
13/09/2025
"ኢትዮጵያ ትችላለች" በሚል መሪ ቃል የታላቁን ህዳሴ ግድብ የ14 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተከፈተ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁን የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ አስመልክቶ በከተማ ደረጃ በማዘጋጀት የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ በአድዋ ድል መታሰቢያ ለእይታ ክፍት አድረጓል።
በዚህ በተዘጋጀዉ የፎቶ እና የስዕል አውደ ርዕይ መክፈቻ ስነስርዓት ላይ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ ፣ናየታላቁ የኢትዮጽያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ዋና ስራ አስፈፃሚ አረጋዊ በርሔ(ዶ/ር ፣ እና ሌሎች ከፍተኛ የፈሬደራልና የከተማ ክፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተዋል።