ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press

ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press የጉራጌን ባህል የማስተዋወቂያ እና በተለያዩ ጠቃሚ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ የመለዋወጫ እና የመማማሪያ መድረክ ነው

ግዙፍ ሆስፒታል ለመገንባት ምዕመናን ድጋፍ እንዲያደርጉ የመካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም ጥሪ አቀረበ
17/11/2025

ግዙፍ ሆስፒታል ለመገንባት ምዕመናን ድጋፍ እንዲያደርጉ የመካነ ሕይወት ጮቢ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም ጥሪ አቀረበ

እስካሁን በትክክል ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ መከሰቱን በማስመልከት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
12/11/2025

እስካሁን በትክክል ምንነቱ ያልታወቀ በሽታ መከሰቱን
በማስመልከት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

ወልቂጤ በራሷ ቀለም እየተዋበች ነው😍
12/11/2025

ወልቂጤ በራሷ ቀለም እየተዋበች ነው😍

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ከናሚቢያ ያገኙት ኢትዮጵያዊ ዜጋ***የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ፕሮፌሰር ኃ/ልዑል ዘለቀ ወ/ማርያም ሲሆኑ ትውልዳቸው በጉራጌ ዞን፤ በእነሞር...
11/11/2025

የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ከናሚቢያ ያገኙት ኢትዮጵያዊ ዜጋ
***
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ፕሮፌሰር ኃ/ልዑል ዘለቀ ወ/ማርያም ሲሆኑ ትውልዳቸው በጉራጌ ዞን፤ በእነሞር ፣ መገር እና ኤነር ወረዳ ልዩ ሥሙ ጎረድ (ሚቄ ከተማ) በሚባል ቦታ ነው፡፡
በናሚቢያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለ11 ተከታታይ እመታት በኮምንኬሸንና ስነልሳን የትምህርት ክፍል ውስጥ በመምህርነት፣ ተመራማሪነት እና በፕሮግራም ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ኃ/ልዑል ከ42 በላይ የምርምር ውጤቶች በታዋቂ ጆርናሎች በማሳተም፣ የምርምር ፕሮጀክቶች hWorld Bank, UNDP, EU & NCRST ፈንድ በማምጣትና በመምራት፣ በምርምር ዘርፍ በመሪ በመሆን የሙሉ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲያገኙ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ውስጥም እያሉ በአርባምንጭ ዩንሸርሲቲ ለ3 አመታት አስተምረዋል፣ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም በመምሀርነት፤ በተመራማሪነት በኋላም በዲንነት ለ24 አመታት አገልግለዋል፡፡
ለቀድሞ አዳማ ዩኒቨርሲቲ መመስረት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከቀድሞ ኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ከክቡር ግርማ ወ/ጎርጊስ ሜዳሊያና የምሥክር ወረቀት እንዲሁም የቀድሞ የት/ት ሚኒስቴር ከነበሩት ከክቡር ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል የት/ት ሚኒስቴር አርማ የያዘ የወርቅ ሽልማት ተሰጥቶአቸዋል፡፡
የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲም ከምስረታው ጀምረው እስከ ድህረ ምረቃና የምርምር ም/ል ፕሬዝዳንት ሆነው ለ14 ዓመታት ያህል በማገልገል ተቋሙ ላይ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ የአፕላይድ ስነልሳንና የሶስዮሎጂ ዘርፍ ተማራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰርኃ/ልዑል ዘለቀ ወ/ማርያም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የ2ኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ ከባንጋሎር ዩኒቨርሲቲ እና የ3ኛ ዲግራቸውም ከፖንጃብ ዩኒቨርሲቲ በማዕረግ ተመረቀዋል፡፡ በምርምር ዘዴዎች ደግሞ ጀርመን ከሚገኘው ቢሌፊልድ ዩኒቨርሲቲ እና ከፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡
የእሳቸው ስኬት የኛም ስኬት ነው ይላሉ ይህን ጽሁፍ የላኩልን አብረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሩት የልብ ጓደኛቸው፡፡ እኛም መልካም የምርምር ዘመንን ከወዲሁ እየተመኘን ተወልደው ባደጉበት አካባቢ ምን አስተዋፅኦ እንዳደረጉ እንዲነገረን እንጠይቃለን፡፡
Via: Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

