Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ This is the official Biruh Media
All the latest news ,Tourism, Entertainment Information in Amharic.

You can follow us on:
Twitter-https://bit.ly/3XtwmG1
Telegram-https://bit.ly/4d7EYbd
Tiktok- https://bit.ly/3zoOKrJ
Youtube- https://bit.ly/3MNLbOO This is the official Biruh media page -Biruhmedia is Ethiopian social Media channel and website . Current, Hot News,Documentary,Tourism,Entertainment Information and more
Capital city:- Addis Ababa. Working Time :-24 hours

Join us on:

Web

site: https://bit.ly/4eyUgHx

Youtube: https://bit.ly/3MNLbOO

Telegram: https://bit.ly/4d7EYbd

Twitter: https://bit.ly/3XtwmG1

TikTok: https://bit.ly/3zoOKrJ

kicks : https://bit.ly/3U45Mm3

Email : [email protected]

20/10/2025

DIDDY COURT LIVE

� New to streaming or looking to level up? Check out StreamYard and get $10 discount! �

...15ኛው ሚዲያ ካፕበቅርብ ቀን..ዮ ስፖርት..Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ Biruh Sport - ብሩህ ስፖርት
07/10/2025

...15ኛው ሚዲያ ካፕ
በቅርብ ቀን..ዮ ስፖርት..
Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ Biruh Sport - ብሩህ ስፖርት

በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት የተቋቋመው "ለመጽደቅ የዘለቄታ" የተሰኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን  ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ አ...
05/10/2025

በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አማካኝነት የተቋቋመው "ለመጽደቅ የዘለቄታ" የተሰኘ ሀገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በደብረ ብርሃን ከተማ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ አስቀምጧል።

ፕሮጀክቱ የአዳሪ ትምህርት ቤት፣ ፊዚኦ ቴራፒ ትምህርት ቤት፣ የተለያዩ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች፣ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክቶች፣ የኮሜዲያን ተሰጥኦ ማበልጸጊያ ትምህርት ቤት፣ ለሴቶች እና እናቶች የቢዝነስ ሥራ ማሠልጠኛ የሥራ ማዕከል ፕሮጀክቶችን በአካባቢዉ ላይ ያከናውናል ተብሏል።

በስድስት ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው ፕሮጀክቱ በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር በእምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ሎሬት አፈ ወርቅ ተክሌ ቀበሌ ሥር በሚገኘው ጋንጎና ቦራሌ ንዑሥ ቀበሌዎች ላይ እንደሚገነባ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ ማኅበረሰቡ ለሚያነሳቸው የረጅም ጊዜ ጥያቄዎችን የሚመልስ ነው ያሉት የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ናቸው። ለብዙ ችግሮች መፍትሔ የሚኾን እንደኾነም ገልጸዋል።

ፕሮጀክቱ በሕዝብ ተሳትፎ የሚገነባ በመኾኑ ለሀገራችን ምሳሌ የሚኾን ነው ብለዋል። ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከተማ አሥተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ነው ያሉት።

በጤና ዕክል የመንቀሳቀስ ችግር ያለባቸው ልጆችን የሚንከባከቡ እናቶች፣ የፊዚዮ ቴራፒ ሥልጠና የሚያገኙበት እና የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ማዕከል እንደሚኖረው የፕሮጀክቱ ሥራ አሥኪያጅ ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ተናግረዋል።

ፕሮጀክቱ ዕውን እንዲኾን የአካባቢው ማኅበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። ፕሮጀክቱም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ እንደሚጠናቀቅም አንስተዋል።

ዘጋቢ:- ብርቱካን ማሞ

አሚኮ ዲጂታል

780 ማይል በብስክሌት የተጓዘዉ ወጣት ብሩክ ተሰራብሩክ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል እና ጥቅም ላይ ከዋሉ እቃዎችና እንጨት በሰራዉ ብስክሌት 780 ማይል ተጉዟል ብሩክ የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን...
02/10/2025

780 ማይል በብስክሌት የተጓዘዉ ወጣት ብሩክ ተሰራ

ብሩክ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል እና ጥቅም ላይ ከዋሉ እቃዎችና እንጨት በሰራዉ ብስክሌት 780 ማይል ተጉዟል

ብሩክ የ24 ዓመት ወጣት ሲሆን በተማረበት ኤምፒሪያል ኮሌጅ በተካሄደው ወርክሾፕ ላይ የሁለተኛ ደረጃ መኪና ጥገና ካደረገ በሗላ የራሱን ብስክሌት ጥቅም ላይ ከዋሉ እቃዎችና እንጨት የራሱን ብስክሌት ለመስራት መነሳሳቱን ገልጿል ።

በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የትራንስፖርት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ ነውክልሎችንና የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ መሆ...
22/09/2025

በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የትራንስፖርት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

ክልሎችንና የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ ወጥ የሆነ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ለአሐዱ አስታውቋል።

በቲክቶክ የዜና አቅራቢ በመሆን የሚታወቀው ብሩክ ኒውስ የጋብቻ ጥምረቱን ፈጽሟል።በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ብሩክ ኒውስ በትዳር ዓለም መቀላቀሉ ብዙዎችን አስደስቷል።እኛም ለብሩክ ኒ...
21/09/2025

