና #እጸልይ ነበር፥”
— ነሀምያ 1፥4

🔥ብዙ ክርስቲያን በዚህ ዘመን እጅጉን ግድየለሽ ሆኗል ሂወቱ ፈርሶ ትውልዱ ፈርሶ ቤተክርስቲያን ፈርሳ #ምንም አይመስለውም🤔

🔥በዚህ ዘመን በዙ ክርስቲያን ከተተከለ ብዙ ዓመት እንደሆነው ንፋስና ፀሐይ እንዳደከመው ድንኩኣን #እንደምንም ነው ያለው

🔥ቁአሚውን ምስጥ በልቶት ቀለም እየተቀባ የታደሰ መስሎ እንደሚቆም ቤት ውስጣችን ፈርሶ እያስመሰልን "ጌታ ይባረክ" ከምንል እግዚአብሔር እንደገና አፍርሶ ይስራን

🔥ከ revival ሉም ሆነ ከተሃድሶ በፊት ነህምያ #እንዳዘነ ልናዝን #እንዳለቀሰ ልናለቅስ ልንፀልይ ይገባል በኛ ላይ በትውልዱ ላይ በቤተክርስቲያን ላይ #የሃዘን መንፈስ ሊመጣ ይገባል

“እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ #ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።”
— 2ኛ ቆሮ 7፥10 ተባረኩ

አገልጋይ አማኑኤል እንዳለ
Bella FBI youth ministry

📕እኛ አንብስም?✍️ ሳኦል አልታዘዘም አጥፋ የተባለውን በሬ ይዞ መጣ አቤት ሳኦል አመፁ(1ኛሳሙ 15:15)... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️  ቃሉ የሚለውን ሳይሆን የማይለውን አርጉ...
25/05/2022

📕እኛ አንብስም?

✍️ ሳኦል አልታዘዘም አጥፋ የተባለውን በሬ ይዞ መጣ አቤት ሳኦል አመፁ(1ኛሳሙ 15:15)... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ ቃሉ የሚለውን ሳይሆን የማይለውን አርጉ የተባልን ይመስል የውሸት የማስመሰል እና የክፋት መንጋ እየነዳን ወደ ቤተክርስቲያን ስንመጣና ለወንድማችን እንቅፋት ስናኖር የማንፈራ😔

✍️ አናንያ እና ሰፒራ ግማሹን ብር ደብቀው መንፈስ ቅዱስን ዋሹ (ሐዋ 5:4) ... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ እነሱስ ከራሳቸው ብር ላይ ነዉ እኛ አስራት እና መባውን ስንዘርፍ የእግዚአብሔርን ቤት ገንዘብ እንዳሻን ስናደርግ እና አልፎ የእግዚአብሔርን ለግል ጥቅማችን የምናረግ😔

✍️ ሲሞን ደፋር ነዉ በገንዘብ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ መስጠት ፈለገ( ሐዋ 8:19)... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ ሺዎች እያስከፈልን በደረጃ ስንፀልይ እና የተፀለየበት እያልን ዘይት ከጨርቅ ምንቸበችብ😔

✍️ እነ አፍኒን እና ፊንሃስ እግዚአብሔርን የመዳፈራቸው ብዛት በመቅደስ ውስጥ አመነዘሩ(1ኛ ሳሙ 2: 12) ... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ እነሱስ ቤተመቅደስ ውስጥ ነዉ እኛ እራሳችን ቤተመቅደስ ሆነን ግን አንዷን ፈትተን አንዷን ስናገባ በመጠጥ በሱስ እና በ ክፉ ስጋዊ ምኞት መቅደሱን የምናረክስ😔

✍️ ቃየን ሴጣን ነዉ የገዛ ወንድሙን ገደለ(ዘፍ4:8) ... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ በወንድማችን አገልግሎት የምንቀና ባልተፈጠረ ታሪከ ስም በማጥፋት እና በኃሜት ስንቱን ባለ ራእይ የምናሳድድ እና የምንገድል😔

✍️ አኪጦፌል ብልግናው ዳዊት ከድቶ በሱ ላይ ክፉ መከረ (2ኛ ሳሙ 17:1) ... እንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ በኛ ክፉ ምክር የስንቱ ትዳር ፈረሰ ስንቱ አገልግሎቱን ጣለ በኛ ክፉ ምክር ስንት ቤተክርስቲያን ለሁለት ተከፈለ ስንቱስ ወዳጅ ተለያየ😔 ደሞ ጮክ ብለን 🔥የአኪጦፌል ምክር ይፍረስ እንላለን 😁 ስንት መፍረስ ያለበት እኛ ጋር ተቆልሎ