ሰሞነኛው የይውረድልን ፖለቲካ !!👇👇👇ለሰሞነኛው የይውረድልን ፖለቲካ  ውስን ይትባህሎችን ከእንግሊዘኛው ወስደን እንጀምርማ፡፡  ፍራንክሊን ዲ ሩዝቬልት የተሰኙ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚደንት “...
10/11/2025

ሰሞነኛው የይውረድልን ፖለቲካ !!
👇👇👇
ለሰሞነኛው የይውረድልን ፖለቲካ ውስን ይትባህሎችን ከእንግሊዘኛው ወስደን እንጀምርማ፡፡ ፍራንክሊን ዲ ሩዝቬልት የተሰኙ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዚደንት “In politics, nothing happens by accident. If it happens, you can bet it was planned that way.” በግርድፉ ሲተረጎምም" በፖለቲካ ውስጥ በአጋጣሚ ምንም ነገር አይከሰትም፣ ከተከሰተ በዚያው መልኩ እንዲሆን የታቀደ እንደሆነ መወራረድ ይቻላል." ብለዋል፡፡
ስናክልበትም አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ፀሃፍት “Every revolution is born out of conspiracy, nurtured in secrecy, and revealed in the open.” ውርስ ትርጉሙ ሲገለጥም “እያንዳንዱ አብዮት በሴራ የተወለደ፣ በድብቅ የዳበረ፣ እና በአደባባይ የሚገለጥ ነው።” ይለናል፡፡
ሰሞነኛው የይውረድልን ፖለቲካ እያንደረደረ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ይወስደናል፡፡ ሰሞኑን በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ፣ በቴሌግራም እና በመሳሰሉት የማህበራዊ ሚዲያ አውዶች በጣት በሚቆጠሩ ፀሀፍቶች፣ የዩ-ቲዩብ የፖለቲካ ተንታኞች (ፑፍ….. ትን አስብላችሁኝ ነበር)፤ የሚለቀቀው እና የሚደመጠው አንድ ግለሰብ ላይ ያተኮረ የ‹ይውረዱልን› ፖለቲካ ቅጥቀጣ ክልሉ ህገ መንግስት አልባ የሆነ፣ የምክር ቤት አባላት የሌሉበት፣ ከክልል እስከ ወረዳ ብሎም እስከ ቀበሌ መዋቅርና አመራር የሌለበት፣ የክልል ካቢኔ አባላት የሌሉበት በንጉሳዊ ወይም በወታደራዊ መንግስት የአገዛዝ ስርዓት የሚመራ ያስመስለዋል፡፡
ይህ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት ክቡር እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) ላይ የተከፈተው ዘመቻ ወይም የወሬ እሩምታ በተግባር ሲገለጥ ምን ቁምነገሮችን ይዞ ይሆን የሚለውን የአመክንዮ ፍተሻ ስናካሄድ ‹ሰረቀ› የሚል ቃልን አናገኝም፤ ‹ገደለ› የሚል ማሳያም የለም፤ ለአካባቢው አድልቶ ምን እንዳደረገም ማሳያ የለም፤ የመሪነት ብቃት መጓደል ስለመኖሩ የተመላከተ ቁም ነገር የለም፡፡ “ታዲያ ምን አለ አትሉኝም?” ምንም ፡፡ ግን ለእሳት መለኮሻነት ቀብድ እንዲሆን ከክልሉ ምስረታ በፊት ላለፉት 30 ዓመታት እና ዘግየት ብለውም ተጋግረው የቆዩ፣ ከክልሉ አዲስ መመስረት ጋር ምላሽ ተሰጥቷቸው የነበሩ ጉዳዮችን አጭቆ የያዘ ነው፡፡ የሚነሱት ምክኒያቶች ፍሬ ነገር ሲፈተሽም፡-
ተከባብረውና ተዋደው የነበሩትና ያሉት የሃዲያና የጉራጌ ህዝቦች በዘመነ ኢህአዴግ ተስማምተው ለዚያውም በወቅቱ የሃዲያ ዞን አስተዳዳሪ ተፈርሞ ወጥቶ ሁለቱም ዞኖች የተግባቡበት የቆሴና አካባቢው ጉዳይ፣
ተዋደው፣ተዋልደው፣ በጦር ሜዳ ላይ በጋራ ተዋድቀውና የጋራ ታሪክ ሰርተው ለምዕተ ዓመታት ሲነገር የሚኖር ታሪክ የሰሩትን የጉራጌና ቀቤና ህዝቦች በመካከላቸው የገፊና ተገፊ ትርክት ለማንበር የመፈለግ ጉዳይ፣
ሸዋ ( ማዕከላዊ ኢትዮጵያ) ድሮም የሃድያ ግዛት ነው የሚል የአላዋቂ ሳሚ ዲስኩር፣
