
28/09/2022
“አዲሱ የአማራ ትውልድ የራሱን መሪ ፈጥሮ የጠላቶቹን ሰንሰለት በጣጥሶ ወደ ነፃነት የሚሻገርበትን ሁኔታ የማደላደል ዓላማ ሰንቆ የተቋቋመወ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል በተመሰረተ በአንድ ዓመት ግዜ ውስጥ ለአማራ ህዝብ ትልቅ ተስፋ የጣሉ በርካታ ተግባራትን መፈፀም ችሏል።
በበርካታ መሰናክሎችን አልፈን የመሰረትነው አደረጃጀት እና ለትውልዱ ያስተዋወቅነው የተደራጀ እና የሰለጠነ የፋኖ መዋቅር የመውለድ ሂደት በአራቱም ማዕዘናት የፋኖ አደረጃጀቶችን እንዲፈጠሩ እና እንዲያብቡ የህዝባዊ ኃይሉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ኩራት ይሰማኛል።
መንግስት በህግ ማስከበር ስም የጀመረው የማሰር እና የማሳደድ ተግባር በሺዊች የሚቆጠሩትን ከህይወት መስዋዕትነት እስከ አፈና እና መዋከብ የሚያጥቃልል ዋጋ ያስከፈለ ሲሆን በተለይም የመሪያችን የአርበኛ ዘመነ ካሴ መታፈን የስርዓቱን አደገኛነት ያረጋገጠ እና ህዝባችንን ያስቆጣ ድርጊት ነው::
የአርበኛ ዘመነ ካሴን መታፈን ተከትሎ የታየው ህዝባዊ ቁጣ እና እንቅስቃሴ ትዉልዱ የኔ የሚለውን መሪ በማዳመጥ እና መሪውን በመጠበቅ በኩል ቁርጠኛ መሆኑን ያረጋግጣል።
ለመላው ህዝባችን፣ ለደጋፊወቻችን እና ለህዝባዊ ኃይሉ አባላት የአርበኛ ዘመነ ካሴን ከአፈና ነፃ መውጣት ጨምሮ ጉልህ የሆኑ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች እስከሚመለሱ ድረስ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ስራ አስፈፃሚ ትግሉን ለመምራት የሚያስችል ቁመና ላይ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!”
ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ
የአ/ሕ/ኃ/ ምክትል ሰብሳቢ