Hoha Multimedia and Promotion

Hoha Multimedia and Promotion የሚዲያና የማስታወቂያ ድርጅት

በቅርቡ የመከላከያ መለያን በመልበስ ከጋዜጠኛ ተ/ሀይማኖት አዳነ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረገዉ አቶ አበባየሁ ደሜ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰምቷል።
31/07/2026

በቅርቡ የመከላከያ መለያን በመልበስ ከጋዜጠኛ ተ/ሀይማኖት አዳነ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረገዉ አቶ አበባየሁ ደሜ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰምቷል።

 ! ➡️ Temesgen Hailuየቀድሞው የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ፕሬዚዳንትና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ፥ የአሁኑ የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ...
30/07/2026

! ➡️ Temesgen Hailu
የቀድሞው የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች ፕሬዚዳንትና አጠቃላይ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሰብሳቢ፥ የአሁኑ የአሶሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ተመስጌን ኃይሉ ትክክለኛ የለውጥ ምልክት ናቸው።

በዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ፕሬዝዳንትነት ዘመኑ እጅግ በርካታ ስራዎችን በመስራቱ በተማሪዎች እና በዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን ያተረፈው ብርቱው ወንድማችን፥ አሁንም በሚመራው ተቋም ላይ ውጤታማ ስራዎችን በመስራቱ ለውጥ እያስመዘገበና ብዙ አድናቆትን እያተረፈ ይገኛል።

የመምራት ችሎታው ከጥንት ነው!🙏
Via Jemal Endris

ሀገራዊ ምክክሩ ቀጥሏል፤ ስለ አዲስ አበባ፣ የፌደራል ሥርዓት፣ የዘመን አቆጣጠርና የጸጥታ ተቋማት የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበዋል‼️በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ...
29/07/2026

ሀገራዊ ምክክሩ ቀጥሏል፤ ስለ አዲስ አበባ፣ የፌደራል ሥርዓት፣ የዘመን አቆጣጠርና የጸጥታ ተቋማት የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበዋል‼️

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ፣ በሀገሪቱ የወደፊት አቅጣጫ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ አማራጭ ምክረ ሀሳቦች ቀርበዋል።

ከተነሱት አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ የአስተዳደር ሁኔታ፣ የፌደራል ሥርዓትና የክልሎች አወቃቀር፣ እንዲሁም የጸጥታ ተቋማት ገለልተኝነት ዋነኞቹ ናቸው።

በዘመን አቆጣጠር ዙሪያ አሁን ያለው ሥርዓት እንዲቀጥል፣ የእስላማዊ (ሂጅራ) የዘመን አቆጣጠር እንዲካተት፣ ወይም ከሃይማኖት ነጻ የሆነ አዲስ የዘመን አቆጣጠር እንዲዘረጋ የሚሉ አማራጮች ቀርበዋል።

በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ጉዳይም የተለያዩ አቋሞች ተንጸባርቀዋል። አንዳንዶች አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል እንድትሆን ሲጠይቁ፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንድትካተት ሀሳብ አቅርበዋል።

ሌላ አማራጭ ደግሞ ከተማዋ የሁሉም ኢትዮጵያውያንና የዲፕሎማሲ ማዕከል በመሆኗ በፌደራል መንግሥት ስር እንድትቆይ የሚል ነው። ድሬዳዋም በቀጥታ ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ እንድትሆን እና የሥልጣን ክፍፍሉ ፍትሃዊ እንዲሆን ሀሳብ ቀርቧል።

በፌደራል ሥርዓት ላይም አሁን ያለው ሥርዓት እንዲቀጥል፣ እንዲሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ ተከልሶ አዲስ የክልል አወቃቀር እንዲዘረጋ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክልሎች በቋንቋ ሳይሆን በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ እንዲደራጁ፣ እንዲሁም ሀገሪቱ በአምስት ዋና ዋና ክልሎች እንድትዋቀር የሚሉ ምክረ ሀሳቦችንም አቅርበዋል።

