04/10/2026
‼
➖➎➖➎➖➎➖➎➖➎➖➎➖➎
እስከ አሁን ባሉት ክፍሎች ስለ ወልድ ዘላለማዊነት አይተናል። የኦጄዎች ግን "ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን እንጂ ፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው አዲስ ኪዳን ላይ ሥጋ ሲለብስ ነው" ይላሉ።
ነገር ግን አዲስ ኪዳን ኢየሱስ ገና ሥጋ ሳይለብስና ዓለም ሳይፈጠር በፊት #ልጅ እንደነበረ በግልጽ ያስተምረናል!
በአዲስ ኪዳን የልጅነቱ ዘላለማዊነት እንዴት ተረጋገጠ?
♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
ዕብራውያን 1፥2 ፦ "... በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን።"
አብ ዓለማትን የፈጠረው #በልጁ በኩል ነው! ዓለም ሲፈጠር "ልጅ" የሚባል አካል ከሌለና ልጅነቱ ማርያም ማህፀን ውስጥ የጀመረ ከሆነ፣ አብ ዓለማትን ? ይህ የሚያሳየው ሥጋ ከመልበሱ ከዘመናት በፊት ዓለም ሲፈጠር የእግዚአብሔር ልጅ እንደነበረ ነው! 🔥🙌
🕎🕎🕎🕎🕎🕎🕎🕎🕎🕎🕎
ገላትያ 4፥4 ፦ "የዘመኑ ፍጻሜ በድረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን... ፤"
1ኛ ዮሐንስ 4፥14 ፦ "አባትም #ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንመሰክራለን።"
አንድን አካል ለመላክ፣ ያ አካል ገና ከመላኩ በፊት ህልውና ሊኖረው ይገባል። እግዚአብሔር አብ የላከው "ልጁን" ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ከማርያም ከመወለዱ እና ወደ ዓለም ከመላኩ በፊት ቀድሞውኑ #ልጅ ነበር! ✨
♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️▪️♦️
ዮሐንስ 17፥24 ፦ "አባት ሆይ... የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እወዳለሁ።"
ወልድ፣ አብ ዓለም ሳይፈጠር በፊት ይወደው እንደነበር ይናገራል። አብ "አባት" ሆኖ፣ ወልድ ደግሞ "ልጅ" ሆኖ ዓለም ሳይፈጠር በፊት የፍቅር ሕብረት ነበራቸው! ⚔️🛡
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
ቆላስይስ 1፥13-17 ፦ "...ወደ መንግሥት አፈለሰን... በኵር ነው። እርሱም ..."
እርሱ "የፍቅሩ ልጅ" ነው፤ ይህ ልጅ ደግሞ "ከፍጥረት ሁሉ በፊት" ነው።
እነዚህ የአዲስ ኪዳን ክፍሎች "የኢየሱስ ልጅነት" ማርያም ማህፀን ውስጥ የተገኘ አዲስ ማዕረግ ሳይሆን፣ የወልድ መሆኑን አፍ አውጥተው ይመሰክራሉ!
‼ ‼
የመጨረሻው ....