ጉራጌ ሊመራን አይገባም፤ ክልሉን ምሁራን ይምሩት፤ የሚል የሚመራው ሰው ምን ጉድለት እንዳለው የማያሳይ ምኩን ሃሳብ፣
‹ታላቁ የ….ህዝብ› የሚል ሌላውን ብሔር በነገድና በውግንና የተነጠለ ለማድረግ የሚሰራ ደባ፣
ኦሮሞ ተነስ፣ሲዳማ ተነስ፣ ጌዴኦ ተነስ….እንትና ተነስ የሚሉ የጋርዮሽ ስርዓት አመለካከቶች የነገሱበት እና ማጠንጠኛቸው ‹የክልሉ ፕሬዚደንት ይውረድ› ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ሃሳቦች ከንቱ እና የ‹እኛ› የሚሉትን አንግሶ የ‹እነርሱ› የሚሉትን ለማኮሰስ ቢሆንም ቅሉ እኛ ደግሞ እንዲህ እንላለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ያለን ህዝቦች ዕጣ ፈንታችን ተዋደን፣ ተከባብረንና ተቃቅፈን መኖር ነው፤ እንደ ቆሴ እና ቀቤና አካባቢ ባሉ ስፍራዎች ለቅሬታ ምንጮች የሆኑ ጉዳዮች ካሉ በመነጋገር፣ በመወያየትና ምሁራንን የመፍትሄ አካል በማድረግ በህግና በህግ አግባብ ብቻ መፍታት ነው፡፡
የጉራጌና የቀቤና ህዝቦች ዘመን የወለደውን ቆሻሻ ሃሳብ የሚመስሉ አይደሉም፤ በጋብቻ የተሳሰሩ፣ የተዋለዱ፣ በጦርሜዳ በእነ አበጋዝ ደርሰሞ እና በኢማም ሀሰን ኢንጃሞ ጀግንነት ለትውልድ ሲያበራ የሚኖር ታሪክ ያበረከቱ ጀግኖች ምድር ነው፡፡ ለቀቤና ከጉራጌ የሚቀርበው፣ ለጉራጌም ከቀቤና የሚቀርበው የለም፡፡
የሃዲያም ሆነ የቀቤና ህዝቦች እንደ ማንኛቸውም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ህዝቦች የራሳቸው የሆነ የሚያኮራ ታሪክ ያላቸው ቢሆንም የጉራጌ ምድር ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያን መንግሥት ያቆሙ፣ ዝነኛ የሆኑ፣ የኢትዮጵያ የጦር መሪዎችን ያፈራ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ አውራጃ ነበር። የታሪክ መዛግብት እንደሚያነሱት እስከ ሞቃድሾ ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ግዛት ባስተዳድሩት ዐፄ ዐምደ ጽዮን [እ.ኤ.አ. ከ1314 ዓ.ም. - 1344 ዓ.ም. ድረስ የነገሡ ዜና መዋዕል ውስጥ ጉራጌ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ጋር ቅርብ ቁርኝት የነበረው ሕዝብ እንደነበር ተጽፎ እናገኛለን። በዘመኑ የጉራጌ አውራጃ የውስጥ አስተዳደር ይመራ የነበረው በጉራጌ ተወላጅ አበጋዞች ነበር።
ጉራጌ የኢትዮጵያን "ሰለሞናዊ መንግሥት" በሸዋ ምድር ካቆሙ የኢትዮጵያ ዋና ዋና ክፍሎች መካከል ቀዳሚው ስለመሆኑ ሌላው ማስረጃ በዐፄ ናዖድ ዘመነ መንግሥት የተጻፈው ድርሳነ ዑራዔል ነው። በዘመኑ ድርሳነ ዑርዔል እንደተጻፈው እግዚአብሔር መስፍንነት ከጉራጌ፥ ከመንዝና ከወረብ እንዳይወጣ ለአጼ ናዖድ [የንግሥና ዘመናቸው እ.ኤ.አ. ከ1494-1508 ዓ.ም. ድረስ ነው] ቃልኪዳን ገባለት ይለናል። ይህ በድርሳነ ዑራዔሉ ከገጽ 311-315 ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን ሙሉው ቃል እንዲህ ይነበባል፤
“ወእምድኅረ ፡ ዝንቱ፡ወሀቦ ፡ ለናዖድ ፡ እግዚእነ ፡ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ኪዳነ ምሕረት ፡ ከመ ፡ ኢይጥፋእ ምስፍና ፡ ወምልክና ፡ በምድረሸዋ ፡ ወመንዝህ ወበሀገረ ፡ ጐራጌ ፡ ዘይብልዎ ምድረ ፡ ወረብ ፡ ወምሁር።”
ትርጉም፡
