
27/12/2022
ነገሮች ከመሆን ላይቀሩ መታገስ አቅቶን የተፃፈ ታሪክ እያለን ሌላ እንፅፋለን ትንሽ መጠበቅ ትንሽ ትዕግስት ጠፍቶ እንቅበዘበዛለን ትርጉም ለሌለው ነግር እንተጋለን::ለነፍሳችን መልስ ለመስጠት ድንጋይ በመፈንቀል ጊዜ እናጠፋለን:: እውነታውን እያወቅን እግዚአብሔር እስኪመጣ ድረስ እኛ በራሳችን plan እንሄዳለን እግዚአብሔርን አንተም እኔም እንሞክ ቀድሞ በተሳካለት ብለን እንወራረዳለን:: የእርሱን ማንነት ረስተን እስካሁን ያለነው በራሳችን የደረስን ይመስል ታዲያ እግዚአብሔር ማንነቱን ሊያስተምረን ሲፈልግ ትምክህቶቻችንን ሁሉ ሸምበቆ አድርጎ መደገፊያ ያሳጣናል :: እኛም ያለሱ ምንም እደሆንን ሲገባን መፍጨርጨር እናቆም እና እሱ ልይ እንደገፋለን :: ያኔ እግዚአብሔር የፃፈውን ታሪክ ባማረ ሁኔታ ይተርከዋል:: ያለሱ የሚሆን የለም እና በእርሱ እንደገፍ :::