በሰላም ግንባታ ዙሪያ የተካሄደው ውይይት ደግሞ የጸጥታ ተቋማት ከፖለቲካ ተጽዕኖ ውጭ ሆነው ለሀገር ብቻ የሚያገለግሉ ተቋማት እንዲሆኑ የሚጠይቅ ምክረ ሀሳብ አካትቷል።

በተጨማሪም በአዲስ አበባ የቦታዎች መጠሪያዎችና በሀገር ደረጃ የሚቆሙ ሀውልቶች ሁሉንም የሚያካትቱ እንዲሆኑ፣ ለ«የአገር ጀግና» የሚሰጥ ማዕረግም ግልጽ መስፈርት እንዲኖረው የሚሉ ሀሳቦች ቀርበዋል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፣ በምክክሩ የቀረቡት ሀሳቦች የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልሆኑ ገልጸው፣ እስካሁን የተቀመጡት በተሳታፊዎች የቀረቡ አማራጭ ምክረ ሀሳቦች ብቻ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በአጀንዳዎቹ ላይ ውሳኔ ተላልፏል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑንም በማስጠንቀቅ፣ የውሳኔ ሂደቱ ገና በቀጣይ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ሬዲዮ

ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፣ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን!!!ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነ...
26/07/2026

ቅዱስ ገብርኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፣ የልባችንን መልካም መሻትም ይሙላልን!!!

ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-
ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-
0918077957 ወይም 0938644444

24/07/2026

Big shout out to my new rising fans! Yibeltale Bishaw

ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት የ2 ዓመት ህፃን እንዳትጮህ አፉን በማፈን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ    በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ኤዳ ዳቡስ ቀበሌ ...
22/07/2026

ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት የ2 ዓመት ህፃን እንዳትጮህ አፉን በማፈን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ ኤዳ ዳቡስ ቀበሌ ጎጥ አንድ በሚባል አካባቢ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈፅሟል።የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አዛዥ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት ተከሳሽ አወድ አልሀሪብ የተባለ ሲሆን ግንቦት 16 ቀን 2018 ከረፍዱ 4፡00 ሰዓት የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሟል።

የ2 አመት ህፃን የሆነችውን ገላሽን በሙቅ ውሃ አጥብሻለሁ በማለት እናቷ ውሃ ልትቀዳ መሄዷን በማረጋገጥ ወደ ራሱ መኖሪያ ቤት ከወሰዳት በኋላ አፏን በማፈን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡

የባምባሲ ወረዳ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች በማስደገፍ ለዐቃቤ ህግ ያቀርባል ዐቃቤ ህጉም ተከሳሹ በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 627(1) ስር በተደነገገው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ለባምባሲ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል፡፡

ፍርድ ቤቱ የቀረበውን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ተከሳሹን ጥፋተኛ መሆኑን በማረጋገጥ የወንጀሉን ክብደትና የቅጣት ማክበጃ እና ማቅለያ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲሉ ኮማንደር ሀሩን ሄረላ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

አርቲስት ጎሳየ ተስፋየ ታሞ ገባ ‼️ተወዳጁ አርቲስት ጎሳየ ተስፋየ በሀገረ እንግሊዝ የነበረዉን ኮንሰርት ለመስራት ከሳምንታት በፊት ወደ ለንደን አቅንቶ ነበር። አርቲስቱ የኮንሰርት ቆይታዉን...
21/07/2026

አርቲስት ጎሳየ ተስፋየ ታሞ ገባ ‼️

ተወዳጁ አርቲስት ጎሳየ ተስፋየ በሀገረ እንግሊዝ የነበረዉን ኮንሰርት ለመስራት ከሳምንታት በፊት ወደ ለንደን አቅንቶ ነበር። አርቲስቱ የኮንሰርት ቆይታዉን አጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ሲደርስ ግን በህመም ምክንያት በዊልቼር እየተገፋ ገብቷል። እግዚአብሔር በምህረት አይኖቹ ይጎብኝህ ወንድማችን‼️

20/07/2026

የሚሸጥ ግሪን ደብተር ቦታ!
አሶሳ ካምፖስ በአዲሱ በር በኩል ወደ አምባ 8 መሄጃ መስመር ላይ 250 ካሬ አለ ገዢ ከሆኑ ብቻ ብሩ በአስቸኳይ ተፈልጎ ነው ይደውሉ 0902168922

ሼር በማድረግ ተባበሩን!!አቶ  #ማስረሻ ሰኞ ዕለት (በቀን 06/11/2018 ዓ.ም) ጠዋት ለስራ እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም፤ ቤተሰቦቻቸውም በጉጉትና በጭንቀት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።ይ...
17/07/2026

ሼር በማድረግ ተባበሩን!!