“ከዚሀ ፡ በኋላ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ከምድረ ፡ ሸዋ ፡ምሁርና ፡ምድረ ፡ ወረብ ፡ ከሚባለው ከጐራጌ ፡ አገር ፡ ከመንዝም ፡አገዛዝና ፡ መስፍንነት ፡ አንዳይጠፋ ፡ ለናዖድ ፡ ቃል ፡ኪዳን ፡ ሰጠው።"
በድርሳኔ ዑራዔሉ እንደተገለጠው የጉራጌ ሕዝብ በዘመኑ የኢትዮጵያ መስፍን ሆነው እንዲሾምላቸው ከተወሰነላቸው ሶስት የኢትዮጵያ አካባቢዎች መካከል አንዱ ነበር። በዚህ መልክ እስከ መካከለኛው ዘመን የማዕከላዊው የኢትዮጵያ መንግሥት ዋልታ የነበረው ጉራጌ ከግራኝ ወረራ በኋላም ለኢትዮጵያ ቤተመንግሥት በጣም ቅርብ ነበር። ከግራኝ ወረራ በኋላ ዋናኞቹ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ራሶች ጉራጌዎች ነበሩ።
ጉራጌ አይመራንም የሚለው ሃሳብ ጠላትነትን ከማንገስ እና የፍቅርን ጽዋ ከማፍሰስ የዘለለ ሌላ ፋይዳ የላቸውም፤ በ ፖለቲካ ሴራ ወይም ኢ-ተገቢ በሆነ መንገድ የሚመጣን ውጤት ለማስተናገድ የሚንበረከክ የለም፡፡ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ህገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ በፓርቲ አሰራርም ሆነ በመንግስት አሰራር ውስጥ ከሚፈልቅ ሃሳብ ውጪ የኃይልና የሴራ የይውረድልን ፖለቲካ ለክልሉ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም፡፡
ኦሮሞ ተነስ፣ሲዳማ ተነስ፣ ጌዴኦ ተነስ….እንትና ተነስ የሚሉ የጋርዮሽ ስርዓት አመለካከቶች የነገሱበት ሃሳብ ለሴራ ፖለቲካው ስክሪን ሴቨር ሆኖ እንዲያገለግል ቢሆንም ቅሉ የህዝባችን ንቃተ ህሊና የደረሰበትን ደረጃ ከመካድ የሚነሳ፤ ጥርጣሬ እንዲነግስ የሚያደርግና የናዚዝም እሳቤ ነው፡፡
ስለሆነም ስናጠቃልለው ከክልል እስከ ታችኛው መዋቅር ላላችሁ መሪዎቻችን ምክረ ሃሳብ አለን፡፡
በአሰራሮቻችን ላይ ከላይኛው እርከን እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ግልጽነት መፍጠር – ሂደቱን በእጅ አዙር እየመሩ ያሉትን የመዋቅሩ ውስጥ እፉኝቶች መመንጠር ጊዜ ሊቸረው የማይገባ ጉዳይ ነው፡፡
በሁሉም አመራሮች ዘንድ እርስ በርስ አመኔታንና ክብርን መገንባት ያስፈልጋል፡፡ በቡድን ውስጥ የተመሰረተ እምነት እና ክብር የመገንባት ጉዳይ የመፍትሄ እርምጃው ግማሽ መንገድ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በተፈጠሩ ጉዳዮች ላይና እየተፈጠሩ ባሉ ክስተቶች ላይ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ማድረግና የፈጣን ግብረ-መልስ ስርዓት መከተል ችግሮችን በእንጭጩ ለመቅጨት ጉልበት ይሆናል፡፡ በአሰራር ጥሰት ላይ ተሳትፎ አደርገው እንደተገኙ የተረጋገጠባቸውን የፖለቲካ መሪ ይሁን እሰከ ታችኛው ያለ ባለሙያ ወይም ግለሰብ ላይ የህግ ተጠያቂነት ማንበር ሰዎች ሥራቸውን በህግና ህግ አግባብ ብቻ እንዲከውኑ ያደርጋል፡፡
የሰሞነኛው ‹የይውረድልን› የሴራ ፖለቲካ ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ይሉትን የአበው ብሂል እንዳያነግስ በልኩ ለማኮሰስ በአጭር ጊዜ ለሌሎች ክልሎችም ጭምር በአርአያነት የሚጠቀሱ የማህበራዊ፣ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ዕድገቶችን አንድ…. ሁለት ተብሎ የማስጨበጥ ስራ ሊያኮራ እንጂ ሊያሳፍር የሚችል አይደለም፡፡ እንኳንስ የክልሉ አመራርና ነዋሪ በፌደራልና በተለያዩ ክልል አመራሮች የተሞክሮ ማዕከል እንደሆነ እየተነሳ ያለን ክልል አመራሩ፣ነዋሪውና አላፊ አግዳሚው ብዙ ሊልለት የሚችል ነው፡፡ ዝም አትበሉ፡፡
አበቃሁ!!

