
25/08/2025
የዩቶፕያ ግሪን ፈንድ 4ኛ ዙር የመኪና እቁብ ወጣ
I የዩቶፕያ ግሪን ፈንድ ሲስተምን በመጠቀም ላለፉት 4 ወራት ለመኪና እቁብ ሲቆጥቡ ለነበሩ ደንበኞች የመኪና እቁብ እጣ አወጣጥ ስነስርአት ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ታዛቢዎች በተገኙብት ዛሬ ነሃሴ 17/2017 ዓ.ም አራተኛው ዙር በስካይ ላይት ሆቴል ተከናውኗል።
የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ የአዲስ አበባ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሐላፊ በተገኙበት በዲጂታል መተግበሪያ ተከናውኗል።
ፕሮጀክቱ ሀገራችን ለምትከተለው አረንጓዴ-መር ዲጂታል ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋዖ የሚያበረክት መሆኑ ተነግሯል።
ዩቶፕያ ግሪን ፈንድ "(Utopia Green Fund) ኢንተግሬትድ የኤሌክትሪክ የመኪና ፍይናንሲንግ ሲስተም በ5 አመት ውስጥ 5,000 ደንበኞችን የኤሌክትሪክ የመኪና ባለቤት ለማድረግ የታቀደ ሲሆን እስካሁን 1,650 አባላት ሲስተም ላይ ተመዝገበዋል፡፡ ሙሉ ቅድመ ክፍያ መክፈል የማይችሉ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተለመደው የመኪና ፋይናንሲንግ በተለየ አስከ 5 አመት ድረስ እየሰሩ የሚከፍሉበት የመኪና ሊዝ አከፋፈል መመቻቸቱ ተነግሯል።
እንዲሁም ሊዙን ያለማቋረጥ ለመክፈል ይረዳቸው ዘንድ በድርጅቱ ስር በሚተዳደረው "ዮቶፕያ የኤሌክትሪክ የሜትር ታክሲ" አገልግሎት በኩል ቋሚ ገቢ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም ለመኪናዎቹ የረጅም ጊዜ ዋስትና ፣ፈጣን የቻርጂንግ ሰርቪስ፣ የተሟላ ጥገና እና መለዋወጫ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡
Via Sisay Guzay