11/10/2025
እናት ባንክ በፒያሳ አዲስ ቅርንጫፍ አስመረቀ
ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም፣ (ሀገሬ ቴቪ)፤ እናት ባንክ "እማዬ" ብሎ የሰየመውን ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት በይፋ ስራ አስጀምሯል::
ባንኩ በአዲስ አበባ ፒያሳ አቡነ ጴጥሮስ ሀውልት አካባቢ በቀድሞው የማስታወቂያ ሚኒስቴር ህንጻ ላይ ሁሉንም እናቶች ይወክላል ያለውን ቅርንጫፍ በይፋ አስመርቋል::
ቅርንጫፉ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ሰዎች ስለ እናቶቻቸው የሚሰማቸውን የሚፅፉበት መዝገብ የተዘጋጀለት መሆኑ ሲገለጽ፤ እናቶች በቤት ውስጥ የሚገለገሉባቸው ባህላዊ ቁሳቁሶች እና ስለ እናቶች የተፃፉ መጻሕፍት በቅርንጫፉ ይገኛሉ ተብሏል::
ባንኩ በተለይም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ አካታች የፋይናንስ አገልግሎትን በማስፋፋት በርካታ ሴቶችን በብድር አቅርቦት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ እያስቻለ ስለመሆኑም በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል::
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዓለም ባንክ የሥርዓተ-ፆታ ፈጠራ ጋር በመተባበር ባካሄዱት የ2025 የባንኮች የስርዓተ ፆታ አካታችነት ምዘና መስፈርት መሰረት እናት ባንክ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ባንኮች የመጀመሪያ በመሆን ትራንስፎርሜሽናል ባንክ መባሉንም አስታውቋል::
በማሕበራዊ መገናኛዎቻችን መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/hagerietv
ትዊተር: https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: https://www.t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: https://www.hagerie.tv