መሶብ- የአንድ ማዕከል አገልግሎትበማ.ኢ ክልል
05/11/2025

መሶብ- የአንድ ማዕከል አገልግሎት
በማ.ኢ ክልል

ሰንጋተራ – ጉራጌ ሰፈር***ከታች ፎቶው የተያያዘው የመላኩ ተገኝ (ዶክተር) ግለ ታሪክ፣ የዚያ ትውልድ የወቅቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ትዝታንና ትውስታን መሰረት ተደርጎ የተጻፈ ባለ...
02/11/2025

ሰንጋተራ – ጉራጌ ሰፈር
***
ከታች ፎቶው የተያያዘው የመላኩ ተገኝ (ዶክተር) ግለ ታሪክ፣ የዚያ ትውልድ የወቅቱ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ትዝታንና ትውስታን መሰረት ተደርጎ የተጻፈ ባለ 300 ገጽ መጽሐፍ ነው።

በዚህ መጽሐፍ ላይ በ1940ዎቹ በአዲስ አበባ በተለይም ሰንጋ ተራ የሚኖሩ ጉራጌዎች ባህሪይ፣ ጠባይ እና የወቅቱ የአኗኗር ዘይቤ በጥቂቱ እንዲህ ሰፍሯል።...............

"እኔና ወንድሜ የተወለድነው ሰንጋተራ ከ'ደሬ ውኃ ስንቁ'' ሰፈርና ጉራጌ ሰፈር” መሀል ባለው በ'ብላታ በቀለ ግቢ ውስጥ ነው። እኔ ትዝ የሚለኝ ግን ጉራጌ ሰፈር ስንኖር ነው። ደሬ ጉራጌ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው ዛሬ አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ካለበት በስተጀርባ የነበረው ሰፈር ነው። ወይን ("ንብ ባንክ እና ዙርያ ገባው" አካባቢ)

የኛ ቤት በጉራጌ ሰፈር ዋናው መንገድ ላይ ሲሆን በጣም ብዙ ሰው የሚመላለስበት ነበር። ግመሎችን የሚነዱና ሸቀጥ በአህያ የጫኑ ነጋዴዎች ወደ መርካቶ ሲሄዱ፣ የኦርማ–ጋራዥ ሠራተኞችና ተማሪዎች በበራችን ሲያልፉ ትዝ ይለኛል።