✍️ አካን ክፋቱ እሱ ድንኩአን ውስጥ በሸሸገው እርም ለእስራኤል ሁሉ መሸነፍ ምክንያት ሆነ (እያ 7:12) ,.. አንላለን እንጂ እኛ አንብስም?🙆‍♂️ ስንት እርም ስንት ውሸት ስንት ጥላቻ ስንት ሙስና ስንት መዳራት ስንት ምንዝርና ስንት ሱስ ስንት ክፋት በጉአዳችን even በስልካችን ውስጥ ደብቀን ለቤትክርስትያን ለቤታችን ለህብረታችን ውድቀት ምክንያት ምንሆን? 😔

🔥 ቅዱሳን በቸርነቱ እንጂ ፊቱ መቆም ሚያስችል ድፍረት ኖሮን አይደለም መፀሐፍ
“አንተ ግብዝ፤ አስቀድመህ በዐይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፤ ከዚያም በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጕድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።”ማቴዎስ 7፥5 (አዲሱ መ.ት) እንደሚል ጣት መጠቆም ትተን እኛ ጋር ያለውን የሚቢሰውን እናሸንፍ🙏

ፀጋ ይብዛላችሁ
አገልጋይ አማኑኤል እንዳለ

በእውቀት📕“ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ምሳ19፡2 ስለክርስትና ሳስበ ከልጅነቴ👨‍⚕ ጀምሮ እየሰማው ያደኩት ነገር አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እጅጉን ይገርመኛል፡፡ በት...
24/12/2021

በእውቀት📕
“ነፍስ እውቀት የሌለባት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም” ምሳ19፡2
ስለክርስትና ሳስበ ከልጅነቴ👨‍⚕ ጀምሮ እየሰማው ያደኩት ነገር አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው እጅጉን ይገርመኛል፡፡ በትምህርት፣ በአገልግሎት፣ በጸሎት ብቻ ምን አለፋችሁ በሁሉ መንፈሳዊ ተግባራት ውስጥ “ክርስትና በሞኝነት ነው” የምትል ከመፈክር ያላነሰች አባባል ቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ቦታ ተሰጥቷት ኖራለች፡፡ ለመሆኑ ይህች አባባል ከየትኛው የመጽሀፍ ቅዱስ ሃሰብ መነሻ ተደርጋ ይሆን፡፡ ኑሮአችንን አገልግሎታችንን አልፎ ህይወታችንን ከዕውቀት ውጪ አርገን ሁልጊዜ ክርስትና በሞኝነት ነው በሚል የወደቀ ብሂል ብዙ ዘመን ያቃጠልነው፡፡ እራሱ ከጊዜውስ ባለፈ ትውልዱን የጸና መሰረት የሌለው የውሃ ላይ ኩበት ያደረግነው፡፡

🔥 እግዚአብሄር እኮ የምድርን ሞኝ ነገር መረጠ መባሉ የዓለምን ጥበበኞች የሚያሳፍርና ድንቅ የሆነውን የሚበልጠውን የእግዚአብሄርን ጥበብ በእኛ ይገልጥ ዘንድ አንጂ በውኑ የእግዚአብሄርን መንግስት የዕውቀት ጠል(ignorant) ሰዎች መሰባሰብያ ሊያደርጋት ነውን ? ካለማስተዋል ህይወት ወደ ማስተዋል ህይወት ተቀይረናል፡፡ በዚህ አጭር ምልዕክት ውስጥ ማስተላለፍ ለፈለኩት ሀሳብም መነሻ የሚሆን ሁላችንም ከምናውቀው ቃል መነሻ ላድርግ፡፡
በትንቢተ ሆሴዕ 4፡6 “አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን አንዳትሆነኝ እጠለሃለው” ይላል፡፡ ካህን ወይንም የትኛውንም መንፈሳዊ አገልግሎት በሞኝነት ሳይሆን በእውቀት ነው፡፡

