12/07/2021
የከፍተኛ ትምህርት ምርምር እና ቴክኖሎጂ ትሥሥር ኮንቬንሽን የመክፈቻ ስነ ስርዐት እየተካሄደ ነው።
ለአራት ቀናት የሚቆየው ኮንቬንሽኑ፤ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲዎች መሪዎች በተገኙበት የመክፈቻ ስነስርዐቱ እየተደረገ ይገኛል።
ከመክፈቻ ስነ ስርዐቱ አስቀድሞ፤ የከፍተኛ ትምህርት፣ የምርምር እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አውደ ርዕይን ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጎብኝተዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው መድረኩ፤ የፈጠራና ምርምር ስራዎችን ለማበረታታት እና ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ተብሏል።
ዩኒቨርስቲዎች፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሃብቶች እና ፖሊሲ አውጪዎች በጉባኤው እየሳተፉ ይገኛሉ።
ጉባኤው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ በጋራ የተዘጋጀ ነው።
https://t.me/EthiopianEducationalTelevision