06/08/2021
ይዞታ /Possession/
ይዞታ ማለት አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጎ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ይዞታ ማለት አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት አሻሚ ወይም ድብቅ ባልሆነ ሁኔታ በቁጥጥር ስር በማድረግ ልታዝበት የምትችል ነው፡፡ መቆጣጠር እና ማዘዝ መቻል ብቻ ሳይሆን በንብረቱም መገልገል እና መጠቀምን ይጨምራል፡፡ ፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1140
ይዞታ በአንድ ሰው በአንድ ንብረት መካከል ስለሚኖር ግንኙነት የሚገልጽ እንጂ የንብረት ባለ ሃብትነት መብት ማለት አይደለም፡፡ ከባለ ሃብትነት መብት የጠበበ ነው፡፡
ይዞታ ለመኖሩ የሚያረጋግጡ መመዘኛዎች
1. አንድ ዕቃ መኖር አለበት ብቻ ሳይሆን በይዞታው ስር የማድረግ ሃሳብ /Animus) መኖር አለበት፡፡ ለመጠቀም እና ለመገልገል በሚል ሃሳብ የተያዘ መሆን አለበት፡፡ ይህም ሲባል ይዞታውን በቁጥጥር ስር ከማድረግ በተጨማሪ ማለት ነው፡፡
2. ተዘዋዋሪ ይዞታ በሚመለከት ደግሞ ዕቃው በሌላ ሰው እጅ የተያዘ ሆኖ ንብረቱን የመቆጣጠር እና የመጠቀም ሃሳብ ግን ከባለ ይዞታው ጋር ሊቀር ይችላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሲታይ ግን ዕቃው ወደ ሄደበት ይከተላል፡፡
ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ሁለት ንድፈ - ሃሳባዊ እነርሱም subjective & Objective ናቸው፡፡
1. ይዞታ የሚገኝበት ሁኔታ፡- በመቆጣጠር፣ ይዞታውን በመጠቀም የመገልገል ሃሳብ ሲኖር በመርሕ ደረጃ ሁለቱም ተሟልተው መገኘት አለበት፡፡
2. ይዞታ ቀሪ የሚሆንበት ሁኔታ፡- ሲጠፋ፣ ለሌላ ሰው ሲተላለፍ፣ ባለ ይዞታው አያስፈልገኝም ብሎ የተወ እንደሆነ፣ በስጦታ ያስተላለፈ እንደሆነ ቀሪ ይሆናል፡፡