አቶ #ማስረሻ ሰኞ ዕለት (በቀን 06/11/2018 ዓ.ም) ጠዋት ለስራ እንደወጡ እስካሁን አልተመለሱም፤ ቤተሰቦቻቸውም በጉጉትና በጭንቀት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
ይህን ግለሰብ ያያችሁ ወይም ያለበትን መረጃ የምታውቁ ደግ ሰዎች ሁሉ እባካችሁን በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል እንድትጠቁሙን በትህትና እና በመማጸን እንጠይቃለን፦
ቤተሰቦች
📞 0915890861

📞 0922243403

እባክዎን መረጃው ለብዙዎች እንዲደርስና ለቤተሰቡ እንዲገኝ ይህንን ፅሁፍ ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን።

የቴሌ መሰረተ ልማት የሰረቁ በቁጥጥር ዋሉ።በአሶሳ ከተማ የቴሌ አውታር ገመድ ዝርጋታ የሰረቁት አራት ተጠርጣሪዎች ከነኢግዚቪቱ ተይዘው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖ...
16/07/2026

የቴሌ መሰረተ ልማት የሰረቁ በቁጥጥር ዋሉ።

በአሶሳ ከተማ የቴሌ አውታር ገመድ ዝርጋታ የሰረቁት አራት ተጠርጣሪዎች ከነኢግዚቪቱ ተይዘው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ገልጿል ።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ቀጠና አምስት ልዩ ስፍራው አዉራ ጎዳና ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ እለቱ ማክሰኞ ሐምሌ 7 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 3:30 ሰዓት ሲሆን 1ኛ አበበ ደሰለኝ አድሴ ፤ 2ኛ/ መለሰ ከበደ ወርቁ ፤3ኛ/አይቸው ብርሀኑ ሀይሉ እና 4ኛ/ ኤፍሬም ሹምድ ጉግሳ የተባሉት በመሬት ውሰጥ የተቀበረውን የቴሌ አውታር መሰመር ገመድ እጅ ከፍንጅ ሲቆፍሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል ።

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ከወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር የምርመራ ቡድን አቋቁሞ የምርመራ ሂደቱን እያጣራ ይገኛል ።

ተጠርጣሪዎቹ ለወንጀልነት ሲጠቀሙበት የነበረው ዲጂኖ መቆፈሪያ በመያዝ ጨለማን ተገን በማድረግ የህዝብ መሰረተ ልማት ሀብት የሆነውን የኔትወርክ አውታር ገመድ በመቁረጥ ላይ እንዳሉ ለስራ በሚንቀሳቀሱ የቀበሌ ኮሚኒቲ ኦፊሰር እና በፓትሮል ቅኝት ላይ በነበሩ አጋዥ ኃይሎች እንዲያዙ ተደርገዋል ።

ወቅቱ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለማሰናከል ተጠርጣሪዎቹ ሆን ብለው ይህን የወንጀል ድርጊት ፈጽመው ተገኝተዋል ተብሏል

በመጨረሻም ለህዝብ ጥቅም የተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ እየደረሰ ያለውን የስርቆት ወንጀል ለመከላከል የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚገኙ የመሰረተ ልማት አውታሮችን በመጠበቅ የወንጀል ድርጊት ፈፃሚዎችን በማጋለጥ እና መረጃ በመስጠት ለፖሊስ የወንጀል መከላከል ሥራ ድጋፉን ሊያጠናክር እንደሚገባ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አሳስቧል ።

Address

Asosa
Addis Ababa
5220

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hoha Multimedia and Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share