በቲክቶክ የዜና አቅራቢ በመሆን የሚታወቀው ብሩክ ኒውስ የጋብቻ ጥምረቱን ፈጽሟል።

በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉት ብሩክ ኒውስ በትዳር ዓለም መቀላቀሉ ብዙዎችን አስደስቷል።

እኛም ለብሩክ ኒውስ እንኳን ደስ አለህ እንላለን፤ የትዳር ህይወትህ በደስታና በፍቅር የተሞላ እንዲሆን እንመኛለን!
#ሼር

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማን ብራንድ አምባሳደር ሆኑ።  በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን በማስመጣት ተመራጭ የሆነው ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋ...
19/09/2025

ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማን ብራንድ አምባሳደር ሆኑ።

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን በማስመጣት ተመራጭ የሆነው ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደን እና ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማን ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መርጧቸዋል ።

* የታማኝነት መገለጫ የሆነው የጋዜጠኝነት ሙያ ባለሙያዎችን የመረጥነው ድርጅቱ ታማኝ አገልጋይ በመሆኑ ነው ተብሏል።

ኢትዮፒካር ዘመናዊነትን የተላበሱና ለኢትዮጵያ መልካ ምድር ተስማሚ የሆኑ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማስመጣትና ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በተጠቃሚዎች ዘንድ ተቀባይነትን እና ታማኝነትን ማግኘት የቻለ ድርጅት ነው።

"ታማኝነት"ን ተቀዳሚ መርሁ ያደረገው ድርጅቱ፤ በቀጥታ ግዢ ከሚያቀርባቸው መኪኖች በተጨማሪ ከተለያዩ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር በመተባበር በውስን ቁጠባ እና መጠነኛ ወለድ ብድር አማራጭን በመጠቀም እስካሁን ለበርካታ መኪና ፈላጊዎች በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን አስረክቧል።

አሁን ላይ የተለያዩ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ሃገር ውስጥ በሚያስመጣቸው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖቹ ከፍተኛ ተፈላጊነትን ያገኘው ኢትዮፒካር ተወዳጆቹን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢዎች በዛሬው ዕለት ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰይሟል።

በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ብሎም በሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢነት ለረጅም አመታት በሙያው የቆዩት ጋዜጠኛ

* እፀገነት ይልማ እና
* ጋዜጠኛ ዮናስ ከበደ

የድርጅቱ አምባሳደር ተደርገው ሲሰየሙ የጋዜጠኝነት ሙያ የታማኝነትና የሃቀኝነት ሙያ መሆኑን መነሻ በማድረግ ኢትዮፒካርም ታማኝ አገልጋይ መሆኑን ለማሳየት ነው ተብሏል።

ሁለቱ ተወዳጅ ጋዜጠኞች ብራንድ አምባሳደር ሆኖ መመረጥ ድርጅቱ ለጋዜጠኝነት ሙያ እና ባለሙያ ያለውን ክብር ማሳያም ስለመሆኑ ተጠቅሷል።

ብራንድ አምባሳደር ሆነው የተመረጡት ዮናስ ከበደ እና እፀገነት ይልማ በአምባሳደርነት በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው በተለይም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ፈላጊዎች ኢትዮፒካር የሚያስመጣቸውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ ምርጫቸው እንዲያደርጉ የማስቻል ስራን እንሰራለን ብለዋል።

በአዲስ አበባ እና በዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ( U.A.E) መቀመጫውን አድርጎ የተመሰረተው ኩባንያው ከኤሌክትሪክ መኪና አምራች ድርጅቶች ጋር ስምምነት በመግባት ለመኪኖቹ የባትሪ ዋስትና በመስጠት እንዲሁም የተሟላ መለዋወጫ አቅርቦትና አስተማማኝ ጥገና ጋር በማቅረብ ደንበኞቹ ከስጋት ነጻ ሆነው እንዲቀሳቀሱ አስችሏል::
#ሼር

Tourism News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ የዎላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል (ጊፋታ) በዓለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ የዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን...
19/09/2025

Tourism News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ
የዎላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል (ጊፋታ) በዓለም አቀፍ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማድረግ የዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት የሣይንስ፣ ትምህርት እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የማይዳሰሱ የባህል ቅርሶች ጥበቃ ዓለም ዓቀፍ መንግሥታት ኮሚቴ 20ኛ ጉባዔ በፈረንጆቹ ከታኅሣሥ 8 እስከ 13 በሕንድ ኒውደልሂ ይካሄዳል።

በጉባዔው ጊፋታ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን በባለስልጣኑ የቅርስ ምርምር መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዮናስ ይልማ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

Music News |  Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ    ድምፃዊት ዲና አንተነህ አዲስ አልበምድምፃዊቷ ይፋ እንዳደረገችው አዲሱ ''ዋጋዬ" የተሰኘው አልበሟ መስከረም 27 /2018 ዓም ...
19/09/2025