🔥ለዚህ ነው ሐዋሪያው ጳውሎስ ለቲቶ በጻፈው ደብዳቤ መግቢያ ላይ ሃወሪያ ስለተደረገበት አገልግሎት ሲናገር በእግዚአብሄር የተመተረጡት እምነትና ወደ እውነተኛ መንፈሳዊነት የሚወስደውን የእውነት እውቀት ለማሳደግ ሐዋሪያ የሆነ... የሚለን እኛ ግን ክርስትና በሞኝነት ነው እያልን ይኸው ዛሬ ላይ ሃጢያትን የሚገስጽ ከሰይጣን ግን የሚሸሽ ትውልድ እያፈራን ነው፡፡ ለዚህ ነው ዛሬ ላይ ወደፊት መላዕክ እሆናለው የሚል አገልጋይና በደመነፍስ አብሮ አሜን የሚል እልፍ ትውልድ ያፈራነው፡፡ ለዚህ ነው ለትንሽ ደቂቃ መንበርከክ የማይችል ነገር ግን አሳዶ ነብያት ጋር ተሰልፎ ደጅ የሚውል የሚያድር ትውልድ ያፈራነው፡፡

🔥ህዝቡ የጠፋው እውቀት ከማጣት የተነሳ ነው፡፡ ምክንያም ያደግነው “ክርስትና በሞኝነት” በሚል እውነትን ሳይሆን ፍላጎታችንን ተከትለን እንድንኖር የሆነው፡፡
ሌላው ይቅርና ለመሆኑ የዘለለም ህይወትስ እውቀት እንደሆነ እናውቅ ይሆን? ብዙ ሰው ስለ ዘላለም ህይወት ምንነት ሲያስብ ወደ ገነት ተመልሰን የምንበላው የዛፍ ፍሬ ይመስለዋል፡፡ ብዙ ሰው ደግሞ እዛ ስንሄድ የምውጠው ታብሌት ይመስለዋል፡፡ ሌላውም ሌላ ሌላውም ሌላ÷ ነገር ግን የዘላለም ህይወት “ዕውቀት” ነው፡፡ በዮሐንስ ወንጌል 17፡3 ላይ "...የላከውንም ኢየሱሰ ክርስቶስን ያውቅ ዘንደ ይህች የዘላለም ሕይወት ነው ይለናል” ይህ ሀሳብ ብዙ ጊዜና ማብራራት የሚጠይቅ ቢሆንም ከሀሳቤ እንዳልወጣ በይደር አቆይቸዋለው፡፡ ነገር ግን በጌታችን በ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት በዓለም ካለው እርኩሰት ማምለጣችን ጀምሮ...2 ጰጥሮ 2፡20... ማደጋችን ፍሬ ማፍራታችን መዳናችን ሁሉ ያለው እውቀት ውስጥ እንደሆነ ልብ ልንል ይገባል፡፡ ብዙ ልናገርበት የምንችልበትን ሰፊ ሀሳብ ባነሳም በዚች አጭር መልዕክቴ ማጠቃለያ ላይ ደግሜ የምናገረው ነገር በሞኝነት ሳይሆን በእግዚአብሄር እውቀት አንኑር “...ጻድቃን ግን በእውቀት ይድናሉ።”
— ምሳሌ 11፥9
አገልጋይ አማኑኤል እንዳለ

📝 የ ወይን ጠጅ📕ብዙ ሰው ከታሰረበት የመጠጥ ሱስ ለመውጣት ቃል ሲናፍቅ በተቃራኒው ብዙ ሰው ደግሞ ለመጠጣት ቃል ይጠቅሳል 🙆‍♂️📕ኢየሱስ ውሃውን ጠጅ አረገው ዮሐ2 ጳውሎስ አትስከሩ  አንጂ...
02/12/2021

📝 የ ወይን ጠጅ

📕ብዙ ሰው ከታሰረበት የመጠጥ ሱስ ለመውጣት ቃል ሲናፍቅ በተቃራኒው ብዙ ሰው ደግሞ ለመጠጣት ቃል ይጠቅሳል 🙆‍♂️

📕ኢየሱስ ውሃውን ጠጅ አረገው ዮሐ2 ጳውሎስ አትስከሩ አንጂ አትጠጡ አላለም ኤፌ5:18 እና ሌሎችም... አሁን አሁንማ ቤተክርስቲያንን አንመራለን የሚሉት ሰዎች ቤት እንኩአን ገበታ ላይ እንደ ውሃ መቅረብ ስለ ጀመረ ቀጣዩ ትውልድ ምንም ሳይቸገር በ ጠጅ የሚሰክርበት መንገድ እየተጠረገለት ነው ያም ሆነ ይህ ግን

📕ጥያቄው መንፈስ ቅዱስ የተሞላ ሰው የ ወይን ጠጅ ይሞላል ወይ? ነው

📕ማንም ሰው አደለም የ ኢየሱስ ደም ፈሶለት በዋጋ የተገዛ አይደለም በ አሮጌው ኪዳን ማንም ለ እግዚአብሔር ራሱን ቢለይ...

