25/10/2020
የፌደራሉን መንግስት 'ሕገወጥ' ብሎ የፈረጀው የትግራይ ክልላዊ መንግስት የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት በፌደራሉ መንግስት እንዳይታዘዝ ጥሪ አቅርቧል። የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ እንዳነሳው በተለይም ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ ወታደር የማዝመት ውሳኔዎች፣ የአደረጃጀትና አመራር ለውጥ ማድረግ፣ ሰራዊት ይሁን ጦር መሳርያ ማንቀሳቀስ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለውና በትግራይ ሊፈፀም የማይችል ብሎታል።