Music News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

ድምፃዊት ዲና አንተነህ አዲስ አልበም

ድምፃዊቷ ይፋ እንዳደረገችው አዲሱ ''ዋጋዬ" የተሰኘው አልበሟ መስከረም 27 /2018 ዓም እንደሚለቀቅ አስታውቃለች ።

Photographer News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ  በዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ለተደራጁ ፎቶ አንሺዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡የዓድዋ ድል መታሰቢያን ብሎም የከተማይቱን የቱሪስት መ...
19/09/2025

Photographer News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

በዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ለተደራጁ ፎቶ አንሺዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያን ብሎም የከተማይቱን የቱሪስት መስህቦችን ከፍ ባለ የፎቶግራፍ ክህሎት ለማስተዋወቅ፤ አቅማቸውን ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም፣ እነዚህ ፎቶ አንሺዎች አንድ ዘመናዊ የፎቶግራፍ አንሺ ሊጠቀምባቸው የሚገቡ ቴክኒኮችን እና ዲጂታል አርትዖት እንዲያውቁና እንዲገነዘቡ፣ የፈጠራ ችሎታቸውን ለማሳደግ እና ሙያን ለማበረታታት ስልጠና ተሰቷቸዋል፡፡

ይህን በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተዘጋጀዉን ስልጠና ለወጣቶቹ የሰጠዉ ባገራችን የፎቶግራፍ ታሪክ ዉስጥ ከፊተኛ ከበሬታን ያተረፈዉና የብዙ ዓመታት ልምድ ያካበተዉ ብሎም በኢትዮጵያ የፎቶግራፊ ሙያ ዉስጥ ጉልህ አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለዉ አንቶኒዮ ፊዮሬንቴ ሲሆን አንቶኒዮ በስልጠናዉ ወቅት ለብዙ ዓመታት ካካበተዉ ልምዱ ለወጣቶቹ በማካፈል ባለሙያዎቹ የበለጠ እንዲነቃቁ አድረገዉአቸዋል፡፡

Adwa Victory Memorial-የአድዋ ድል መታሰቢያ

Tourism News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ የሞተር ጀልባዎች ከቀረጥና ከታክስ ነፃ እንዲገቡ መፈቀዱ ተገለፀበሞተር ኃይል የሚንቀሳቀሱ ጀልባዎች ከቀረጥ እና ከታክስ ነፃ ሆነው ...
19/09/2025

Tourism News | Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ

የሞተር ጀልባዎች ከቀረጥና ከታክስ ነፃ እንዲገቡ መፈቀዱ ተገለፀ

በሞተር ኃይል የሚንቀሳቀሱ ጀልባዎች ከቀረጥ እና ከታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ቱሪዝምን በመሳብ ረገድ ሊያገለግሉ የሚችሉ ከ20 በላይ ታላላቅ ሐይቆች መኖራቸውን ያሳወቀዉ ሚኒስትሩ

አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ማናቸውም በንግድ ሥራ ላይ የተሠማራ ሰው የሚከተሉት ጀልባዎች ወደ ሀገር ማስገባት እንደሚችል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

1. ፈጣን እና ቅይጥ አገልግሎት የሚሰጡ ለዓሣ ማጥመጃ እና ለአጫጭር ርቀት የመንገደኛ ማጓጓዣ ወዘተ. የሚውሉ አነስተኛ እና መካከለኛ የሞተር ጀልባዎች(outboard motor boats)
2. በመካከለኛ ሐይቆች ላይ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ፤ ለቱሪስት እና ለአደጋ ጊዜ የሚያገለግሉ ፈጣን ጀልባዎች(speedboats)
3. ለቱሪስቶች ጉብኝት አገልግሎት የሚውሉ ግልጽ ወይም በከፊል የተሸፈኑ ጀልባዎች(Tourist excursion boats)
4. ለሰዎች ማጓጓዣ የሚውሉ ጀልባዎች (Ferries)
5. ለጥናት እና ምርምር የሚያገለግሎ ጀልባዎች(Research boats)
6. ለግል አገልግሎት የሚውሉ ጀልባዎች (Private motor boats)
7. በጸሐይ ኃይል እና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ጀልባዎች( Eco boats)
8. ጠፍጣፋ እና ባለ ጣሪያ የሞተር ጀልባዎች (pontoon boats)

እና የመሳሰሉት ለሀገራችን ሐይቆች ተስማሚ የሆኑ የሞተር ጀልባዎች ቀረጥ እና ታክስ ሳይከፈልባቸው ወደ ሀገር ሊገቡ ይችላሉ ሲል የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።

Ethiopian Broadcasting Corporation

Address

Biruh Media
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 00:00 - 23:45
Tuesday 00:00 - 23:45
Wednesday 00:00 - 23:45
Thursday 00:00 - 23:45
Friday 00:00 - 23:45
Saturday 00:00 - 23:45
Sunday 00:00 - 23:45

Telephone

+251921332168

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Biruh Media - ብሩህ ሚዲያ:

Share

ETHIO VOICE -ኢትዮ ቮይስ

YOUTUBE - ETHIO VOICE