📕በ ዘኍልቁ 6 (አዲሱ መ.ት)
¹ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
² “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፣ ‘ወንድም ሆነ ሴት ናዝራዊ ይሆን ዘንድ ራሱን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) #ለመለየት ስእለት ቢሳል፣
³ ከወይን ጠጅና ከሌላም ከሚያሰክር መጠጥ ይታቀብ፤ የወይንም ሆነ የሚያሰክር የሌላ መጠጥ ኾምጣጤ አይጠጣ፤ እንዲሁም የወይን ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ።
⁴ በናዝራዊነቱ ወቅት ከወይን ተክል የሚገኘውን ማንኛውም ነገር፣ የወይኑን ዘር፣ ግልፋፊውንም እንኳ ቢሆን አይብላ ይላል ::

በነገራችን ላይ #መለየት ማለት #መቀደስ ማለት መሆኑን ልብ ይሉአል

📕ማንም ሰው አደለም ቤተ መቅደስ ሆኖ መንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አርጎት አደለም በ አሮጌው ኪዳን እንኩአን ሰው ታቦቱ ወዳለበት ወደ መገናኛው ድንኩአን ሲቀርብ መች ጠጅ ይጠጣል?...

📕ዘሌዋውያን 10 (አዲሱ መ.ት)
⁸ እግዚአብሔርም (ያህዌ) አሮንን እንዲህ አለው፤
⁹ “ #እንዳትሞቱ አንተና ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን በምትገቡበት ጊዜ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፤ ይህም በልጅ ልጃችሁ ዘንድ የሚጠበቅ ዘላለማዊ ሥርዐት ነው።
¹⁰ የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን፣ ርኵሱንና ንጹሑን #ለዩ አደል አንዴ የሚለው

📕እኛ እኮ አሁን ቤተ መቅደስ ነን 🙆‍♂️

📕ሰው አንዴት ጠጃም ለመሆን ጥቅስ ይፈልጋል? የምንበላው እና የምንጠጣው እንኩዋን ለእግዚአብሔር ክብር ይሁን አደል እንደ የሚለው 1ቆሮ 10:35?

📕እንደኔ ማንም ጠጅ ሲያምረው የወይንም ሆነ የገብስ... Bible ላይ መታከክ አይጠበቅበትም ለኛ ግን “በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና። የወይን ጠጅም ሆነ ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ በእናቱም ማሕፀን ሳለ በመንፈስ ቅዱስ ይሞላል።” ሉቃስ 1፥15 (አዲሱ መ.ት)ይላል ::

📕በመጨረሻ ዳግ hiward የተባለ ፀሐፊ ያለውን ነገር ልበልና ልቸርስ ' ሀጥያተኛ ሰው 2 ምርቻ አለው እሱም ጽድቅ ወይ ሀጥያት ነው ፃድቅ ግን ብዙ ምርቻ አለው እሴ ደግሞ እግዚአብሔር ከሚከብርባቸው ነገሮች መሃል ያለው ምርጫ ነው'::

ለ ከበረ ሕይወት ተጠርተናል!
አገልጋይ አማኑኤል እንዳለ

https://youtu.be/hV7sJlm5NwM
02/12/2021

https://youtu.be/hV7sJlm5NwM

ቆየት ያለ የወንጌል መዝሙር በዘማሪ አማኑኤል አንዳለ 2008 ዓም

https://youtu.be/HuTdpGLfxsk
02/12/2021

https://youtu.be/HuTdpGLfxsk

ቻናላችንን subscrib በማድረግ አዳዲስ ትምህርቶችን አና live ዝማሬውችን ይከታተሉ.

https://youtu.be/Ae11P7Hzw1c
02/12/2021

https://youtu.be/Ae11P7Hzw1c

ቻናላችንን subscrib በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ በቅርብ ቀን አዳዲስ ትምህርቶችን አና ዝማሬዎችን አንዲሁም ለሕፃናት የሚሆኑ ፕሮግራሞችን ይዘን ወደናንተ ልንመጣ ዝግጅታቸንን ቸርሰናል አሁኑ.....

https://youtu.be/vrGjjoQo6EA
02/12/2021

https://youtu.be/vrGjjoQo6EA

The song is about how great Gods love for us.ቻናላችንን Subscribe በማድረግ የተለያዩ ዝማሬዎችን እና ትምህርቶችን ይከታተሉ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lewi Christian Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share