
04/08/2024
በፓሪስ 2024 ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በውሃ ዋና የወከለችው ሊና አለማየሁ በ50 ሜትር ነፃ ቀዘፋ አዲስ የኢትዮጵያ ክብረወሰን አስመዝግባለች፡፡
ሊና አለማየሁ የመጀመሪያ ውድድሯን በአራተኛነት ማጠናቀቅ ችላለች። በዚህም በ50 ሜትር ሴቶች የነጻ ቀዘፋ ውድድር ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ሳትችል ቀርታለች።
በውድድሩ የገባችበት ሰዓት 31 ሴኮንድ ከ87 ማይክሮ ሴኮንድ ከዚህ በፊት በያኔት ስዩም ተይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ክብረወሰን እንድታሻሽል አስችሏታል።
በ2012 በለንደን ኦሊምፒክ ዋናተኛ ያኔት ስዩም በ50 ሜትር ይዛው የነበረው ክብረወሰን 32:41 ሰከንድ ነበር።