ደጃፍ እናቴ የምትሠራውን እየሠራች ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን እመለከት ነበር። ለዓይን ያዝ ሲያደርግ የጎረቤታችን የወንድሙ አባት ክራራቸውን ሲጫወቱ የሚያመሹት ነገር ዛሬም ድረስ አልተረሳኝም።

ጠዋት ጠዋት እማማ ትክከሏ #“በላለዴ ምጣ" ሳይሉ አያልፉም ነበር።

ከበስተኋላችን ከሚኖሩት ጎረቤቶች ደግሞ ጠዋት ጠዋት ላም ስትታለብ፣ ቡና ሲወቀጥ፣ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ሲዘገጃጁ ይሰማል፤ በሰንጋ ተራ።

አብዛኛው ነዋሪ ትሑትና ሰው አክባሪ ነበር።

በሳምንቱ በተወሰኑ ምሽቶች መንደርተኛው ሁሉ አቶ ባለሜና እማማ ትክከሏ ቤት ይሰባሰባል። ቡና በትልቅ ጀበና ይፈላል፤ የበቆሎ ቆሎ ቁርስ ይቆላል።

ትላልቁ ሰው ቡና ሲጠጣ እኛ ኩታሮቹ ቆሏችንን እንበላና ከበሮ ይመጣል። ከዚያ በኋላ በጉራጊኛ ዘፈንና ጭፈራ ቤቱ ይደምቃል። እኔም ወንድ ልጅ መጨፈር ያለበትን የጉራጊኛ ጭፈራ ስልት ተማርኩ።

ያኔ የነበሩ ጓደኞቼ አይረሱኝም። ፍቅሬ፣ ጉልላት፣ ፍቃዱ፣ እነ ገረመው ዘርጋው፣ ፍቃዱ ወልዴ፣ ግርማ ጣሴና አስራት ጣሴ ታላላቆቻችን ነበሩ። እናቴ ከጉራጌ ሰፈር ሴቶች ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ስለነበራት ጉራጊኛ ልቅም አድርጋ ትናገር ነበር።"

ምንጭ:- ማህበራዊ ሚዲያ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በር በዚህ መልኩ እየተሰራ ነው
01/11/2025

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በር በዚህ መልኩ እየተሰራ ነው

የህዝባችንን ችግር የሚሰማው አንድ ተወካይ እንዴት አጣን? ***ትንናንት የተካሄደው የእንደራሴዎች ምክር ቤት ስብሰባ ህዝባችን ስለገጠመው ወቅታዊ ሁኔታ ይነሳል ብዬ ጠብቄ ነበር:: አንድ "ተ...
29/10/2025

የህዝባችንን ችግር የሚሰማው አንድ ተወካይ እንዴት አጣን?
***
ትንናንት የተካሄደው የእንደራሴዎች ምክር ቤት ስብሰባ ህዝባችን ስለገጠመው ወቅታዊ ሁኔታ ይነሳል ብዬ ጠብቄ ነበር:: አንድ "ተወካይ" እንኳን አላነሳውም::
የሶዶ ክስታኔ ቤተ ጉራጌ ሕዝብ ከዚህ ወቅት በላይ አስቸጋሪ ጊዜ ሊያሳልፍ የሚችልበት ጊዜ ያለ የሚኖርም አይመስለንም። በዚህ ፈትታኝ ወቅት እንኳን ድምፁን የሚያሰማለት ተወካይ በማጣቱ ደግሞ በጣም የሚያስቆጭ ነው::

ሶዶ ክስታኔ የተደቀነበት ችግር አሁን ላይ ከልክ በላይ አፍጥጦ ቀዬው ገብቷል። አርሶአደሩ ወደ ከተማ ተሰድዶ ሳይሆን መንደሩ ውስጥ ከሚስቱና ልጆቹ ጋር እየታፈነ፤ እየተገደለና ንብረቱ እየተቃጠለ ይገኛል። በአጭሩ ታታሪው፣ ባለታሪኩና ጨዋው ሶዶ ክስታኔ ቤተ ጉራጌ የተለያዩ ውክቢያዎችና ጥቃቶችን በገፍ እየደረሰበት ነው።

ይህን ግፍ እየደረሰበት ባለበት የተካሄደው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ አመት 2ኛ መደበኛ ስብሰባው መፍትሄ ያስቀምጣል የሚል ከፍተኛ ግምት በብዙዎች ዘንድ ተስሰጥትቶት ነበር። ይህ ስብሰባ ''ሰሚ ያጣው የሶዶ ክስታኔ ሕዝብ'' በተጨነቀበትና ሕዝቡ ከፍተኛ ምሬት ውስጥ በገባበት ወቅት የተከናወነ ነው። ነገር ግን በዚህ ስብሰባ እንኳን ፍትሃዊ የሰላምና ፀጥታ ጥያቄውን ለምክር ቤቱና ምላሽና ማብራሪያ ለመስጠት በስብሰባው ለተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጨዋነት የሚያቀርብ አንድ/አንዲት ተወካይ ሊያገኝ አልቻለም።
#ከጉራጌ ተወላጅ የተላከ መልዕክት

የአርቲስቷ ህልፈት**"የክስታኔ ጉራጌ ዘፈን ያበረከተችው አርቲስት የጌታነሽ ጣሰው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች::አርቲስቷ "የሰብ ሀገርሽ የሰብነ" በሚል ስራዋ ትታወቃለች::ለአርቲስቷ ቤተሰ...
20/10/2025

የአርቲስቷ ህልፈት
**"
የክስታኔ ጉራጌ ዘፈን ያበረከተችው አርቲስት የጌታነሽ ጣሰው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች::
አርቲስቷ "የሰብ ሀገርሽ የሰብነ" በሚል ስራዋ ትታወቃለች::
ለአርቲስቷ ቤተሰቦችና ዘመዶች መጽናናትን እንመኛለን፡፡

በጉራጌ ዞን  የተጠለሉ ከ15,000 በላይ ተፈናቃዮች መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠየቁ***ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ከኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳና ም...
17/10/2025

በጉራጌ ዞን የተጠለሉ ከ15,000 በላይ ተፈናቃዮች መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠየቁ
***
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ከኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳና ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ተፈናቅለው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ ከ15,000 በላይ ተፈናቃዮች፣ መንግሥት የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የኢትዮዽያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠይቋል፡፡

ሰዎቹ የተፈናቀሉት በ2016 ዓ.ም. መጋቢትና ሰኔ ውስጥ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ባደረሰው ጥቃት ምክንያት ሲሆን ከ15,000 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ከሚኖሩበት አካባቢ ሸሽተው በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማና አበሽጌ ወረዳ ዳርጌ ከተማ ተበታትነው ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ኢሰመኮ የፌዴራል መንግሥት ምግብና መጠለያን ጨምሮ ሌሎች ሰብዓዊ ድጋፎችን እንዲያደርጋላቸው፣ በቀድሞ አካባቢያቸው ያለውን የሰላምና ፀጥታ ሁኔታ በማረጋገጥ፣ ቤተሰብ መሥርተው በኖሩበትና ንብረት ያፈሩበት አካባቢ በዘላቂነት እንዲመልሳቸው ጠይቀዋል።
በጥቃቱ ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው የተሰደዱ ተፈናቃዮች 30,000 እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን 15,000 የሚሆኑት በጉራጌ ዞን ወልቂጤና አበሽጌ ወረዳ ሲኖሩ ቀሪዎቹ ወደተለያዩ የሐገሪቱ አካባቢዎች መሰደዳቸው ሪፖርተር የተፈናቃዮቹ አስተባባሪን ጠቅሶ ዘግቧል።

Via: Zebidar Media/ ዘቢዳር ሚዲያ

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የንግስ በዓል በምድረ-ከብድ***የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የንግስ በዓል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ የምድረ-ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም...
15/10/2025

የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የንግስ በዓል በምድረ-ከብድ
***
የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የንግስ በዓል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ የምድረ-ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በድምቀት እየተከበረ ነው፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች መልካም በዓል እንመኛለን!
ፎቶ፡- የሶዶ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኬር አውድ ፕሬስ Kere-Awed Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share